Site icon ETHIO12.COM

በማይካድራ እስከአሁን 117 መቃብሮች ተገኝተዋል፤ ጋዜጠኖች በነጻነት እንዲዘግቡ ተፈቀደ

በማይክድራ ተጨማሪ 117 መቃብሮች መገኘታቸውንና እስካሁን ድረስ ሲካሄድ የቆየው የሃኪሞች የምረመራ ውጤት በቅርቡ ይፋ ሲሆን የወንጀሉ ዝርዝር ይፋ እንደሚሆን የፊደራል አቃቤ ህግና ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ አስታወቁ። በይፋ በመግለጫው ላይ ባይገኝም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ይህን ድርጊት ገብተው እንዲዘግቡ የቃድ ተሰጥቷል።

ዛሬ ፋና እንዳለው በማይካድራ ጭፍጨፋ ከተሳተፉት 279 ተጠርጣሪዎች መሀል ያልተያዙትን ለማደንና ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቀዋል።

ከታች ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።ከማይካድራ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የአካባቢው ወጣቶች ሙሉ የምግብ አቅርቦት ተሟልቶላቸው ፀጥታን ታስከብራላችሁ በሚል ተመልምለው ስምሪት እንደተሰጣቸው ተገለፀ፡፡ ጭፍጨፉውን የሚያከናውኑበት ስለታማ ነገሮችም ቀድሞ ታድሏቸው እንደነበረ ተገልጿል። በጉዳዩ ላይ በተደረገ ምርመራ ጭፍጨፋው ብሄር ተኮር እና በአብዛኛው ወንዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡በሂደቱም 10 ሴቶች መደፈራቸው ነው የተነሳው።

ከጭፍጨፋው በኋላም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከ117 በላይ ጉድጓዶች መገኘታቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ እና የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራልና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም መንግስቴ በጋራ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡ሙሉ ውጤቱም በምርመራ ስራው ላይ ከተሳተፋ ሀኪሞች ሲገለፅ ይፋ እንደሚደረግ ተነግሯል ። በማይካድራ ጭፍጨፋ ከተሳተፉ 279 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 36ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡ ቀሪዎቹ በስደተኛ ስም ወደ ሱዳን ገብተዋልም ነው የተባለው፡፡ ምርመራው አሁንም ያልተጠናቀቀና በተቋቋመው ግብረ ሀይል አማካኝነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል ። 

ፋና ባይዘግበውም ኢትዮ 12 እንዳጣራቸው መንግስት ጋዜጠኖች በነጻነት ገብተው እንዲዘግቡ ፈቃድ ሰጥቷል። ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ይኸው ተጋባራዊ ይሆናል።

Exit mobile version