የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነት አደረገ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት ማድረጉና መስማማቱ ተገልጿል።
በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የልዑካን ቡድን ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት የልዑካን ቡድን ጋር በነበራው ቆይታ በቀጣናዊ፣ ዓለም አቀፋዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝርና በጥልቀት ተወያይቷል። ከውይይቱ በኋላም ተቋማቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያና የጀርመን የመረጃና የደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነትን ፣ሕገ-ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውርን እንዲሁም ሌሎችንም ወንጀሎች በጋራ ለመከላከል የመረጃ ልውውጥ ማድረግም የስምምነታቸዉ አካል መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልገሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከዉ መረጃ አመልክቷል።
በሌላ ዜና በአዲስ አበባ እና በዴንቨር ከተሞች የሁለትዮሽ ስምምነት የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። ስምምነቱን አስመልክቶ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት የስምምነቱ ትኩረት የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በንግድ ፣ በኢንቨስትመንት እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
“በአለም የንግድ ቀን ፕሮግራም ላይም ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ምርቶችን አቅርበናል” ያሉት ከንቲባዋ በዴንቨር ከተማ ከአቀባበል ጀምሮ በቆይታቸው ለተደረገላቸው መስተንግዶ ከንቲባ ሃንኮክን እና ባልደረቦቻቸውን አመስግነዋል። ኢዜአ
በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉ
በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በትህነግ መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ ብዙዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አንድ ኮሎኔል…
የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉ
በተመረጡ ቦታዎች፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን ፋኖ አስታወቀ። ይህን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአባይ ድልድይን ለመመረቅ ወደ ባህር ዳር እንዳይመጡ ለ”ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ” በሚል በተለያዩ ቦታዎች ቦንብ ማፈንዳቱን ሃላፊነት ወስዶ ባስታወቀበት ወቅት ነው።…
ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
አሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች፤ ኤምባሲው ንግግር መደረጉን አስታውቋል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ…
ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
ፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በህዝብ ጥቆማ እንደሆነ ተመልክቷል። ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ…
“ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
በሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መገኘቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አማራ ክልል…