ባለፈው አርብ የጸደቀው የውሳኔ ሀሳብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና አባል አገሮች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የበለጠ እንዲተጉ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
‘Countering disinformation and promotion and protection of human rights and fundamental freedoms’ የሚል ርዕስ ያለው ይህ የውሳኔ ሀሳብ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭት በሰብዐዊ መብቶችና መሰረታዊ በሆኑ ነጻነቶች እንዲሁም ዘላቂ በሆኑ የልማት ግቦች (Sustainable Development Goals) ላይ እያስከተለ ያለውን አሉታዊ ሚና አጽኖት ሰጥቷል።
ሀሰተኛ መረጃ ለግጭት፣ ለመድሎ፣ ለሰብዐዊ ቀውሶች መከሰትና ለአለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም የውሳኔ ሀሳቡ እውቅና ሰጥቷል። በተጨማሪም የውሳኔ ሀሳቡ የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በማናቸው የመገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ ጥላቻንና ግጭትን የሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎችን አውግዟል።
የውሳኔ ሀሳቡ አገሮች ለሰላምና ለትብብር ጠንቅ የሆነውን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማይጻረር መልኩ የመዋጋት ሀላፊነት እንዳለባቸውም ያሳሰበ ሲሆን የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የፖሊሲ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የብዙ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ያሰመረ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጽነትን በማስፈንና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚያበረታቱ አሰራሮችን በመቀነስ የራሳቸውን በጎ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርቧል፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመዋጋት ረገድ ቀዳሚ ሚና እንዲጫዎቱም ሀላፊነት ሰጥቷል።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ በፓኪስታን አርቃቂነትና በበርካታ አገሮች ድጋፍ የቀረበ ሲሆን ለወራት ውይይት ሲደረግበት ነበር።
EthiopiaCheck Updates
- በትግራይ የጊዚያዊ አስተዳደሩና የትህነግ አለመግባባት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል – ጎራ የለየ ግጭት?በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በህወሐት መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ… Read more: በትግራይ የጊዚያዊ አስተዳደሩና የትህነግ አለመግባባት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል – ጎራ የለየ ግጭት?
- የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉበተመረጡ ቦታዎች፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን ፋኖ አስታወቀ። ይህን ያስታወቀው… Read more: የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉ
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ