“ፊቤላ ኢንዱስትሪ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር የሚጠጋ ዘይት ለገበያ አቅርቧል”

አቶ በላይነህ ክንዴየፊቤላ ኢንዱስትሪ ባለቤትና የቢኬጂ የቦርድ ሰብሳቢ ፊቤላ ኢንዱስትሪ በመጀመሪያው ዙር የውጭ ምንዛሪ ተመድቦለት ባስገባው ጥሬ እቃ ተጠቅሞ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር የሚጠጋ ዘይት እና 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ተጓዳኝ ምርቶችን አምርቶ ለገበያ ማቅረቡን የፊቤላ ኢንዱስትሪ ባለቤትና የቢኬጂ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይነህ ክንዴ አስታወቁ። ስምንት ሚሊየን […]

የኦሮሚያ ክልል 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አስታወቀ ። ምርጫው ህዝቡ በነፃነት ድምፁን የሚያሰጥበት በመሆኑ ከቀደሙት ምርጫዎች ልዩ እንደሚያደርገው ገለጸ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞኪራሲያዊነቱን ለማረጋገጥ ከላይ እስከ ታች […]

ሸገር ዳቦ – በሰዓቱ ማድረስ የሚችልበት አቅም እንደሌለው አስታወቀ

– ዳቦ በሰዓቱ ባለመድረሱ በሥራቸው ላይ ጫና እንደፈጠረባቸው በሸገር ዳቦ አከፋፋይነት የተደራጁ ወጣቶች አመለከቱ– ያሉት ተሽከርካሪዎች ውስን በመሆናቸው ዳቦውን በሰዓቱ ማድረስ እንዳልቻለ ሸገር ዳቦ አስታውቋል ዳቦ በሰዓቱ ባለመድረሱ በሥራቸው ላይ ጫና እያደረሰባቸው እንደሆነ በሸገር ዳቦ አከፋፋይነት የተደራጁ ወጣቶች አመለከቱ ። ያሉት ተሽከርካሪዎች ውስን በመሆናቸው ለ384 ሱቆች በሰዓቱ ማድረስ […]

“ ብጥብጥና ሁከት ድህነት ውስጥ አስገብቶናል”

‹‹ሀብት ለማፍራት ብቻ ሳይሆን ያለውንም ለመጠበቅና ህይወትን ለመታደግ የሰላም መኖር ወሳኝ ነው›› አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የጸጥታ መደፍረስ ክስረት በመሆኑ ሀብት ለማምጣት ብቻ ሳይሆን ያለውንም ለማስጠበቅና ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት ለመታደግ የሰላም መኖር ወሳኝ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ። በክልሉ […]

The crocodile’s tears!

By Nigussie Meshesha (PhD) Why Egypt becomes as such over selfish and a complete lier in the bid to use the Nile alone? Why does it want to mislead the world with unlived truth? One, however, ought not to be destructed by the false allegations of Egypt on […]

አዲሱ ሲዳማ – በኤዶ ቀበሌ የሚኖሩ የጉጂ ማህበረሰብ አባላት “በኦሮሚያ ክልል ስር መተዳደር እንፈልጋለን”

አዲሱ የሲዳማ ክልል በያዝነው በመጋቢት ወር ብቻ በሶስት ቦታዎች ላይ ከወሰን ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ችግሮች ገጥመውታል። ሁለቱ ጉዳዮች የተያያዙት በኦሮሚያ ክልል ከሚገኘው ምዕራብ አርሲ ዞን ሲሆን አንዱ ደግሞ በደቡብ ክልል ከሚገኘው የወላይታ ዞን ጋር ነው። ከሁነቶቹ ሁሉ ከበድ ያለውና በጊዜ ረገድም ቀረብ ያለው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 24፤ […]

በድርጅት ስም ዕጣ ደርሶታል በሚል ከሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ፖሊስ አሳስበ

በኮካ ኮላ ድርጅት ስም የ200 ሺህ ዶላር ተሸላሚ በመሆንዎ እንኳን ደስ አለዎት” በሚል የማጭበርበር ስራ እየተሰራ በመሆኑን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ መድረግ እንዳለበት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ አሳስበዋል፡፡ ድርጅቱ ለምርጥ ደንበኞቹ የሽልማት ፕሮግራም አዘጋጅቶ የነበረ እና ከተመረጡ ደንበኞች አንዱ እርስዎ ኖት በሚል ለተለያዩ ጉዳዮች ማስፈፀሚያ የሚሆን 640 ሺህ የኢትዮጵያ […]

በትግራይ ክልል ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለማሻሻል ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ

በትግራይ ክልል ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ለማሻሻል ህብረተሰቡን መሰረት ያደረጉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ጊዜያዊ አስተዳደሩ በክልሉ ባለፉት ሶስት ወራት በክልሉ በተከናወኑት የፀጥታ ስራዎችን ዙሪያ ላለፉት ሁለት ቀናት ሲገመግም ቆይቷል። የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር ግርማይ ካህሳይ እንደገለጹት የፀጥታ ስራዎችን ለማሻሻል […]

“የመተከል ዞን ግብረሃይል እስካሁን ውጤታማ ተግባራትን ቢያከናውንም አሁንም ቀሪ ስራዎች ይጠበቁበታል”

በመተከል ዞን የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረሃይል እስካሁን ውጤታማ ተግባራትን ቢያከናውንም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቀሪ ስራዎች እንደሚጠበቁበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚኒሰትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል የመንግስት የስራ ሃለፊዎችን […]

“አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ የሚያወድም ጊዜው ያለፈበት የኬሚካል ክምችት አለ” በሚል የተሰራጨው መረጃ የተዛባና የተሳሳተ መሆኑን ብሄራዊ ደህንነት አሳሰበ

“አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ የሚያወድም ጊዜው ያለፈበት የኬሚካል ክምችት አለ” በሚል የተሰራጨው መረጃ የተዛባና የተሳሳተ መሆኑን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሳሰበ አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ የሚያወድም ጊዜው ያለፈበት የኬሚካል ክምችት አለ በሚል በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ የትስስር ገፆች የተሰራጨው መረጃ የተዛባና የተሳሳተ በመሆኑ፤ ህብረተሰቡ የዕለተ ተዕለት እንቅስቃሴውን ያለስጋት […]

የአዳም የማምረቻ መሳሪያዎች ፋብሪካ 1.9 ቢሊዮን ብር በትኖ መሰብሰብ አልቻለም

የአዳማ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ ያጋጠሙትን ችግሮች በፍጥነት ፈትቶ አርሶ-አደሩ የቴክኖሎጅ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ። የአርሶ-አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ችግሩን መፍታት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ ማምረቻ ኢንዱስትሪው ለሰባት አመታት በዱቤ ሸጦ ያልሰበሰበው ገንዘብ ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር […]

የተከዜ የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች ምንም ዓይነት ጥገና ሳይፈልጉ ወደሥራ መግባታቸው ተገለጸ

የተከዜ ኃይል ማመንጫ ሁለቱ ዩኒቶች ምንም ዓይነት ጥገና ሳይፈልጉ ወደ ሥራ መግባታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን አስታወቁ። ከዚህ በፊትም ግድቡ ተመቷል ፣ ከዚህ በኋላ አገልግሎት አይሰጥም ሲባል የነበረው ሐሰት መሆኑንም አመለከቱ። አቶ ሞገስ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስ ታወቁት፣ የተከዜ ኃይል ማመንጫ ከዚህ ቀደም ኃይል […]