የአማራ ክልል ርዕሰ ብሄር አገኘሁ ተሻገር ለክልሉ ዓቅሙ የደረሰና ብቁ የሆኑ ወጣቶች የክተት ጥሪ አስተላለፉ። የሽብር ቡድኑ ቃል አቀባይ “ከአማራ ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለ” በሚል በገሃድ ከተናገሩ በሁዋላ ክልሉ ያስተላለፈው ይህ ጥሪ ከዳር እስከዳር ንቅናቄ ፈጥሯል።
“በክልሉ ውስጥ የማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሣሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ ከነገ ጀምሮ ለህልውና ዘመቻ እንዲዘምት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የክተት ጥሪ አስተላለፉ” ሲል ነው የክልሉ ሚዲያ ይፋ ያደረገው።
አሜሪካ በኢትዮጵያ መፍንቅለ መንግስት አካሂዳ ትህነግን በመሪነት ለማስቀመጥ እላይ ታች በምትልበት ወቅት የአማራ ክልል ” ለህልውና ዘመቻ ክተት” ማለቱ ስጋት ፈጥሯል።
የትህነግን ምርጫ በብቸኝነት የታዘቡት የኖርዌይ ተወላጅ ፕሮፌሰር ሼትል የአማራ ክልል ይህን ዜና ይፋ ባደረገ ደቂቃዎች ውስጥ በቲውተራቸው አማራ መሳሪያ ያለው ሁሉ ከነገ ጀምሮ ወደ ጦር ግንባር እንዲዘመት መተራቱን ጠቅሰው፤ የሲቪል ጦርነት እንደሚቀሰቀስ ጠቁመዋል። የአቶ አገኘሁ ተሻገርን ምስልና ጥሪ አትመው ለነጮቹ ባሰራጩት መልዕክት ማሳረጊያ እንደተለመደው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ወቅሰዋል።
ዜናው እንደተሰማ በቀጥታ የተላከላቸው የውጩ ማህበረሰብ እንዲያሰራጩ ሲሆን ሰውየው ከቀናት በፊት መንግስት እንደሚገለበጥ የሚያትት ጽሁፍ በማጋራት ” አዳዲስ ተተኪዎቹ ይዘጋጁ” የሚል ሃሳብ አሰራጭተው ነበር።
አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው አገሪቱ ሕዝብ ለመንግስት ድጋፍ እየሰጠ ባለበት፣ ትህነግን እንደማይፈልግ እያወገዘ ድምጹን በሚያሰማበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ለመጫን ያሰበችው ሃይል ተቀባይነት እንደማይኖረው፣ ክልሎች ጭራሹኑ ጆሮ እነደማይሰጡት አለመረዳቷ አስገራሚ እንደሆነ ተመልክቷል።
የአማራ ክልል ራሱን በነባር የጦር መኮንኖች ካደራጀ በሁዋላ ለህልውና ዘመቻው እንደሚነሳ ብ/ጄነራል ተፈራ መናገራቸው አይዘነጋም። አዲሱ የልዩ ሃይል አዛዥ እንዳሉት ዘመቻው ስር ነቀለና ትህነግን ለመቸረሻ ጊዜ የሚነቅል ነው።
ትህነግ በትግራይ የሰለጠኑ 250 ሺህ ወታደሮችና አንድ ሚሊዮን በላይ ሚሊሻና ለክተት የተዘጋጀ ሃይል፣ እንዲሁም እጅግ በርካታ ሕጻናትን መልምሎ ውጊያ ላይ ቢያሰልፍም አሜሪካን ጨምሮ ኢትዮጵያ ላይ ውርጅብኝ የሚያወርዱት አገራት ምንም ያሉት ነገር የለም። ይህን በማስረጃ የተደገፈ ጉዳይ በዝምታ ያለፉት አገራቱ የአማራ ህዝብ “ለህልውና” በሚል የጠራውን ክተት ተከትሎ የተለያየ መግለጫና የውግዘት ማሳሰቢያ እንደሚያወጡ ይጠበቃል።
አብዛኞች የሰላም አማራጭ እንዲፈለግ እየወተወቱ ቢሆንም ታላላቁ አገራት መንግስት ለመገልበጥ ከትህነግ ጎን መሰለፋቸው ችግሩን አሳዛኝና ውስብሰብ እንዳደረገው እየተገለጸ ነው።
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support Forces (RSF), the… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in support of… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF