ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ ቁ.6
ታኅሣሥ 14 ቀን 2014 ዓም
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡ በግምገማውም በግንባር ለተገኘው ድል የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣ ሞያቸውንና ገንዘባቸውን ለሀገራቸው ሳይሰስቱ በመስጠት የፈጸሙት የደጀንነት ገድል አኩሪ መሆኑን ተመልክቷል፡፡ ለዚህ የሕዝባችን ከፍተኛ አስተዋጽዖ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ ምስጋና ያቀርባል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ የተገኙ ድሎቻችንን ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን፣ ለዚህም በማኅበረሰቡ፣በአስተዳደር አካላትና በጸጥታ አካላት መወሰድ የሚገባቸውን ተግባራት በመለየት የሚከተሉትን ትእዛዛት ሰጥቷል፡፡
- ከሕዝብ ችግር ለመጠቀም የሚፈልጉ አንዳንድ አካላት፣ ወደ ሀገር ቤት የሚመጣውን የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ምክንያት አድርገው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መነሣሣታቸው ተደርሶበታል፡፡ ይህ ደግሞ ድኻውን የኀብረተሰብ ክፍል ስለሚጎዳ በእነዚህ ሕገ ወጥ አካላት ላይ መንግሥት አስፈላጊውን ቁጥጥርና ሕግ የማስከበር ተግባር እያከናወነ ነው፡፡ በመሆኑም በየአካባቢው በመሠረታዊ ፍጆታዎችና አገልግሎቶች ላይ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና ያለ አግባብ በሚያከማቹ አካላት ላይ፣ የንግድ ቢሮዎችና የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዝዘዋል፡፡
- ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡት አካባቢዎች አስተዳደርን መልሶ የማቋቋምና መሠረታዊ የኅብረተሰብ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ያለው እንቅስቃሴ ወጥ በሆነ ሁኔታ እየተተገበረ አለመሆኑን ገምግሟል፡፡ በዚህም ምክንያት የጸጥታ ችግሮችና የወንጀል ተግባራት ነጻ የወጣውን ማኅበረሰብ እያማረሩት ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ክልል መንግሥት የየአካባቢውን አስተዳደር በአስቸኳይ በብቁ አመራሮች እንዲያደራጅ፤ መደበኛ የፖሊስ ኃይሎችም የተጠናከረ ሥራ እንዲጀምሩ እንዲያደርግ፣ እነዚህን ለማድረግ ባልተቻለባቸው ቦታዎች የሚንቀሳቀስ የመከላከያ ኃይል፣ ነጻ በወጡ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር በሚፈጥሩ አካላት ላይ፣ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድ ታዝዟል፡፡
- አሸባሪው ኃይል ተቆጣጥሯቸው በነበሩ አካባቢዎች፣ ባደራጃቸው ሕገ ወጥ መዋቅሮች አማካኝነት፤ የቀደመው አስተዳደር ይጠቀምባቸው የነበሩትን ማኅተሞች በመጠቀምና አዳዲስ ሕገ ወጥ ማኅተሞችን በመቅረጽ ሕገ ወጥ መታወቂያዎችን መስጠቱ፤ የተለያዩ ሕገ ወጥ ሰነዶችን ማዘጋጀቱ ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም በየአካባቢው የተቋቋሙ የመስተዳድር አካላትና የጸጥታ ኃይሎች አሸባሪው ሕወሐት ያስቀረጻቸውን ማኅተሞች፣ መታወቂያዎችና ሌሎች ሰነዶች እንዲያመክኑ ታዝዘዋል፡፡
- ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውሮችና ጠላት አንጠባጥቧቸው የሄዱ የጦር መሣሪያዎች በመኖራቸው ለሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ አዝማሚያዎች መኖራቸው ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም የየአካባቢው ልዩ ኃይልና ፖሊስ በአስቸኳይ እነዚህ ጉዳዮች ሥርዓት እንዲያሲዙ ታዝዘዋል፡፡ እነዚህ ኃይሎች ባልተጠናከሩባቸው አካባቢዎችም የመከላከያ ኃይል አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ
- በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉበትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በትህነግ መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት… Read more: በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉ
- የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉበተመረጡ ቦታዎች፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን ፋኖ አስታወቀ። ይህን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር… Read more: የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉ
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?More stories ኦሮሚያ- የሕዝብ ተመራጮች ኦነግ ተደራዳሪዎቹን በስም ይፋ እንዲያደርግና ራሱን እንዲገልጥ ጠየቁMarch 21,… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት