Site icon ETHIOREVIEW

የአሜሪካ አትላንቲክ ካውንስል ተመራማሪ ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የፈጸሙት ስምምነት “ታሪካዊ” ሲሉ አደነቁ

በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በሰጥቶ መቀበልና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ነው ሲሉ በሣህል ቀጠና የቀድሞ የአሜሪካ ልዩ መልክተኛና የአትላንቲክ ካውንስል የፖለቲካ ጉዳዮች ተመራማሪ አምባሳደር ጄ ፒተር ፋም ገለጹ። አትላንቲክ ካውንስል የአሜሪካን የፖሊሲ ግብዓት ማዕከል ከመሆኑ አንጻር አስተያየታቸው ከፍተኛ የፖለቲካ ፋይዳ እንዳለው ተመልክቷል።

አምባሳደር ጄ ፒተር ፋም በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት÷ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያለማቅማማት በመግለጽ እንዳሉት ከሆነ የአፍሪቃ ቀንድንም የሚያሻሽል በረከት ይዞ ይመጣል።

ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ብዛትና የመልማት አቅም እንዲሁም ከወደብ ኪራይ ዋጋ ውድነት አንጻር በጅቡቲ ወደቦች ላይ ብቻ ጥገኛ ሆና መቀጠል እንደማትችል ከተገነዘበች ቆይታለች ሲሉ መሰረት አሲዘው ጉዳይን በጥልቅ እንደሚያውቁት በሚያሳይ መልኩ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ላይ የቀረቡት አምባሳደሩ የመግባቢያ ስምምነቱ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ነባራዊ ሁኔታዎች ያገናዘበ፣ በሰጥቶ መቀበልና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ መሆኑንም በመጥቀስ ስምምነቱ ቀጠናውን ስለማ ይነሳል በሚል ለሚቀርበው አስተያየት የተቃርኖ ምልሽ ሰጥተዋል። እንደውም ያሻሽለዋል ነው ያሉት። የተደረሰው ስምምነት የቀጣናውን ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ ሊያሻሽል እንደሚችል ገልጸዋል።

በፈረንጆቹ በ1960ዎቹ በርካታ ሀገራት ሶማሊላንድን በነጻና ሉዓላዊት ሀገርነት እውቅና ሰጥተዋት የነበረ መሆኑን አስታውሰው ÷ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከሶማሊያ ግዛት ጋር እንድትቀላቀል ተደርጓል ነው ያሉት።

ከዚያድ ባሬ አስተዳደር መፈራረስ በኋላ ሶማሊላንድ የራሷ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች በማድረግ የራሷን አስተዳደር ምስረታ ከ30 ዓመታት በላይ መቆየቷንም አንስተዋል።

ከኢትዮጵያ ባሻገር ሌሎች ሀገራትም በሶማሊላንድ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ ንግግራቸው ” ምነው ኢትዮጵያ ላይ ሲሆን ብቻ ጫጫታ አስነሳ” በሚል ዜጎች ከሚያቀርቡት የቁጭት አስተያየት ጋር ተመሳስሏል።

ለአብነትም የእንግሊዝ ኩባንያዎች ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ዱባይ ፖርትስ ኩባንያ ጋር በመሆን ቢሊየን ዶላሮችን በማውጣት በበርበራ ወደብ ልማት ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ቢዘገይም ቢፈጥንም፤ ቢፈለግም ባይፈለግም ሶማሊላንድ ዓለም አቀፍ እውቅና የማግኘቷ ጉዳይ አይቀሬ ነው ሲሉም ተናግረዋል አምባሳደሩ።

Exit mobile version