አፍሪካ የቡድን ሃያ አገራት ቋሚ አባል ሆነች

የአፍሪካ አገራት ወደ ብሪክስ የመጉረፍ ስሜት ይፋ ሲሆን የቡድን 20 አባል ሀገራት ሃምሳ አምስት አባል አገራትን ያቀፈውን የአፍሪካ ህብረትን ቋሚ አባል አድርጎ መቀበሉ ይፋ አደረገ። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኒው ደልሂ እየተካሄደ ባለው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ህብረት ቡድኑን መቀላቀሉን ገልጸዋል። ውሳኔው ለአፍሪካ የጸጥታው ምክር ቤት አባልነት ምልክት ሆኖ ተወስዷል።

የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ቋሚ አባል እንዲሆን የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ሁሉም የአባል ሀገራቱ መሪዎች እንደተስማሙበት ተመልክቷል። በኢንደስትሪ የበለጸጉና ከአዳጊ አገራት የላቀ የምጣኔ ኃብት ዕመርታ ያስመዘገቡት አገራት መሰባሰቢያ የሆነው ህብረቱ አፍሪካ በአንድ ድምጽ መወከሏን በሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ በኩል ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረትን ሊቀመንበር የሆኑትን የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በቡድን 20 ለህብረቱ የተዘጋጀውን መቀመጫ እንዲይዙ ተጋብዘው ስፋራቸውን ወስደዋል።

ደቡብ አፍሪቃ የተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨመሮ ስድስት አገራትን መቀበሉን ተከትሎ የቡድን ሃያ አገራት አፍሪኪአን በአባልነት ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውንና ግብዣ ማቅረባቸውን የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ አስታውቀው እንደነበር ይታወሳል።

ቢቢሲ ይህን ዜና አስታኮ የሚከተለውን ዘገባ አካቷል። በቡድን 20 አገራት ጉባኤ ላይ ከሚነሱ ነጥቦች አንዱ የዩክሬን ጉዳይ የነበረ ሲሆን፣ ቢቢሲ ይፀድቃሉ ከተባሉ ሰነዶች መካከል የተመለከተው ሰነድ እንደሚጠቁመው ስለ ዩክሬን እስካሁን የተጠቀሰ ነገር የለም። ሰነዱ የባንክ ዘርፍን ማሻሻልና ክሪፕቶከረንሲን መቆጣጠር ጨምሮ ሌሎችም ነጥቦችን ያካተተ ነው።

በሌላ በኩል የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሕንድን ‘ባሐራት’ በሚል ስም መጥራታቸው ውዝግብ ፈጥሯል። አገሪቷ ስሟን በይፋ ስለመቀየሯ እስካሁን የተባለ ነገር ግን የለም።

ሌላው በጉባኤው የሚነሳው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ነው። ታዳጊ አገራት የበለጠ ተጎጂ ስለሚሆኑ ካደጉ አገራት አንዳች መተማመኛ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ሲገለጽ ቆይቷል። የመጀመሪያው የቡድኑ ውይይት አንድ ምድር ወይም ‘One Earth’ የሚባል ሲሆን የአካባቢ ጉዳይን የተመለከተ ይሆናል።

ታዳጊ አጋራት በሕንድ ተወክለው በሚካሄደው ውይይት ሃብታም አገራት የካርበን ልቀትን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት በገንዘብ፣ ቴክኖሎጂና መሠረተ ልማት እንዲደግፉ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።

See also  ከ400 በላይ ተጠርጣሪ ሌቦች በድንገተኛ ኦፕሬሽን ተያዙ

Leave a Reply