ቴድሮስ ስልጣናቸውን በመጠቀም የሕወሓትን አላማ ማስፈጸማቸውን እንዲያቆሙ ተጠየቀ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን በመጠቀም የሕወሓትን አላማ ለማስፈጸም የሚያከናውኑትን ተግባር እንዲያቆሙ ዘጠኝ ተቋማት ለዳይሬክተሩ በጋራ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ጠየቁ። ደብዳቤውን የጻፉት የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር፣ ’አሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ’(ኤፓክ)፣ ’ኢትዮጵያን ዳያስፖራ ሃይ ሌቭል አድቫይዘሪ ካውንስል ኦን ኮቪድ-19’፣ ’ኢትዮጵያን ስኮላርስ ኢን ኖርዲክ ካንትሪስ’፣ የደቡብ አፍሪካ የሕክምና ማህበር፣ […]

Continue Reading

የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ጥብቅ ገደብ ጣለ

የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ከግንቦት 7—8 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው 5ኛ ዙር 18ኛ መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ 1ኛ/ በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ጥይት ያለ አግባብ መተኮስ የተከለከለ ነው። 2ኛ/ ጥይት የተኮሰዉን ሰዉ መደበቅ አይቻልም። 3ኛ/ […]

Continue Reading

የ18 ዓመቱ ጎረምሳ በኒውዮርክ የገበያ አዳራሽ በጥይት እሩምታ አስር ሰው አጠፋ

በኒውዮርክ የመገበያያ አዳራሽ በተከፈተ ተኩስ የአስር ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ጥቃቱ ዘርን መሰረት ያደረገ የጥላቻ ወንጀልም ነው በሚል ፖሊስ ምርመራ ከፍቷል። ጥቃቱን ፈጽሟል የተባለ የ18 አመት ወጣት በቡፋሎ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል። ፖሊስ የግለሰቡን ማንነት ይፋ አላደረገም። ተጠርጣሪው ቅዳሜ ከሰአት በኋላ በተጨናነቀ የመገበያያ አዳራሽ ከገባ በኋላ ነው ተኩስ የከፈተው። ጥቃቱን በበይነ መረብ በቀጥታ ለማስተላለፍም ካሜራ […]

Continue Reading

ሕንድ ስንዴ ወደ ውጪ መላክ አቆመች

ሕንድ በዩክሬን ጦርነት እና ከፍተኛ የሙቀት መጠን ባሳደረው ጫና ሳቢያ ስንዴ ለዓለም ገበያ ማቅረብ አቆመች። ውሳኔውን የቡድን ሰባት አባል አገራት የግብርና ሚኒስትሮች አጥብቀው ኮንነዋል።የሕንድ የውጭ ንግድ መሥሪያ ቤት ትላንት አርብ መንግሥት በሚያስተዳድረው ጋዜጣ ባወጣው መግለጫ ዓለም አቀፍ የዋጋ ግሽበት የሕንድ፣ የጎረቤቶቿን እና ተጋላጭ አገራትን የምግብ ዋስትና ደሕንነት እየተፈታተነ እንደሚገኝ አትቷል። መሥሪያ ቤቱ የሕንድ ፈቃድ ያልተሰጠው […]

Continue Reading

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

በየጊዜው እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ሰለባ ላለመሆን ዜጎች ማንነታቸው ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር በበይነመረብ በሚደረጉት ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንዲወስዱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ- ኃይል አሳሰበ። ግብረ-ኃይሉ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች በይዘትም ሆነ በአፈጻጸም ስልታቸው ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ባሻገር በርካታ […]

Continue Reading

የሶማሊያ ምርጫ ፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በአፍሪቃ

ከአንድ ዓመት በላይ ሲጠበቅ የነበረው የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ይካሄዳል።በነገው ምርጫ አሸንፎ ስልጣን የሚይዘው ፕሬዝዳንት የሰርጎ ገቦች ጥቃትና ረሀብ ያስከትላል ተብሎ የሚያሰጋውን ድርቅ ጨምሮ በርካታ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል። በበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት በድህነትና በኮሮና ሰበብ ህጻናት በግዳጅ ለጉልበት ስራ መዳረጋቸው ከቀድሞው ብሷል።የሶማሊያ የሕግ መምሪያና የሕግ መወሰኛ ምክርቤቶች ከ15 ወራት በላይ የዘገየውን የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ያካሂዳሉ። ጎሳን […]

Continue Reading

አቢሲኒያ ባንክ 60 ወለል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ሊያስገነባ ነው

– ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ይሆናል አቢሲኒያ ባንክ 60 ወለል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ሊያስገነባ ነው አቢሲንያ ባንክ በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚያስገነባው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ ግንባታ ጨረታውን ካሸነፈው ቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ጋር የግንባታ ውል ስምምነት ፊርማ ዛሬ ግንቦት 04 ቀን 2014 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በደማቅ ስነ-ስርዓት አከናዉኗል፡፡ የአቢሲኒያ ባንክ የወደ ፊት ዋና መ/ቤት […]

Continue Reading

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተሳሳተ መረጃ ስሜ ጠፍቷል ሲል ማብራሪያ እንዲሰጠው ቢቢሲን ጠየቀ

በመማር ማስተማር፣ ማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና በጥናትና ምርምር አንጋፋ ከሚባሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ ነው-ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፡፡ ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎንም በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ላበረከተው አስተዋጽኦ “የሰላም ዩኒቨርሲቲ” በሚል መጠሪያ ይታወቃል፡፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1/2014 ዓ.ም ተቀማጭነቱን ኬኒያ ናይሮቢ ላደረገው ብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ቢቢሲ) በጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ቢቢሲ በተዛባ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ዝና እና መልካም […]

Continue Reading

«የትግራይ ሕዝብ ያተረፈው መከራና ስቃይ ነው»

“አሸባሪው ህወሓት የሚፈፅምብንን ግፍ ከቀዬአችን አፈናቅሎናል” – የትግራይ ክልል ነዋሪዎች አሸባሪው ህወሓት የሚፈፅምብን ግፍና መከራ ከቀዬአችን አፈናቅሎናል ሲሉ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል በሃይቅ ጃሬ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን የአማራ ክልል ሕዝብ በሚችለው ሁሉ ወገናዊ ድጋፍ እያደረገላቸው መኾኑን ገተናግረዋል። “ከቀዬአችን ተፈናቅለን ወደ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መጥተናል፣ ሕዝቡም ተቀብሎ እያስተናገደን ነው” […]

Continue Reading

ከሶማሊ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ የአቋም መግለጫ

የሶማሊ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀገራችን እና በክልላችን ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታዩ እና እያቆጠቆጡ ያሉ አካሄዶችን በአፅንኦት ሲመለከት ቆይቷል። በተለይም ፅንፈኛ በሆኑ አካላት በሃይማኖት ሽፋን ከውጭ ሃይሎች ጋር በመስራት አብሮ ተዋልዶና ተጋብቶ በኖረ ህዝብ መካከል መከፋፈልን እና ብጥብጥን ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ እኩይ ተግባራትን የክልላችን መንግስት እና ህዝብ አጥብቆ የሚኮንነው እና የሚያወግዘው ተግባር ነው። […]

Continue Reading

በድሬዳዋ ከተማ በነበረው ሁከት ተሳታፊ የነበሩ 89 ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በእለቱ የነበረውን ሁከት አስመልክቶ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ እና የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምርያ የህዝብ ግንኙነትና የለውጥ ስራዎች ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ በጋራ በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በሰጡት መግለጫ÷ በክርስትና እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው የረመዳንና የዐብይ ፆም ፍፁም ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም አብሮነት የታየበት መሆኑን አመላክተዋል፡፡ በተጨማሪም ሙስሊሙ ለክርስቲያኑ ከቤተክርስትያን […]

Continue Reading

በሃይማኖትን ሽፋን የሚፈጸሙ የወንጀል ተግባራትን መንግሥት እንዲያስቆም የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወራቤ ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና በፕሮቴስታንት አማኞች ቤተ አምልኮዎች ላይ የተፈፀውን ጥቃት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና በፕሮቴስታንት አማኞች ቤተ አምልኮዎች ላይ የተፈፀውን ሕገ ወጥና […]

Continue Reading

“ሕገወጦች በድንጋይ ከሰል አመላላሽ አሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው”

ሕገወጦች በድንጋይ ከሰል አመላላሽ አሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሱ በመሆኑ በሲሚንቶ ምርት አቅርቦት ላይ ስጋት መደቀኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች አስታወቁ።  አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ምርቱን ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ማቅረብ እንቸገራለን ሲሉ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል። ከድንጋይ ከሰል ምርት ወደሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚያመላልሱ አሽከርካሪዎች በህገወጦች ምክንያት ዘረፋና የግድያ ሙከራ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል። በተለይ በቤኒሻንጉል […]

Continue Reading

“የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን”

ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ክስተት አስመልክቶ እንዳሉት፤ የክልሉ መንግሥት ተገቢውን ክትትል አድርጎ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል። እንደ ሀገር ከገጠሙን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳንላቀቅ ሃይማኖትን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር […]

Continue Reading

“ሃይማኖት የሰላም እንጂ በምንም ምክንያት የግጭት መንስኤ ሊሆን አይችልም”

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ የተከሰተውን ክስተት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ጉባኤው ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ሃይማኖት የሰላም እንጂ በምንም ምክንያት የግጭት መንስኤ ሊሆን አይችልም! ሃይማኖት የሰላም፣ የአብሮነትና የፍቅር መሠረት ናት፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ሃይማኖቶች በሙሉ ፍቅርን፤ ሰላምን፤ አብሮነትን፤ በጋራና በትብብር ማደግን እንዲያስተምሩ ፈጣሪ ኃላፊነት […]

Continue Reading

የምስ.አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ስትራቴጂክ ከፍተኛ የአማካሪዎች መድረክ በአ.አ በመካሄድ ላይ ነው

በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ውይይቱን ያስጀመሩት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር አብርሀም በላይ በምስራቅ አፍሪካ የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን ማበጀት እንደሚገባና ለዚህም የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ስትራቴጂክ ከፍተኛ የአማካሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሀይል የስትራቴጂክ ከፍተኛ የአማካሪዎች ቡድንን እንደ ተቋም ማደራጀቱ ለሰላም ግንባታ ስራው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት […]

Continue Reading

የፑቲን ቀጣይ ዒላማ – ኦዴሳ የወደብ ከተማ

የፖለቲካ 101- ትንተና የማሪፖል ከተማ ነገር ያለቀለት መሆኑን በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ አዞቪስታል ከተባለው የኢንዱስትሪ መንደር ውጭ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በሩሲያ እጅ ገብታለች፡፡ በዚህም ምክንያት በርካቶች የሩሲያ ቀጣይ መዳረሻ የት ይሆን? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ የሩሲያ ማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሩስታም ሚኒንካዬቭ “ሩሲያ በምስራቅ እና ደቡብ ዩክሬይን የሚገኙ ቦታዎች ትቆጣጠራለች” በማለቱ አሁን ዕቅዱ ግልጽ ሆኗል፡፡ በመሆኑም ቀጣዩዋ […]

Continue Reading

በኦሮሚያ ድርቁ ባስከተለው ጉዳት 1.3 ሚሊዮን እንስሳት ሞቱ

አዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ26 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን እንስሳት መሞታቸውን የክልሉ የአደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያና አደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር አቶ ቤኛ ዱሬሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በስምንት ዞኖች በተከሰተው ደርቅ 14 ሚሊዮን የሚሆኑ እንስሳት ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ26 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ አንድ ነጥብ […]

Continue Reading

«አጋር ጅርጅቶች ለትግራይ የሚያቀርቡት የህክምና ቁሳቁስ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ አለባቸው»

– እንደ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያሉ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሃይሎች የሚያሰራጩት መረጃ መሰረት ቢስ ነው፣ ለትግራይ ክልል የህክምና ቁሳቁስ እያቀረቡ ያሉ አጋሮች የሚያቀርቡት ቁሳቁስ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ እንዳለባቸው የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ገለጹ። ኮሚሽነሩ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአጋሮች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል። አጋሮቹ […]

Continue Reading

አፓርታማዎችን በሳምንት የሚያጠናቅቅ የፈጠራ ውጤት ይዞ በፋይናንስ የሚፈተነው ወጣት

ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ 60 በመቶ ያህሉን ዋና ዋና የግንባታ ዕቃዎቿን ከውጭ አገራት ነው የምታስገባው። ለዚህም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪ ታደርጋለች። ይህን የውጭ ምንዛሪ ለማደን በአገር ልጆች የሚሠሩ የፈጠራ ውጤቶችን ከመጠቀም ይልቅ ከውጭ የሚመጡ ግብዓቶችን መጠቀም የተለመደ ተግባር ሁኗል።  በዚህ ምክንያትም የአገር ውስጥ የፈጠራ ባለቤቶችን ደግፎ ለቁም ነገርና ለውጤት ማብቃት አልተለመደም። ወንድማገኝ ገለታ ከእነዚያ የፈጠራ ባለቤቶች […]

Continue Reading

አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች የቅጥፈት ሪፖርት ማውጣታቸውን በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች እይጋለጡ ነው

“አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች በወልቃይት ዙሪያ ያወጡት የጋራ ሪፖርት ፍጹም ሐሰት መሆኑን በቦታው ላይ ተገኝቼ ለማየት ችያለሁ ስትል” በቨርጂኒያ ግዛት የምትኖረው የፑሽ ስታርት ሚዲያ ጋዜጠኛ ቤቲ ተከስተ ከአሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን እንዲሁም አሜሪካዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ጀማል ካውንተስ ጋር በመሆን ምስክርነቷን ሰጠች። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ቤቲ ተከስተ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የተገኙትን የጅምላ መቃብሮች መመልከቷንና አሁንም […]

Continue Reading

«ግብፅንና ሱዳን የሚጎዱበት ምክኒያት የለም» ሃምዛ ናስር

ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን ስትገነባ ራሷን ከመጥቀም ባለፈ የሌሎችንም ጥቅም ታሳቢ አድርጋ እንጅ እንደሚባለው ግብፅንና ሱዳንን ለመጉዳት አደለም ። የመካከለኛው ምስራቅ የውሃ ፎረም ፕሬዝዳንት የሆኑት ሃምዛ ናስር አልጀዚራ ላይ በነበራቸው ኢንተርቪው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ ነው። እንደ ሃምዛ አስተያየት ከሆነ ኢትዮጵያ ከግድቡ ሀይል ማመንጨት በመጀመሯ የግብፅና የሱዳን ወንድሞቻችን የውሃ ደህንነታችንን ይጎዳል የሚለው ክስ መሰረት ቢስ […]

Continue Reading

ትህነግ ያሰማራቸው 247 የጉህዴን ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 247 የጉህዴን ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ። የወረዳውን የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የፀጥታ አካላት ያላሰለሰ ጥረት እያረጉ እንደሚገኙ የገለፁት፣ የወረዳው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሻለቃ ደምስ ዳኘ እነዚህ የጥፋት ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ከቀረበላቸው የሠላም ጥሪ በተጨማሪ፤ በአካባበቢው ህግን ለማስከበር እየተወሰደ […]

Continue Reading

ለባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የተዘረጋ የኤሌክትሪክ ሽቦ የሰረቁ በጽኑ እስራት ተቀጡ

ለባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የተዘረጋ የኤሌክትሪክ ሽቦ ቆርጠው የሰረቁ ሁለት ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ ለአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የተዘረጋ የኤሌክትሪክ ሽቦ ቆርጠው የሰረቁ ሁለት ተከሳሾች በጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ተከሳሽ ፀጋዬ ቴዎድሮስ እና ያብስራ ተስፋዬ በ1996 ዓ.ም የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)ሀ እና የቴሌኮሙኒኬሽንና የኤሌክትሪክ ሀይል መሰረተ ልማት አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ የወጣውን […]

Continue Reading

በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው አጣሪ ኮሚቴ በፈተና አስተራረም ዙሪያ የደረሰበትን ሂደት ይፋ አደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴርና የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጄንሲ የ12ኛ ከፍል ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ውጤት ማስታወቃቸው ይታወሳል። የመግቢያ ፈተናው ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ በተማሪዎች፣ በመምህራን፣ በወላጆች እና በተቋማት ጭምር ቅሬታ ፈጥሯል። የፈተና ውጤቱ የአስተራረም ስህተት አለበት፣ በጦርነቱ ውስጥ የነበሩ አካባቢዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች ተነስተውበታል። አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በአማራ ክልል ወረራ ፈፅሞ ቆይቷል፣ […]

Continue Reading

“ጂፒኤስ ያስገጠሙ የሕዝብ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ይደረግላቸዋል”

ከ12 ሰዎች በላይ የመጫን አቅም ያላቸውና ጂፒኤስ ያስገጠሙ የሕዝብ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ባወጡባቸው አካባቢ በሚመጣው የመረጃ ቋት (ዳታ ቤዝ) መሠረት የነዳጅ ድጎማው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። የነዳጅ ድጎማውን ለማግኘት እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ጂፒኤስ ማስገጠም እንደሚኖርበት ተጠቁሟል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት […]

Continue Reading

በኒው ዮርክ የባቡር ጣቢያ በደረሰ ጥቃት በርካታ ሰዎች ቆሰሉ

ብሩክሊን ሰንሴት ፓርክ በሚባለው የከተማዋ ቀበሌ የሠላሳ ስድስተኛው መንገድ የምድር ለምድር ባቡር ጣቢያ ውስጥ ጥቃቱ የደረሰው ጠዋት እንቅስቃሴ በሚበዛበት ሰዓት ላይ መሆኑን የከተማዋ ባለሥልጣናት ገልጸዋል። ሰንሴት ፓርክ በሚባለው የሰራተኛ ሰፈር በሚገኘው የባቡር ጣቢያ በደረስው ጥቃት አስራ ስድስት ሰዎች የተጎዱ ሲሆን አስሩ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል። ከመካከላቸው አምስቱ በከባዱ የተጎዱ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቁዋል። ጥቃቱን ያደረሰው […]

Continue Reading

ከሰሜን ሸዋ ዞን የህዝብ ሰላምና ደህንነት መምሪያ የተላለፈ መልዕክት

በትላንትናው እለት ማለትም በቀን 3/08/2014 ከሰአት በኋላ በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ አቅራቢያና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አዋሳኝ ወሰን ቁርቁር በተባለ አካባቢ በነበረ የግለሰቦች ግጭት ተከስቶ የነበረ የፀጥታ ችግር በሸዋሮቢት ከተማ ፣ በቀወት ወረዳ፣ በጅሌ ጥሙጋ አመራሮች ፣ በሀይማኖት አባቶች ፣በአካባቢው ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር ውሏል ሲሉ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ አሳውቀዋል። […]

Continue Reading

በጂንካና አካባቢው በተፈጠረ የፀጥታ ችግር 133 ተጠርጣሪዎች ተያዙ፤ ፖሊሶችና የመንግስት ኃላፊዎች አሉበት

ከሰሞኑ በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 133 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል 4 የፖሊስ አባላት ይገኙበታል ብለዋል። በመንግሥት መዋቅር ስር ያሉ የአመራር አካላት፣ ራሳቸውን የሕዝብ ወኪል አድርገው በማኅበራዊ […]

Continue Reading

ሮማን አብራሞቪች፡ ከማደጎ እስከ ቢሊየነርነት

ገና በሦስት ዓመቱ ወላጆቹን በሞት የተነጠቀው ዛሬ ላይ ከዓለማችን እጅግ ከናጠጡ ባለጸጎች መካከል ተጠቃሹ ነው፤ ሮማን አብራሞቪች። ሮማን አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያለው የጠበቀ ግንኙነት የገነባውን ገናና ስምና ንግድ እያሳጣው ይገኛል። ”እርግጠኛ ሰዎች ለሦስት ወይም አራት ቀናት እኔ ላይ ትኩረት ያደርጉ እና ከዛ ያልፋል። እኔ ላይ ትኩረት አያደርጉም። ማን እንደሆንኩኝ ቶሎ ይረሳሉ። እኔ […]

Continue Reading

በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተያዘ

በሰሜን ጎንደር ዞን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የዞኑ አስተዳደር ሕገ-ወጥ የንግድ ሥርዓትን ለመከላከል ለአንድ ወር ያክል በሠራው የቁጥጥር ሥራ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኢንዱስትሪ ውጤቶች እና የግብርና ምርቶች መያዛቸውን የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዝናቸው ንጉሤ ገልጸዋል። ምርቶቹ የተያዙት የዞኑ አስተዳደር ጥምር ኃይል አቋቁሞ በአንድ […]

Continue Reading

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች እንዲዘጉ ታዘዙ

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች በሙሉ እንዲዘጉ ታዘዙ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ቢዝነስ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች በሙሉ እንዲዘጉ ታዘዙ ትዕዛዙን ያልፈጸመ መሥሪያ ቤት በጀት አይለቀቅለትም። የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ የግል ባንኮች የከፈቷቸውን ሒሳቦች በአስቸኳይ እንዲዘጉ፣ ይህንንም ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር በግል […]

Continue Reading

የሩስያ ኃይሎች በምስራቅ ዩክሬን በኩል የማጥቃት ዘመቻቸውን ማፋፋማቸው ተነገረ

የሩስያ ኃይሎች በምሥራቃዊ ዩክሬን በኩል የሚያደርጉትን የማጥቃት ዘመቻ እንደገና አጠናክረው መቀጠላቸው ተነገረ። ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ የዘለቀውና 46ኛ ቀኑን የያዘው የሩስያ እና የዩክሬን ጦርነት በዛሬው ዕለት በዩክሬን ምሥራቃዊ ግዛት በኩል እየተፋፋመ መምጣቱ እየተዘገበ ነው። ዩክሬን በምሥራቃዊ ግዛቶቿ በኩል ከሩስያ ኃይሎች የሚሰነዘርባትን ጥቃት ለመመከት ኃይሏን እያሰባሰበችና በአካባቢው የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎችን ከስፍራው የማስወጣት እንቅስቀሴዋን መቀጠሏን የተለያየዩ መገናኛ ብዙሃን […]

Continue Reading

የሚኒስትሮች ግብረኃይል በአፋርና በአማራ ክልል ለተሰማራው የምርመራ ቡድን የተጠናከረ ድጋፍ እያደረገ ነው

የሚኒስትሮች ግብረኃይል ጽ/ቤት በአፋር እና በአማራ ክልል ለተሰማራው የምርመራ ቡድን የተጠናከረ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ በሚኒስትሮች ግብረኃይል ጽ/ቤት ስር ከተቋቋሙ 4 ኮሚቴዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የወንጀል ምርመራ እና ማስቀጣት ኮሚቴ በአፋር እና በአማራ ክልል ለተሰማራው የምርመራ ቡድን የተጠናከረ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ካሳ ገለጹ፡፡ ቡድኑን ለማጠናከር እየተሰሩ ካሉ ስራዎች ጋር በተያያዘ […]

Continue Reading

ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግላጫ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መጋቢት 20 ቀን 2014 በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ቆርኬ/አውራ ጎዳና በሚባለው ልዩ ሥፍራ በምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች በጉዞ ላይ በነበሩት የህዝብ ሚሊሻና የፌዴራል ፖሊስ ላይ ባደረሱት ዘግናኝ ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፤ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ዘመዶቻቸው በሙሉ መጽጽናናትን ይመኛል፡፡ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጠናከርና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ በምንገኝበት […]

Continue Reading

የኦነግ ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ ውሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ ውሳኔ ሰጥቷል። ቦርዱ ፓርቲውን አሰመልክቶ የተሰጠው ውሳኔው እንደሚከተለው ቀርቧል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ ውሳኔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራር መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ ከፓርቲው አመራሮች ሲቀርቡለት የነበሩትን ክርክሮች በመመርመር ውሣኔ […]

Continue Reading