Site icon ETHIO12.COM

ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ በመላው ዓለም ከተፈፀሙ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃቶች በርካታ ንፁሃን ዜጎች የተገደሉበት ወንጀል ሆኖ መመዝገቡን ኢንተርፖል አስታወቀ

ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው የሽብር ወንጀል በመቅደም በርካታ ንፁሃን ዜጎች የተገደሉበት ወንጀል ሆኖ መመዝገቡን ኢንተርፖል አስታወቀ

ጁንታው ባሰማራቸውና ሳምሪ በተሰኙ ፀረ-ሰላም ሃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው የሽብር ወንጀል በመቅደም በርካታ ንፁሃን ዜጎች የተገደሉበት ወንጀል ሆኖ መመዝገቡን አለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል አስታወቀ።

እአአ በህዳር 2020 በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃቶችን አስመልክቶ አለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል መረጃ ያወጣ ሲሆን፤ በጁንታው በተሰማሩና ሳምሪ በተባሉ ሃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቦኮሀራምና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለያዩ ሀገራት ከፈፀሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው ብሎታል።

ጁንታው እኩይ ተልዕኮውን ለማሳካት አስታጥቆ ያሰማራቸው ሳምሪ የተሰኙት ንጹሀንን የጨፈጨፉት ሀይሎች በማይካድራ በፈፀሙት ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ግድያ 600 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን በኢንተርፖል የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ያወጣው መረጃ ያሳያል።

እነዚህ ቡድኖቹ የፈጸሙት ጭፍጨፋ ከሰብዓዊ ፍጡር በማይጠበቅ መልኩ ጭካኔ የተሞላባቸው ናቸው ያለው መረጃው፤ ድርጊቱን አጥብቆ ኮንኗል።

ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋና ናይጄሪያ ውስጥ ሜይጉዱሩ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቦኮሃራም ያካሄደው ግድያ በሰብዓዊነት ላይ ከተፈፀሙ ከባድ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚ ተርታ ላይ የሚሰለፉ ናቸው ብሏል።

(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version