ጀርመን የኢሚግሬሽን ህጓን እያሻሻለች መሆኑን የጠቀሱት ክሊንግቢል ጸረ ሴማዊነትን እና ሽብርን የሚደግፉት ግን የጀርመን ፓስፖርታቸውን ይነጠቃሉ ብለዋል።
በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ጀርመን የምትከተለው ፖሊሲ
በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ጀርመን የምትከተለው ፖሊሲ
ጀርመንን ጨምሮ በአውሮጳ፣ አሜሪካና ሌሎች ሃገራት “አሸባሪ” ተብሎ የተሰየመው ሐማስ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዓ.ም የጋዛን አጥር ሰብሮ በመግባት በሙዚቃ ድግስ ላይ የነበሩትን ስቪል እስራኤላውያን ላይ በፈጸመው ጥቃት ከ260 በላይ እስራኤላውያን መሞታቸውን ተዘግቧል። ከዚያም ቀጥሎ ሃማስ ወደ እስራኤል በተኮሳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተወንጫፊ ሮኬቶችና ከባድ መሳሪያዎች እንዲሁም እስራኤል በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ከሁለቱም ወገኖች በርካታ ንጹሃን ስቪል ዜጎች አልቀዋል። እስከዛሬ ረፋዱ ድረስ የነበሩ የጉዳት መጠንን የሚያመላክቱ ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስራኤል በፈጸመችው የበቀል እርምጃ ከፍልስጤማውያን በኩል 2,800 ገደማ ሲሞቱ ሃማስ ባስወነጨፋቸው ሮኬቶችና መድፎች ደግሞ ከ 1,400 በላይ እስራኤላውያን ሞተዋል። ከሁለቱም ወገን ከ6ሺህ የማያንሱ ሰዎች እንደቆሰሉም የተለያዩ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
በሁለቱም በኩል የቀጠለውና ሁለተኛ ሳምንቱን ያሳለፈው ጦርነት ወደ አካባቢው ሐገራት እንዳይዛመት አስግቷል። በተለይም “ከጀርባ አለች” የምትባለው ኢራን በቀጥታ እጇን ካስገባች ጦርነቱ ከቀጠናዊ ጉዳይንነት ወጥቶ ዓለም አቀፋዊ ቅርጽ ሊይዝ እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
የተለያዩ የዓለም ሃገራት በዚህ ጦርነት ላይ የሚከተሉት ፖሊሲና ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና በይፋ እየገለጹ ነው። ጀርመንም ጦርነቱን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲና በሃገር ውስጥም መተግበር ስለሚገባቸው መመሪያዎች ይፋ አድርጋለች።
የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ለምክር ቤት እንደራሴዎች ባደረጉት ንግግር እንደተናገሩት።
” በዚህ ወቅት ጀርመን አንድ አማራጭ ብቻ ነው ያላት፤ ከእስራኤል ጎን መቆም። ይህም ለእስራኤል ደህንነት መቆም ትልቁ የጀርመን መንግስት ቁርጠኝነት ነው ማለታችን ነው። ከራሳችን ታሪክ ከሆሎኮስት የመነጨው ሃላፊነት፤ የእስራኤልን መንግስት ህልውና እና ደህንነት መደገፍ ዘልአለማዊ ያደርገዋል።
በእስራኤል የሃገሪቱን ዜግነት የወሰዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጀርመናውያን አሉ። በዚህ በጀርመንም በሺዎች የሚቆጠሩ የጀርመን ዜግነት የወሰዱ እስራኤላውያን ይኖራሉ። በሃማስ ከታገቱት መካከል በርካታ ጀርመናውያን ይገኙበታል።”
ስለ ኢራን
ከሃማስ ጀርባ ኢራን እንዳለችበት አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሃገራት ይከሳሉ። መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስም ከኢራን ድጋፍ ውጭ ሃማስ ይህን ጥቃት ሊፈጽም እንደማይችል ነው ያስረዱት።
“ሃማስ ከአለፉት ዓመታት ጀምሮ ያለኢራን ድጋፍ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት በእስራኤል ግዛት ውስጥ ሊፈጽም አይችልም። የኢራን አገዛዝ ባለስልጣናትና አንዳንድ የመንግስት ተወካዮች ጥቃቱን አስመልክተው የሰጡአቸው መግለጫዎች በጣም የወረዱ እና ደስ የማይሉ ናቸው። በቴህራን ውስጥ ያለው አመራር ያለምንም ሃፍረት እውነተኛ ገጽታውን እየገለጠ ነው። ይህም በጋዛው ጦርነት ላይ ያለውን ሚና ያረጋገጠ ነው።”
ስለፍልስጤም ባለስልጣናት
ከዚ በተጨማሪ ሾልስ በእስራኤል ስለደረሰዉ ጥቃት የፍልስጤም ባለስልጣናት ዝምታን አውግዘዋል።
“የፍልስጤም ባለስልጣናት እና ፕረዚደንት ማህሙድ አባስ ለምን ይህን የሽብር ጥቃት አላወገዙም ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። ዝምታቸው አሳፋሪ ነው ለማለት እወዳለሁ።”
ለፍልስጤም ስለሚደረጉ የልማት ድጋፎች
ሾልስ ለፍልስጤማውያን ስለሚደረገው ድጋፍም መንግስታቸው የሚከተለውን ፖሊሲ ይፋ አድርገዋል። ከፍልስጤም ጋር የሚኖረው የልማት ትብብር እንደሚያጤኑት እና የእስራኤልን ደህንነትና ጸጥታን በሚያረጋግጥ መልኩ እንደሚፈጸም አስረድተዋል። ከጀርመን መንግስት በኩል የሚደረጉ ማንኛውም ድጋፎች በሃማስ እጅ እንዳይወድቁ መንግስታቸው ብርቱ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ነው መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ይፋ ያደረጉት።
በጀርመን ስለሚኖሩ የሃማስ ደጋፊዎች
ሌላው መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ያነሱት ጉዳይ በጀርመን ውስጥ የሚኖሩ የሃማስ ደጋፊዎችን በተመለከተ ነበር። የሃማስ ደጋፊዎች በተለያዩ የጀርመን ከተሞች ባካሄዷቸው ሰልፎች የእስራኤልን ባንዴራ አቃጥለዋል፤ ጀርመንን ጨምሮ በአውሮጳና አሜሪካ እንዲሁም በሌሎች ሃገራት “አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀውን ሃማስን እንደሚደግፉ ገልጸዋል። መራሄ መንግስቱ በእነዚህ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ነበር አስረግጠው የተናገሩት። የሃማስን ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን ያሉት ሾልስ ከምንም በላይ ይህን ጥቃት በመላው አካባቢው ላይ ወደለየለት ግጭት እንዳይቀየር የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው፤ እናም ሁሉም ሰው በዚህ ሁኔታ ሽብርን ከማባባስና ከማስቀጠል እንዲቆጠብ እናስጠነቅቃለን ሲሉም አክለዋል።
ይህን ሽብር የሚያወድስና የሚደግፍ ሁሉ ተጎጂዎችን ማዋረድ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ክብርንና የጀርመንን ህገመንግስት የረገጠ ተግባር ነው። እንደዚህ አይነት ተግባር ያስደነግጠኛል ትክክልም አደለም። በማለትም ለሸንጎው አስረድተዋል።
በጀርመን ለሃማስ ድጋፍ ያረርጋሉ የተባሉት የተለያዩ አደረጃጀቶችም እንደሚታገዱም ነው ጀርመን ያስታወቀችው። ከነዚህም አንዱ ሳሚ ዱን የተባለ የፍልስጤም የትብብር መረብ እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የትብብር መረቡ አባላት በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ሃማስ በእስራኤላውያን ላይ ጥቃት በመፈጸሙ ደስታቸውን ሲገልጹ፤ እንዲሁም ለአላፊ አግዳሚው እንደቸኮሌት ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን ሲበትኑ ታይቷል። መራሄ መንግስት ሾልስ ይህን ድርጊት የጀርመንን እሴቶች እንደሚጻረር በመግለጽ በጀርመን ውስጥ በምልክት ጭምር የሃማስን የወንጀል ድርጊቶችን ማወደስ በሕግ እንደሚያስጠይቅ በአጽንኦት አስረድተዋል።
በጀርመን ውስጥ ወደ 500 የሚሆኑ የትብብር መረቡ አባላት ያሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ የጀርመን ዜግነት ያላቸው መሆኑን ይነገራል። የጀርመን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈጽሙትን ፓስፖርታቸው እንደሚነጠቁና እንደሚባረሩ ነው ያስጠነቀቀው።
ሚንስቴር መስሪያቤቱ በሃማስ ደጋፊዎች ላይ ጠንከር ያለ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ በገለጸበት መግለጫው የሃማስ ደጋፊዎችን ከሃገሩ እንደሚያባርራቸው በሚኒስትሯ በኩል ይፋ አድርጓል። የጀርመን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ፌዘር የሃማስ ደጋፊዎችን ለማባረር ማንኛውም ሕጋዊ እርምጃ እንጠቀማለን ሲሉ ነው በመግለጫቸው የተናገሩት።
የ ናንሲ ፌዘር መግለጫ በሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪም ድጋፍ አግኝቷል። የፓርቲው መሪ ሎርስ ክሊንግቢል “የሃማስ ደጋፊዎች፤ በጎዳናዎች ላይ ወጥተው ሃማስን የሚደግፉ ከሆነ ከጀርመን ይባረራሉ” ሲሉ ዝተዋል። አክለውም በሃማስ ደጋፊዎች ላይ ሁሉም ሕጋዊ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለዋል።
ጀርመን የኢሚግሬሽን ህጓን እያሻሻለች መሆኑን የጠቀሱት ክሊንግቢል ጸረ ሴማዊነትን እና ሽብርን የሚደግፉት ግን የጀርመን ፓስፖርታቸውን ይነጠቃሉ ብለዋል።
dw report
- በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉበትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በትህነግ መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው… Read more: በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉ
- የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉበተመረጡ ቦታዎች፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን ፋኖ አስታወቀ። ይህን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአባይ ድልድይን ለመመረቅ ወደ ባህር ዳር እንዳይመጡ ለ”ቅድሚያ… Read more: የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉ
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ።… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ