ETHIO12.COM

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህጋዊነት የተመዘገቡ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወስደዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ለማከናወን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል አንደኛው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት/ የሚያስገቡበት መርሃ ግብር መሆኑ ተመላክቷል

በጊዜ ሰሌዳው መሰረትም  ከጥር 13 ቀን እስከ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፓርቲዎች ምልክት የሚያስገቡበት እና ቦርዱ አጣርቶ የሚያፀድቅበት እንደሆነ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፀድቋል። በዚህም መሰረት ምርጫ ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እና ምልክቶቻቸውን በ ፌስቡክ ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል።

Exit mobile version