Site icon ETHIO12.COM

የአሜሪካ መንግስት በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገለፀ!!!!

የአሜሪካ መንግስትን አቋም ይፋ ያደረጉት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የሚድያ ዳይሬክተር የሆኑት ሳሙኤል ዌርበርግ ናቸው።

ዳይሬክተሩ ከግብፁ መኸዋር ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ “በህዳሴው ግድብ ጉዳይ የጆ ባይደን መንግስት #ጣልቃ_አይገባም” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳን በውይይት ልዩነታቸውን መፍታት ይችላሉ ብሎ የአሜሪካ መንግስት እንደሚያምን የገለፁት ሃላፊው፤ “ልክ አሜሪካ እና ካናዳ በወሰን ተሻገሪ ወንዞች ውሃ አጠቃቀም ላይ የፈፀሙትን አይነት ስምምነት ሶስቱ ሃገራት ማድረግ ይችላሉ” ብለዋል ።

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ተጎራባች ሃገራት ከመሆናቸው ባሻገር ጥንታዊ ናቸው ያሉት ዌርበርግ፥ “የሚጠቅማቸውን እና የሚጎዳቸውን መለየት ይችላሉ ” ሲሉም ተናግረዋል።

በቃለ መጠይቁ ላይ ” ወደፊትስ የጆ ባይደን መንግስት ምን አይነት ሚና ሊኖረው ይችላል?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፥ ” ስልጣን ከተረከበ አጭር ጊዜ የሆነው የባይደን አስተዳደር ስለግድቡ ግምባታ ሆነ፥ ስለድርድሩ ሁኔታ ምንም መረጃ ለጊዜው የለውም፤ ገና ወደፊት ጊዜ ሲፈቅድ ነው ስለጉዳዩ በዝርዝር የሚያውቀው ” በማለት በይፋ አስታውቀዋል።

ምን አልባት ሶስቱም ሃገራት ተስማምተው ጥሪ ካቀረቡ ግን የአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚችል ገልፀዋል።

“የአሜሪካ ሚና ማደራደር ይሁን፥ ቴክኒካዊ ድጋፍ መስጠት የሚለውን ተስማምተው መወሰን ያለባቸው ሶስቱ ሃገራት ናቸው። ያለ ሶስቱ የጋራ ስምምነት የምናደርገው ምንም ነገር የለም።” በማለት ጆ ባይደን ትራምኘ በጀመሩት መንገድ ፈፅሞ እንደማይቀጥሉ አስገንዝበዋል ።

“በዶናልድ ትራምኘ አስተዳደር ጊዜ አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ድርድር የነበራት ሚና ምን እንደነበር #መፈተሽ አለበት” ሲሉም ዌልበርግ ገልፀዋል።

በእኝህ ከፍተኛ ሃላፊ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የተገለፀው የአሜሪካ መንግስት በህዳሴ ግድብ ያለው ወቅታዊ አቋም የግብፆውያንን አንጀት አሳርሯል።

መረጃው ይፋ የሆነው ግብፃውያን የባይደንን ድጋፍ ለማግኘት ሁሉንም አማራጭ እየሞከሩ ባሉበት ወቅት መሆኑ ደግሞ ለግብፅ ትልቅ ክስረት ነው!!! ከኢትዮጵያ ጋር በመደራደር ብቻ እንጂ በሶስተኛ ወገን ጫና መፍትሄ ሊመጣ እንደማይችል ዳግም የሚያስገነዝባቸውም ነው!!!!

አዎ! ጊዜው የኢትዮጵያ ነው!!!!

Via Selam Mulugeta

Exit mobile version