Site icon ETHIOREVIEW

አል ሸባብ ሦስት የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ካምፖችን ተቆጣጠረ

አልሸባብ ጋልሙዱግ በሚባል ክልል ከሶማሌ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ ሶስት የሶማሊያ ጦር ካምፖችን በቁጥጥሩ ስር አድርጓል።

አል ሸባብ ከሶማሊያ ጦር ጋር አምስት ሰዓታት ያህል የቆየ ከባድ ጦርነት ካካሄደ በኋላ ከጥቃቱ የተረፉ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር የ”ጎርጎር ኮማንዶ” መኮንኖችና ወታደሮች እንደተናገሩት በውጊያው ከ230 በላይ  የሶማሊያ ወታደሮች መሞታቸውን እንዳረጋገጡና ስፍር ቁጥር የሌላቸው መቁሰላቸውን ገልፀዋል።

የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር በቦታው ያሰፈራቸው ወታደሮቹ 4 ሻለቃ የ”ጎርጎር ኮማንዶዎችን” ሲሆን 15 የአል ሸባብ አሸባሪዎች ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ሞትና የአካል ጉዳት አስተናግዷል።

የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር በአል ሸባብ ከበባ ውስጥ ሆኖ ምንም ዓይነት የሽፋን ኃይል ማሰማራት አልተቻለውም ተብሏል።

ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ በአል ሸባብ የሽብር ቡድን ላይ ዘመቻ ጀምሬያለሁ ካሉበት የቅርብ ጊዜ መግለጫቸው ወዲህ ብቻ የተገደሉ ወታደሮች ቁጥር ከ 4,000 በላይ ሲደርስ ከ300 በላይ የሶማሊያ ጦር አዛዦችም በሽብር ቡድኑ መገደላቸውን ዘገባዎች አስታውሰዋል። (Esleman Abay)

Exit mobile version