Site icon ETHIO12.COM

“ትህነግ ኤርትራን እንዳትነሳ አድርጎ የማውደምና የህዝቡን ማህበራዊ ክብር የማዋረድ እቅድ ነበረው” ተስፋዬ ገ/አብ

ተሳፋዬ ገብረአብ ” የጄኔራሉ ዳግማዊ ስህተት!” ሲል በቀድሞው ጄነራል ጻድቃን ተሳልቆ ” ስላልተፈጸመ የማልጽፈው” ያለውን አሰቃቂ እቅድ ሚስጢር አድርጎ ዜና አሰራጨ። በተመሳሳይ ገጹ ላይ ” ሰበር ዜና ጠብቁ” ሲል ሌላ ሚስጢር አስቀምጧል። ዜናውን ገምቱ ብሏል።

በዜናው ትህነግ ኤርትራ ላይ ደግሶ የነበረውን በዝርዝር ጽፏል። ከአማራ በመቀጠል ” ኤርትራን ለዘላለሙ እንዳትነሳ አድርጎ ማውደም። መሰረተ ልማቶችን ማፈራረስ፣ የኤርትራውያንን ትውፊት፣ ማህበራዊ ክብር፣ አገራዊ ስሜት እና ሰብአዊ ኩራት መድፈር እና ማዋረድ – ነበር የታሰበው” ሲል ተስፋዬ ጽፏል። ከኤርትራ ጉዳይ ውጪ ያለው ዜና በተደጋጋሚ የተደበደበና አቃቤ ህግ ሰነድና ማስረጃ አስደግፎ ያቀረበው ሪፖርት ላይ የሰፈረ ነው። እንደሚከተለው ይነበባል።

መቼም ጄኔራል ጻድቃን እንዲህ ያለ ዳግማዊ ስህተት ላይ ይወድቃል ብዬ ገምቼ ባለማወቄ ራሴን ታዘብኩት። ራሴን የታዘብኩት እነ ስዬ፣ እነ ጻድቃን፣ እነ ስዩም፣ እነ አባይ በትክክል ያቀዱትን፣ ያለሙትን፣ የተመኙትን የከሸፈ ህልም ከሰማሁ በሁዋላ ነው።

እቅዳቸው ወዲህ ነው!

በቅድሚያ የኢትዮጵያን መከላከያ ሃይል ማጥቃትና መቆጣጠር። በመቀጠል ጎንደር፣ ባህርዳር እና ደሴን መቆጣጠር።

ልክ በዚህ ጊዜ አብይ አህመድ ቤተሰቡን ይዞ ስለሚኮበልል አዲሳባ ላይ በተደራጁ አባላት እና ደጋፊዎች ቤተመንግስቱን መቆጣጠር።

በመቀጠል ትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን በማስገደድ ከፊት በማስቀደም እንደ ፓሎኒ ኩዋስ እየነጠሩ አስመራ እና ምጽዋን መያዝ።

ከዚያም ህሊና አልባ ኢትዮጵያውያንን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ምኒስትር አድርጎ በመሾም ኢትዮጵያን በእጅ አዙር መግዛት።

በመቀጠል ኤርትራን ለዘላለሙ እንዳትነሳ አድርጎ ማውደም። መሰረተ ልማቶችን ማፈራረስ፣ የኤርትራውያንን ትውፊት፣ ማህበራዊ ክብር፣ አገራዊ ስሜት እና ሰብአዊ ኩራት መድፈር እና ማዋረድ – ነበር የታሰበው።

እዚህ ለመግለጽ የማልፈልገው አሰቃቂ ድርጊት በኤርትራውያን እና በአማራ ማህበረሰብ ላይ ለመፈጸም አቅደው እንደነበርም በቂ መረጃ አለኝ። ልገልጸው ግን ፍላጎት የለኝም። ምክንያቱም ታሰበ እንጂ ስላልተፈጸመ መግለጹ ጥቅም የለውም። የታሰበውን ቀርቶ የተፈጸመውን የአርሲ የጦርነት ታሪክ በጨረፍታ በመጻፌ እንኳ የተሸከምኩትን ሸክም እኔ ነኝ የማውቀው።

ዞረም ቀረ ወያኔ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ንጹሃን ዜጎች ላይ ለመፈጸም ያቀደውን አሰቃቂ ድርጊት መፈጸም በጀመረ ልክ በ18ኛው ቀን ነገሮች ሌላ ሆኑ። ክፉ አሳቢ የወያኔ መሪዎች ክፉ ገጠማቸው። ተማረኩ ወይም ተገደሉ። ባህርዳር እና አስመራን ለማውደም ያሰቡትን ራሳቸው በራሳቸው ላይ ፈጸሙት። በ30 አመታት የገነቡዋትን ትግራይ በ3 ሳምንታት አፈራረሷት። እናም የወያኔ መሪዎች ከሚሳኤል መተኮስ ወደ መማረክ ተሸጋገሩ። ከዚያም አልፎ በአሜሪካ መሬት ላይ ሲንደባለሉ ታዩ። ይህ መንደባለል አሳፋሪ ትርኢት ሆኖ ታየ።

ጄኔራል ጻድቃን በእግሪ መኸል ውጊያ በገጠመው አሰቃቂ ሽንፈት ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰ ሰው እንደመሆኑ እንዴት ዳግም ሊሳሳት እንደቻለ ግን መረዳት አቅቶኛል።

Exit mobile version