Site icon ETHIOREVIEW

የባህር በር ህልውናችን!! አብይ አህመድ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” ሲሉ አወጁ

የአባይ አጀንዳ ሲቋጭ የቀይ ባህር ጉዳይ መነሳቱ አጀንዳው እጅግ ተደርጎ የታሰበበት ለመሆኑ ማሳያ ተደርጓል። “የቀይባህር አጀንዳ ሃሳብ ማስቀየሪያ ነው” በማለት ለፕሮፓጋንዳ የሚነሱ የማይሳካላቸው በዚሁ መነሻ እንደሆነም ተመልክቷል። እጅግ ሰላማዊ በሆነና በስጥቶ መቀበል መርህ አማራጮችን አቅርበው ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን እንዳለባት ያመለክቱት አብይ “ጉዳይ የህልውና ነው” ብለውታል።

መለስ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ”ሲሉ አሰብ ወደብና ቀይ ባህርን አስመልክቶ ለተከራከሩ የሰጡት መልስ ነበር። ኢትዮጵያን የሚያክል አገር የተቆለፈባት እንድትሆን የተስማማው ትህነግ፣ ላለፉት ሰላሳ አመታት ኢትዮጵያ አንጡራ ሃብቷን እንድትበትን ፈርዶባት ኖሯል። የድርጅቱ መሪ መለስ ” አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ከኤርትራ መቀማት ይቀላል” በሚል ስጋት ወደፊት “አገር” የመሆን ህልማቸውን አስልተው መናገራቸውን ምስክሮች መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በድርጅት ወይም በፓርላማ አባልነታቸው ሳይሆን፣ በአንድ አገር ወዳድ እንደሚናገሩ አስታውቀው እንደተናገሩት የቀይ ባህርና የአባይ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ህልውና ናቸው። ሑሉም የኢትዮጵያ ንብረት ሆኖ ሳለ፣ ስለ አባይ ማንም እንደማይፈራን፣ እና ግን ህጋዊ መብት ስላለን ቀይ ባህር መናገር እንፈራለን ሲሉም ፍርሃቻው አግባብ አልነበረም ብለዋል።

አብይ አህመድ አዲሱ ዓመት በርካታ ድሎች የሚገኙበት እንደሆነ መናገራቸው አይዘነጋም። አብይ አህመድ ትልቅ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ማስቀመጣቸን ተከትሎ ህዝብ በስፋት እየተነጋገርበት ነው። አብይ አህመድ ያስቅመጡትን ትላቅ አጀንዳ የሰሙ ” ምን አለበት ሻለቃ አድማሴ ይህን አዋጅ ቢሰሙ” ብለዋል።


Exit mobile version