Site icon ETHIOREVIEW

አብይ አሕመድ – የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደርን “በጥብቅ” እየተገመገሙ ነው

ትግራይን ቢጊዚያዊነት እንዲያስተዳድር የተሰየመው የአቶ ጌታቸው አመራር “ጥብቅ” የተባለ ግምገማ ላይ መሆኑንን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባሰራጨው መረጃ ይፋ አድርጓል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩትን ስራዎች እና መሻሻሎች በጥልቀት መገምገም ጀምረዋል። ይህ በፌደራል እና የክልል ኃላፊነት ባላቸው የስራ ተዋንያን የሚደረገው ጠቃሚ ግምገማ በድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ እና በሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ነው” ሲል ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

በቪዲዮ ምስል የተሰራጨው ይህ ዜና በግመገማው ላይ ለአስረጅነት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ካቢኔዎች ሙሉ በሙሉ ተገኝተዋል። ይህም ማለት ግምገማው ሲካሄድ በየዘርፉ ለሚቀርበው ጥያቄም ሆነ ምላሽ የጉዳዩ ባለቤቶች ቀጥተኛ ምላሽም ሆነ መከራከሪያ የሚያቀርቡበት እንዲሆን ታስቦ እንደሆነ ተገምቷል።

ለያንዳንዱ ዘርፍና ተቋማት ከሚመከታቸው ክፍሎች፣ ከመንግስት ቀጥታ ድጎማና እርዳታ የአገልግሎት መልሶ ግንባታ ወጪን ሳይጨምር ለትግራይ ክልል ከ37 ቢሊዮን በላይ መሰጠቱን መንግስት ዘርዝሮ ይፋ ካደረገ በሁዋላ ” ይህ ሁሉ ብር የት ገባ?” በሚል በርካቶች ጥያቄ መሰንዘራቸው ይታወሳል።

በዝርዝር ለቀረበው 37 ቢሊዮን ብር ጉዳይ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ለመንግስት ምላሽ ባወጣው መግለጫ ያለው ነገር የለም።

ከአማራ ክልል ጋር ያለውን የይዞታ ክርክር ጉዳይ “በህዝብ ድምጽ ውሳኔ ይፈታል” በሚል የቀረበውን አንድ ጉዳይ ነጥሎ በማውጣት “የፕሮቶሪያ ስምምነት ተጥሷል” በሚል የተቃውሞና ” በትግራይም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው የሰላም ማስፈን ተግባር አልሳተፍም” የሚል ማስፈራሪያ አዘል መግለርጫ ነበር ያወጣው።

ይህ በሆነ ቀናት ውስጥ ለግምገማ አዲስ አበባ የገባው የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ለግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ መቅመጡ በርካቶችን አስገርሟል። ዜናውን ተከትሎም ” እዛና እዚህ ሆኖ መግለጫ እያተለዋወጡ በምስኪኖች ስቃይ ፖለቲካ ከመቆመር ተቀራርቦ መወያየት የተሻለ ነው” በሚል አስተያየት የሰጡ ጥቂት አይደሉም።

በአንዳንድ የትህነግ ደጋፊ ልሳኖችና ማህበራዊ አውዶች ” በቅርቡ ውጊያ እንጠብቃለን” የሚሉ ድምጾች ሲሰሙ ሰንብተዋል። ይሁን እንጂ እነደተናፈሰው ሳይሆን ሁለቱም አካላት ለንግግር መቀመጣቸው የጦርነት ስጋት ለገባቸው መልካም ዜና ሆኗል።

እነ ዶክተር ደብረጽዮን በአዲስ አበባ ቆይታቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጽህፈት ቤት ፣ አብርሆትን፣ የሳይንስ ማዕከልን፣ የአንድነት መናፈሻንና የመሳሰሉትን ፕሮጀክቶች እንደሚጎበኙ፣ አደዋ ሙዚየም ምርቃት ላይም እንደሚያደሙ ግምት አለ።

Exit mobile version