በፌዴራል የጋራ ገቢዎች ቀመር መሠረት ባለፉት 11 ወራት ከ20.7 ቢሊዮን ብር በላይ የክልሎች ድርሻ መሆኑን በመለየት ማስተላለፍ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገለጹ።
ይህ የበጀት ክፍፍል ከአለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ 11 ወራት አንፃር ሲታይ የ16.6 ቢሊዮን ብር ወይም 400.14% ዕድገት አለው።ይህ ገንዘብ የክልሎችን የልማት ወጭ በመሸፈን ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገልጸዋል።
ለክልሎች የተላለፈው የገቢው ምንጭ ከኤክሳይዝ፣ ከተርን ኦቨር፣ ከተጨማሪ እሴት እና ከንግድ ስራ ገቢ ግብር ታክሶች ብቻ የተሰበሰበ ነው ተብሏል።የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፌዴሬሽን ም/ቤት መሻሻል በመቻሉ፣ የተቋሙ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ በመምጣቱ እና ተቋሙ በተቀመጠው የማከፋፈያ ቀመር መሰረት ክፍፍሉን በአግባቡና በትክክል መስራት በመቻሉ የጋራ ገቢው ድርሻ ማደጉ ተገልጿል።
ክፍፍሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ታላቁና ፍትሃዊ ነው የተባለ መሆኑንን ለማሳየት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገላጭ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል። በሰንጠረዥ አስደግፎ የቀረበው ማስረጃ ሃሜታንና የጎንዮሽ ወሬዎችን ያስቀራል ተብሏል።
- በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉበትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በትህነግ መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም… Read more: በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉ
- የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉበተመረጡ ቦታዎች፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን ፋኖ አስታወቀ። ይህን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአባይ ድልድይን… Read more: የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉ
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ