Site icon ETHIO12.COM

አዲስ አበባን በኑሮ ውድነት ለማተራመስ እቅድ ተይዟል፤ ከ2 ሚሊዮን በላይ ጀሪካን ዘይት በድብቅ ተከማችቶ ተገኘ

አዲስ አበባ ላይ በንግድ አሻጥር ነውጥ ለማስነሳት የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተሰማ። በተለያየ የፖለቲካ ሴራ የተሞከረው አገሪቱን የማመስ ሙከራ ባለመሳካቱ ሕዝቡ በኑሮ ውድነት እንዲነሳ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንን ያስታወቁ እንዳሉት፣ እነዚህ አካላት በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ የሚያደርጉት የመጨረሻ ሙከራ እንደሆነ ታውቋል።

መርካቶ በአከፋፋይነት የሚሰራ የመረጃ ምንጭ እንደነገሩን መንግስት አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ መጋዘኖችን እንዲያስስ ጠቁመዋል። አያይዘውም አዲስ አበባ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ባሉ መጋዘኖች ውስጥ ቀበሌዎች ያልታሰበ ፍተሻና ቅኝት እንዲያደርግ መክረዋል።

ምርትን በመደበቅና በገበያ ላይ ያሉ ምርቶችን በመሰብሰብ የአቅርቦት እጥረት በመፍጠር የኑሮ ውድነቱን ማጋጋል፣ የኑሮ ውድነቱን በማጋጋል በሚዲያ ማስተጋባት፣ ፖለቲከኞችና አጋሮቻቸው አጀንዳውን በመቀባበል ህዝብ እንዲነሳሳ ለማድረግ በጥምረት ለመስራት ነው እቅድ የተያዘው።

በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት መኖሩን የሚያምኑ እንዳሉት አሁን የተያዘው ይበልጥ የአቅርቦት እጥረት በማባባስ ሕዝብ ለዓመጽ እንዲነሳ ማነሳሳት ነው። አንዳንድ ፖለቲከኞችና ደጋፊዎቻቸው ይህንኑ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ጅማሮ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ሕዝብ በኑሮ ውድነት ሁከት እንዲያስነሳና ምርጫው እንዲረበሽ አቅደው የሚሰሩት ክፍሎች በዋናናት አዲስ አበባ የከተሙና ከቀደመው አስተሳሰብ ጋር ቁርኝት ያላቸው እንደሆነ ነው መረጃውን የሰጡት የተናገሩት።

መንግስት ሰፊ ጥቆማ እንደደረሰው ያመለከቱት ጥቆማ ሰጪ እንዳሉት በቅርቡ በርካታ ሸቀጥ የደበቁ እንደሚያዙ እምነታቸውን ገልጸዋል። ሰፊ መረጃ መንግስት እንደደረሰውና አንዳንዶች መሳሳታቸውን ጠቅሰው ኔት ዎርኩን እንዳጋለጡም አመልክተዋል።

ሕዝብና መዋቅሩን የሚያውቁ ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር መዋሉን ኢዜአ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት ሊያዝ የቻለው ፌዴራል ፖሊስ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ነው።

Exit mobile version