Site icon ETHIO12.COM

ኢሳያስ አፉወርቂ – የትልቁ ስዕል ቅኔ፣ የቅዠቱ መነሻ፣ የቀጣናው ባዶ የፖለቲካ ጉሊት

ኤርትራን ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ያለ ተቀያሪ እየመሩ ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በየዓመቱ የሚያቀርቡት ይፋ ንግግር ለመዘግየቱ ብዙ ምክንያት ቢደረሰርም ትናንት ሰፊውን ትንታኔያቸውን አሰምተዋል። ትንታኔያቸው የፖሊሲ ለውጥ ዜና ይኖርበታል የሚል ግምትና ዜና ስለነበር በጉጉት ቢጠበቅም “ ስሙና ቀዳሚውን ምረጡ” የሚል ሃሳብ አጋርተዋል።

በሶስት አበይት ሃሳብ የተከፋፈለው ንግግራቸው/ጥያቄና መልስ አይባልም/ እጅግ ጥልቅ የሚባል ስለመሆኑ፣ ክርክር የለውም። ሃሳባቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እምነት ጋር እንደሚመሳሰል በግልጽ በሚያሳየው ንግግራቸው፣ የቀጠናውን ጂኦ ፖለቲካ አራት ቦታ በልተው ሁሉም ብልቶች ያላቸውን መስተጋብር፣ መስተጋብራቸው አንዱ ከአንዱ እንደሚቆረኝ፣ አንዱን የሚነካ ሌላውን እንደሚነካ ገላጻ ሰጥተዋል።

በገለጻቸው ቃል በቃል ባይናገሩም ትህነግ በቀጣናው ላይ እንዴት ያለ በሽታ እንደነበር ትልቁን ስዕል በመሳል አሳይተዋል። ትልቁ ሰዕል ከተሳለ የቆየ ቢሆንም ትህነግ በሚከተለው ፖለቲካ ሳቢያ ስዕሉ ኢህአዴግ ውስጥ ለውጥ እስክመጣ ድረስ ውበቱ ሊታይ አልቻለም ነበር።

“ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ ምርጫችን ናት” ለምን?

ኢሳያስ ቃል በቃል ኢትዮጵያ ለኤርትራ አንደኛ ምርጫዋ እንደሆነች አስታውቀዋል። ይህን ያሉት ግን ዝም ብሎ ለማለት ሳይሆን በሂሳብና በፖለቲካዊ እሳቤ ቁልጭ ባለ ማብራሪያ ነበር። ብዙዎች ከሰሞኑ የህግ ማስከበር ዘመቻ ጋር አያይዘው ቢተረጉሙትም ጉዳይ ለየቅል ነው።

የናይል ተፋሰስ አገራት፣ የምስራቅ አፍሪቃ ጎረቤታሞች፣ የቀይባህርና የባብ ኢልማንደብ ወሽመጥ ተጋሪ አገሮችን ለይቶ በማሳየት የቀጣናውን የፖለቲካ ፍስት ያስቃኙት ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸው እጅግ ውብ ሊከቸር ነበር የተባለው እዚህ ነጥብ ላይ ነው።

አራቱን ዋና ጉዳዮች ካነሱ በሁዋላ ያደጉት አገራት / ጡንቸኞቹ / ማለታቸው ነው፣ ፍላጎታቸውን ሲያክሉበት ሙሉ ቀጣናው የዓለም ፖለትካ እምብርት መሆኑ ይታያል። በዚሁ መነሻ በቀተናው ላይ ያለው የተለያየ ፍልጎት በምስራቅ አፍሪቃ ውስጣቸው የረጋ ጠንካራ መንግስታት እንዲኖር እንደማያስችል አዙረው ያስረዳሉ። እንደ ፍላጎታቸው መጠንና ብዛት ያሻቸውን ለማድረግ ሲሉ ችግር ይደፋሉ። ወይም ስፖንሰር ያደርጋሉ።

ትህነግ ኢትዮጵያ ላይ ሲከተለው የነበረው የዘር ፌደራሊዝም ፍጹም አግባብ እንዳልሆነ፣ ዝድሮ ችግር እንደሚያመጣ፣ በዓለም የተለያዩ አገራት ተሞክሮ ውጤቱ አደገኛ እንደሆነ የሚታወቅ የጎሳ ፌደራሊዝም ኢትዮጵያ ላይ ሲታወጅ እያወቁ ለዚሁ አጥፊ ስርዓት 20 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውን ኢሳያስ

አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ወደብ ባይኖራትም የቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ ቀዳሚ ሚና እንዳላት ኢሳያስ ሲናገሩ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ የሆነችበትን ዘመን ለቅሶ ያስታውሳል። ከግብጽ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ሶማሌና ኬንያ ተለይታ ወደብ አልባ እንድትሆን በመሪዎቿ የተፈረደባት ትዮጵያና 120 ሚሊዮን ህዝቧ በቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ ሚናዋ እጅግ የጎላ መሆኑንን ኢሳያስ ሲናገሩ ማዳመጥ ልብን ያቆማለ። ሆኖም ግን ኢሳያስ ባዩበት መንገድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወያኔ ያፈረሠውን የባህር ሃይላ እንደገና ማቋቋምቸው ሲሰናሰል የኢሳያስ ስዕል ጨረፍታው መታየት ይጀምራል። በዚሁ ስዕል ሂሳብ ኢትዮጵያ ከ120 ሚሊዮን ሕዝቧ ጋር ለኤርትራ ህዝብ ቅድሚያ ታስፈልጋለች።

ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ ጋር ተያይዞ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ታዩ አልታዩ ለሚለው ጉንጭ አልፋ ጩኸት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ከሁሉም ትበልጣለች ሲሉ በቅርቡ ወደ ተግባር ይገባል ባሉት ኢኮኖሚያዊ ቁርኝትና ከሁለት ዓመታት በፊት የፈረሙት የወታደራዊና ደህንነት የጋራ ስምምነት መሰረት እንደሆነ ልብ ይሏል። በዚህ እሳቤ በምራቅ አፍሪቃ ኮሪዶር ላይ ጡንቸኞቹ ለሚያራምዱት ማናቸውም የጥቅማቸው ማስፈጸሚያ ዘመቻ ኤርትራና ኢትዮጵያ መረብ መመሰረታቸው ምን አልባትም አብይ አሕመድ እንደሚሉት ሁለቱ አገራት የቀጣናው አክተር ለመሆን አቅደው እየሰሩ መሆናቸውን ያሳያል። ሶማሌን ጨምሮ!!

መለስ – ኢትዮጵያ ላይ የተጫነ ከሃጂ

ኢሳያስ ትልቁን ስዕል ሲያሳዩ በቅዠት በኢትዮጵያና ኤርትራ ፍራሽ ላይ ትገነባለች የተባለቸው ታላቋ ትግራይ እውን እንድትሆን ተይዞ የነበረውን እቅድ ቀደም ሲል ቢነካኩትም በዛሬ ንግግራቸው አድምተውታል። ከኢትዮጵያና ከዓለም እይታ እንደ ቪኖ ቡሻ ተስፋንጥረው በድንገት ተረት የሆኑት አቶ መለስ “ እስከ ቻልን እንገዛለን፣ አንገዛም ሲሉ በየቦታው ፈንጂ ይፈነዳዳል” ሲሉ የመለሱላቸው መልስ ያስታወሱት የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ውልደትና ሞትን አጠር አድርገው ሲያስረዱ ነበር። ይህን ይዘው ነው ዛሬ “ ኢትዮጵያ ስትፈራርስ በማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ” የሚሉ ትፋቶች የሚሰሙት።

አፍቃሪ ትህነጎች ኤርትራ እንድትገነጠል መለስ ውለታ መራታቸውን፣ ቀድመው እውቅና መስጠታቸውን፣ እሱ ብቻ ሳይሆን የአሰብ ወደብን እንደምያፍለጉ ለተባበሩት መንግስታት ደብዳቤ መጻፋቸውን እንደ ኩራት ያነሳሉ። በዚሁ ኩራታቸው ኢሳያስን ከሃጂ ያደርጋሉ። መለስ ግን አሰብን ለመስተት ሲስማሙ በሁዋላ ላይ / ትግራይ አገር ስትሆን ማለታቸው ነው/ አሰብን ከኢትዮጵያ ላይ ከመውሰድ ከኤርትራ ላይ መቀማት ይቀላል በሚል ሂሳብ እንደሆነ ይህን ሪፖርት ያዘጋጀው መረጃው አለው።

አቶ መለስ አወረሱ የሚባለው ሌጋሲ ወይም ውርስ ሲጠቃለል “ ማእከላዊ መንግስቱን መምራት ካልቻልን ትግራይን ገንጥለን ሌሎቹን እናባላለን” የሚል ሰይጣናዊ የፖለቲካ ሂሳብ እንደሆነ ፍንትው አድረገው ያሳዩት ኢሳያስ “ ህገ መንግስት ብሎ እንዳነብና አስተያየት እንድሰጥ ጠየቀየኝ። ሁለት ቀን ደጋግሜ አየሁት። ከዛም ይህ አይሆንም አልኩት። መለስም እንደሱ እንደምትል አውቅ ነበር። ግን እሱኑ ነው የምናስቀጥለው” ሲሉ አቶ መለስ እንደመለሱላቸው አስታውሰዋል።

የሚመራትን አገር እንዲህ ባለ ደባ ሲተበትቧት የነበሩት መለስ በአምላክ ፍርድ ላይመለሱ ሲያሸልቡ አገር ዙሪያው አበል ተከፍሎት ሃዘን እንዲቀመጥ፣ ለዚሁ ማንነታቸው የሚሆን መታሰቢያ ግብር ከቁሚዎች ላይ እንዲወሰድ፣ ሰፊ መሬት ተከልሎ የዚሁ ዓላማ አራማጆች እንዲፈነጩበት መደረጉ ኢትዮጵያ ማን ላይ ወድቃ እንደነበር……..

ሲጀመር የኢትዮጵያን ታሪክ አምክኖ ለማፈራርስ በማቀድ ሲሰራ የነበረው ትህነግ በመለስ ውርስ እየጋለበ ለውጡ ረግጦ ወደ ትግራይ ከገባ በሁዋላ የያዘው አባዜ ግብአቱን እንዳጣደፈለት ኢሳያስ ሲናገሩ “ ጦርነት ምን እንደሆነ የማያውቅ” ሲሉ ነው ያንኳሰሱት። የተረፈው ሃይልም ተለቅሞ እንደሚጠፋ ሲናገሩም “ ሊረዱዋቸው የሚፈለጉ አሉ። አይሳካም” ሲሉ የተከፋዮችን ጩከትና ለቅሶ እንዳልሰማ አልፈውታል።

ትልቁ ስዕል – ኢትዮጵያና ኤርትራ

ኢሳያስ ቀሪውን “እናንተ አስቡት” በሚል ሂሳብ ትልቁን ስዕል ሲያሳዩ ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ናት። የዓለም አቀርፍ ተቋማት መቀመጫ ናት። በምስራቅ አፍሪቃ በህዝብ ብዛትና በርካታ ጎረቤት ያላት አገር እንደመሆኗ፣ የናይል ፖለቲካ እምብርት እንዲሁም የቀይ ባህር ፖለቲካ የሚመለከታት በመሆኑ፤

ኤርትራ የቀይ ባህር እምብርት፣ የናይል ተፋሰስ አካል፣ ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣የመንና ሳዑዲ አረቢያ ጋር የባብ ኤልማንደብ ወሽመጥ ተጋሪ፣ የምስራቅ አፈሪቃ ፖለቲካ አባል እነደመሆኗ ሁለቱ አገሮች የውስጥ ሰላማቸውን አጠናክረው ህብረት ቢፈጥሩ በቀጣናው ምን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ኢሳያስ ያሳዩት ትልቁን ስዕል በመሳል ነው።

ወያኔ አፈጣጠሩም ሆነ እድገቱና ዓላማው ትልቁን ስዕል ማየት ሰለማያስችለው አገሪቱን በጎሳ ፖለቲካ ተብትቦ ሲርመጠመጥ መቆየቱ ኢሳያስ ያሰቡትን ስዕል መየት እንዳልተቻለ በተዘዋዋሪ ተናግረዋል። ጉዳዩ የእይታና የሩቅ አሳቢ መሆን ጉዳይ በመሆኑ ዛሬ አብይ አህመድ በምስራቅ አፍሪካ ሊፈጠር ይገባዋል ከሚሉት የንግድና የፖለቲካ መጋመድ እሳቤ አንጻር ኢሳያስ መደመራቸውን ያረጋገጡት ሃሳቡ ቀድሞም በውስጣቸው እንዳለ በማሳየት ነው።

አብይ አህመድን በቀናነት ደጋግመው ያነሱዋቸው አቶ ኢሳያስ ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳን በዘር፣ ሶማሌ በጎሳ እየተፋለሙ ለዚህ የከፋ ደረጃ መድረሳቸውን አንስተው “ የጎሳና የዘር ፖለቲካ” ከቀጣናው መጥፋት እንዳለበት ገልጸዋል። የዘር ፖለቲካ መቆሚያ እንደሌለውና ወርዶ ወርዶ ቤተስብ እስከመቁጠር እንደሚያደርስ ያስታወቁት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ ጎሰኛነት ሲጠፋ ብቻ ትልቁን ስዕል ማየት እንደሚቻል ጠቁመዋል። ጎሰኝነት እንዲወገድ አሳስበዋል።

የሰላም ስምምነቱ እንደተጀመረ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከወያኔ ሰዎች ጋር እንዲገናኙ፣ ሁሉም ነገር እንዲከፋፈት ይፈልጉና ይጠቁ እንደነበር ያስታወሱት ኢሳያስ “ አብይ አህመድ ክትህነግ ሰዎች ጋር በቀናነት ሊሰራ ሞክሮ ነበር” ካሉ በሁዋላ እሳቸው ግን ከሚያውቁት የወያኔ ባህሪ አንጻር እርጋታ መምረጣቸው፣ ከወያኔ ባህሪ አንጻር መቻኮል እንደይገባና ዋጋ እንደሚያስከፍል፣ ለዚህም የዳረጋቸው ከወያኔ ጋር ምንም ነገር መስራት እንደማይቻል ማረጋገጣቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

ያም ሆኖ ኦምሃዠር ላይ ከዶክተር ደብረጽዮን ጋር ሲገናኙ “ ለምንድነው ለጦርነት የምትዘጋጁት” በለው ሲጠይቁ “ ጦርነት የለም” እንዳሉዋቸው ደግመው “ እየተዘጃጃችሁ እኮ ነው” ሲሉ “ እመነኝ ጦርነት የለም” ሲሉ ደብረጽዮን መመለሳቸውን አስታውሰዋል። በወቅቱ ምክር መለገሳቸውንም አንስተዋል።

የኢሳያስ ንግግር የአንድ ወገን ቢሆንም ንግግራቸው ሚዛን የሚደፋው ትህነግ ኢሳያስን ለማስወገድ ተቃዋሚ ከማደረጃት አልፎ የኤርትራን ደጋማ አካባቢዎች በማካለል አገር ለመስረት ሲንቀሳቀስ እንደነበር በርካታ ማስረጃ መኖሩ ነው።

ባዶ ጉሊት – የረሃብ ጩኸት

የትህነግ መሪዎች ድንገት ተስፈንጥረው ትግራይ ከገቡ በሁዋላ በቀጠናው የነበራቸው ድምጽ ሟሟ። በዚህ መልኩ ከቀጠሉ ሙሉ በሙሉ ስለሚቀልጡ “ አለን፣ ያለ እኛ” በሚል ሁከት ስፖንሰር ማድረግ ጀመሩ። ምስራቅ አፍሪቃ እንደሚነድ በቅምጥ ሚዲያዎቻቸውና በሚከፈላቸው ነጫጮቹ ካድሬዎች ውስወሳውን አጠናከሩ። ጎን ለጎን በውስጥ ካሉ ባንዶች ጋር ስልጣን ተቧድነው በሶስት ሳምንት የሚያልቅ ጦርነት ነደፉ። ይህንኑ ጦርነት እነ ዳንኤል ብርሃኔ እንደ ህንድ ፊልም “ አጠር ቀልጠፍ ያለ፣ ጊዜያችንን በማይገድል መልኩ፣ ወጪ ሳናበዛ … ” እያሉ ሲተነትኑት ነበር።

ዋናዎቹ ሞንስተሮች ደግሞ ህጻናት እየመለመሉ ወታደራዊ ሰልፍ ያስኮመኩሙ ገቡ። ወዳጆቻቸው በትርክት ታሪክ ልባቸው ተደፍኖ፣ በተዘረፈ ሃብት ህሊናቸው ተዘግቶ “ ጦርነት ባህላችን፣ የባህል ቸዋታችን” እያሉ የድሉን ወላፈን ፈጥረው እያሸተቱ ሰክረው ሰላማዊውን ህዝብ አሰከሩት።

በሌላ በኩል ተደራዳሪ ሃይል አዘጋጅተው ቤተመንግስት የሚገባ አሻንጉሊት ስለው ቀን ቆረጡ። ውስጥ አዋቂዎች ቢትዮጵያዊያን ሃፍረት እየተሳለቁ ሊዘፍኑ ከበሮ ጸሃይ ላይ መቀቀል ጀመሩ። የሚታሰሩ ተለዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና ካቢኒያቸው እጃቸው ተጠፍሮ መሳቂያ ሲሆኑ የታያቸው ቁጥሩ ለማይታወቅ ጊዜ መጸዳጃ ይመላለሱ ነበር። መዳሃኒት ቀለባቸው የነበረ በዚህ ፋንታዚ ወደ አልኮል አዘነበሉ። ጌታቸው እየተሳደበ ሲወራጭ በቋመጡት ደጋፊዎች ስሜት ላይ ሃሺሽ ሆነባቸው። በዚህ ሁሉ እብደትና ስካር አርፎ የተናውን አንበሳ ብልቱን ነኩት።

ኢሳያስ “ እብደት” ያሉት ቅዠት ይህ ነበር። በኩል ሰዓት አዲስ አበባንና አስመራን መያዝ። ታላቋን አገር መግንባት። ሁሉም አልሆነም። በስተመጨረሻ ባዶ የቀጠናው የፖለቲካ ጉሊት ሆነው አረፉት። ሰላሳ ዓመት ሙሉ ስንዴ ሲሰፍሩለት የነበረውን ሕዝብ ዛሬም መላወሻ የፖለቲካ ካርታ አደረጉት። በዚሁ ክፍተት ነው እንግዲህ የቀድሞ ወዳጆቻቸው ሊረዱዋቸው የሚያጫጭሱት። ኢሳያስ ግን በቅቡ ይለቀማሉ ነው ያሉት።

https://ethio12.com//wp-content/uploads/2021/02/64616539-f9ef-4c83-9c73-a5f471c5f3f7_32k-1.mp3

ኢሳያስ ስለ ኤርትራ የውስጥ ጉድይ ያሉት በሪፖርቱ አልተካከተም። ለአንባቢ ይመች ዘነድ ከቃል በቃል ትርጉም ይልቅ ሃሳባቸውን በመውሰድ መጻፉን መርጣናል።

Exit mobile version