Site icon ETHIOREVIEW

የኤርትራ አምባሳደር ከአገሯ ለቀው እንዲወጡ ዩናይትድ ኪንግደም አዘዘች

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በለንደን የኤርትራ አምባሳደር አገር ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። እንግሊዝ የኤርትራውን አምባሳደር ከሎንዶን ውጡ ማለቷን ተከትሎ ከኤርትራ በኩል ይህ እስከተጻፈ ድረስ የተባለ ነገር የለም።

ከዲፕሎማቲክ ምንጮች መስማቱን ገልጾ የዘገበው ቢቢሲ እንዳለው አምባሳደር እስጢፋኖስ ሃብተማርያም አገር ለቀው እንዲወጡ ከመታዘዙ ውጭ እንግሊዝ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችበትን ምክንያት አልዘረዘረም።

ኤርትራና እንግሊዝ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ቢሆንም፣ እንግሊዝ በተደጋጋሚ ኤርትራን በሰብአዊ መብት ረገጣና በትግራይ በተፈጸመ ጥቃት አጠንክራ ኤርትራን ተጠያቂ ከሚያደርጉ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ከሚያወግዙ አገራት መካከል ግንባር ቀደም መሆኗ ይታወቃል።

በተገባደደው 2023 የነጮቹ ዓመት፣ በኤርትራ የዩኬ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ዲፕሎማት በኤርትራ መንግሥት በኩል ለአንድ ዲፕሎማት ሊደረግ በሚገባ ደረጃ ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ወደ አሥመራ መጓዝ ሳይችሉ እንደቀሩ ይታወሳል።

ይህ የአሁኑ የዩኬ ውሳኔ ለዚያ አጻፋዊ ምላሽ ይሁን በሌላ ልዩ ምክንያት ለጊዜው የታወቀ ጉዳይ የለም። የኤርትራው አምባሳደር ሎንዶንን ለቀው እንዲወጡ ቢደረገም የአምባሳደሩን ቦታ በመሸፈን የኤምባሲው (ሚሲዮን) ከፍተኛ ተጠሪ በመሆን የሚሠሩት ሳሌህ አብዱላህ ስለመሆናቸው ቢቢሲ የኤርትራ ኤምባሲ ድረ-ገጽ ጠቅሶ ዘግቧል።

የኤርትራ ባለሥልጣናት የዩኬ ተሿሚ አምባሳደር ወደ ምድብ ቦታቸው ገብተው ሥራቸውን እንደጂምሩ ለምን አስፈላጊውን ነገር እንዳላደረጉ የተሰጠ እስካሁን የተሰጠ ምክንያት የለም።

Exit mobile version