Site icon ETHIO12.COM

በመገፋት የሚጸነሰ ጽናት

አሊሰን ፊሊክስ በተለያዩ የሩጫ ውድድሮችን በማሸነፍ ትልቅ ስም ያላት አሜሪካዊት የአጭርና መካከለኛ ርቀት ፈጣን ሯጭ ናት ።
ይህ ታዋቂነቷም ፡ እውቁን የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይክን ስቦት የረጅም ጊዜ ውል አስፈርሟት ነበር ። እና በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ አሊሰን አረገዘች ።
ይህን የሰማው የረጅም ጊዜ ስፖንሰሯ ናይክ ፡ ከንግዲህ በባለፈው ውል መቀጠል አንችልም ። ከእርግዝናና ከወሊድ በኋላ እንደድሮው ልትሆኚ ስለማትችይ 70% ክፍያሽን እቀንሳለሁ አላት ። አሊሰን ይህ መሆን የለበትም ስትል ከናይክ ጋር ተከራከረች ።
ሆኖም ናይክ ይህን ቅሬታዋን ከመመለስ ይልቅ ቃል በቃል ” Know your place and just run ” ልክሽን ( ደረጃሽን አውቀሽ ትሮጭ እንደሁ ሩጭ ) በማለት በውሳኔው ፀና አሊሰን ጥሩ እንደዛ ከሆነ ከናንተ ጋር ያለኝን ውል አቋርጣለሁ አለች ። ናይክ በዚህ ተስማማ ውላቸው ተቋረጠ ።
አሊሰን ፊሊክስ የመጀመሪያ ሴት ልጇን ወለደች ።
እና ከሁለት አመት በኋላ ወደ ልምምድና ውድድሩ ተመለሰች ። ቦታሽን ደረጃሽን አውቀሽ ዝም ብለሽ ሩጪ ያላትን የናይክን ልብ ሰባሪ አባባል ወስዳም “I Know My Place ” ( ደረጃዬንማ አውቃለሁ ) የሚል የድርጅት ሞቶ ያለው SAYSH የሚባል የራሷን ብራንድ ፈጥራ ፡ በራሷ ካምፓኒ የተመረተ ጫማ ለብሳ መሮጥ ጀመረች ።

እና በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው ኦሎምፒክ መድረክ ተሳትፋ 11 ሜዳልያዎችን ሰብስባ ብዙ ሜዳልያ በማግኘት ታሪክ ሰራች ።
አሁን ላይ በአሊሰን ፊሊክስ ካምፓኒ የሚመረተው ይህ SAYSH የሚባለው ጫማ በ150 ዶላር የሚሸጥ ተቀባይነት ያለው ብራንድ ሆኗል ።
Wasihune Tesfaye

Exit mobile version