Site icon ETHIO12.COM

ኢዜማን ጨምሮ ስድስት ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ቀይሩ ተባሉ፤ ኢዜማ በመላው አገሪቱ ብቻውን ይወዳደራል

ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመረጧቸውን ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አደረገ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ እየተከናወነ እንደሆነ ይታወቃል።በዚህም መሰረት እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ያስገቡ መሆኑን የገለጸው ቦርዱ፤ ስድስት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ አድርጓል።በዚህም መሰረት

1. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ፣

2. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየ

3. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየ

4. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ

5. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ – ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ

6. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል።)“በዚህ መሰረት የምርጫ ምልክቶቻችሁን ያላስገባችሁ፣ እንድትቀይሩ የተገለፀላችሁ ወይም መቀየር የምትፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንድታጠናቅቁ ቦርዱ እያሳሰበ የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎችን ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል” ብሏል።

በሌላ የምርጫ ዜና ኢዜማ በቀጣዩ ምርጫ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ሳይዋሀድ ብቻውን በመላው የሃገሪቱ የምርጫ ወረዳዎች እንደሚወዳደር አስታወቀ።የኢትዮጲያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሳወቀው ለቀጣዩ ስደስተኛ ዙር ሃገራዊ ምርጫ በመላ ሃገሪቱ ባሉት 435 የምርጫ ወረዳዎች ዕጩዎችን ያቀርባል፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንደተናገሩት ፓርቲያቸው በአዲሰ አበባ በሚገኙ 23 የምርጫ ወረዳዎች ለመሳተፍ ከፍተኛ ዝግጅት ላይእንደሚገኝ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ካሰራጩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

Exit mobile version