ከለውጡ በሁዋላ ኤርትራ አምባሳደር ሆነው የከረሙት ሬድዋን ሁሴን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ተክተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። በምትካቸው ማን እንደሚሰየም እስካሁን ይፋ አልሆነም።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የተለያዩ ሹመት መስጠታቸውን ተከትሎ ነው አቶ ሬዲዋን አቶ ገዱን መተካታቸው የታወቀው። ይፋ በሆነው የሹመት ዜና ይፋ ባይነገርም ሹመቱ የማያሻማ ትርጉም እንዳለው ታውቋል። አቶ ገዱ የደህንነት አማካሪ ሆነው በፋኖ ስም በሚደራጀው አደረጃጀት ውስጥ እጃቸው እንዳለበት ሲታሙ እንደነበር ይታወሳል።
በኢህአዴግ የምርጫ ዘመቻ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን አንጀት እንዳራሱ የሚነገርላቸው አቶ ሬድዋን እስካሁን በስልጣን መቆየታቸው በበርካቶች ዘንዳ ብልጽግና ከሚወቀስበት ጉዳይ አንዱ ነበር። አቶ ሬድዋን ህዝብ የሚወዳቸውን የተቃዋሚ አመራሮችንና አመለካከትን በማበሻቀጥ የሚታወቁ የቀድሞው ስረዓት ታማኝ እንድነበሩ በርካቶች ሲናገሩ ቆይተዋል። አሁን የተሰጣቸው ስልጣን ረጋ ብለው ስለ ጡርታቸው እንዲያስቡ የሚረዳቸው እንደሆነ ተገምቷል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ዳባ ደበሌ፣ የቀድሞ ኦሮሚያ ሊቀመንበር ሙክታር አይነት ሰዎችን መሸከሙ አሁንም ድረስ ብልጽግናን የሚያስወቅስ ነው።
ዛሬ ይፋ በሆነው ሹመት መሰረት አቶ ሄኖስ ወርቁ የነዳጅና ኢነርጂ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ካሊድ አብዱራሂማን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል፣ አቶ ወንደሙ ሴታ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸው ታውቋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል ዋና ኦዲተርነት መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተርነት ወይዘሮ መሰረት ዳምጤን እንዲሁም አቶ አበራ ደምሴን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተርነት በማድረግ ሹመቱን እንዲያጸድቅላቸው መተየቃቸው ታውቋል።
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በህዝብ ጥቆማ እንደሆነ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ መከራዋን ለመካፈል አይደለም፤ በተቃራኒው እንጀራዋን በልተው… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- “የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እየፈጸሙ ነው” – ትምህርት ቤቶችን ካምፕ አድርገዋልበአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ በላይ ማሻቀቡ ይፋ እየሆነ ባለበት… Read more: “የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እየፈጸሙ ነው” – ትምህርት ቤቶችን ካምፕ አድርገዋል
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለተከላ… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው