ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ ላይ የጸጥታው ምክር ቤት ሳይስማማ ተበተነ፤ አማራ ትህነግን በህግ ሊጠይቅ ነው

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስለትግራይ ቢወያይም ያለስምምነት መጠናቀቁን ዲፕሎማቶች እንደነገሩት ጠቅሶ ኤፒ በሰበር ዜናው አመለከተ። ከቀን በፊት ስብሰባው እንደሚካሄድ ውስጥ አዋቂዎች እንደነገሩት የዜና ምንጩ በተመሳሳይ በሰበር አብስሮ ነበር።

የጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ እንደ አጀንዳ እንዲቀርብ የጠየቀችው አየርላንድ ነበረች። የስብሰባው መካሄድ እንደተሰማ የትህነግ ደጋፊዎችና የፕሮፓጋንዳ ሰራተኞች / ነጭ ተከፋይ ሚዲያዎችና ባልደረቦቻቸው አምነስቲን ጨምሮ / ዜናውን በከፍተኛ ደረጃ ሲረጩት ውለው ነበር።

ሩሲያ፣ ቻይናና ህንድ አጀንዳው የአንድን አገር ሉዓላዊነት የሚጻረር በመሆኑ መግለጫ ሊወጣ እንደማይገባ አቋም በመያዛቸው ሳይሳካ ቀርቷል። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ሉዓላዊነቷን በሚጻረር መልኩ የሚቀርቡ ማናቸውንም ጉዳዮችና አካሄዶች አጥብቃ እንደምታወግዝ በተደጋጋሚ ስታስታውቅና ከውዳጅ አገሮች ጋር በተለይ ውይይት ስታደርግ መቆየቷ የሚታወስ ነው።

ህግን የማስከበር እርምጃውን ዝቅ ለማድረግ የሚካሄድን አሉታዊ ዘመቻ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ማስታወቋ ብቻ ሳይሆን፣አሁንም መንግስት የወንጀለኛው ቡድን አባላትን እና ጥፋተኞችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ ስራውን እንደሚቀጥል በጽኑ አረጋግጦ እየሰራ መሆኑንን አመልክቷል።

Samson Michailovich የሚባሉት ኢትዮጵያዊ የማህበራዊ ገጽ አንቂ ግን ስብሰባው እንደሚካሄድ በተሰማና ኢትዮጵያ ላይ ከባድ ውስኔ እንደሚተላለፍ የሚጠቅሱ ዜናዎች ሲሰራጩ “የዛሬው የጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ! ፩. የዛሬውን የጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ እንዲያዝ የጠየቀችው አየርላንድ ነች ። ፪. ስብሰባው የትግራይ- ኢትዮጵያን ጉዳይ የሚመለከተለው እንደ ተጨማሪ አጀንዳ ነው። ( any other business) ፫. በአጀንዳው ላይ የሚደረገው ውይይት የሚያተኩረው የኢትዮጵያ መንግስት የምግብ ማዕቀብን እንደ ጦርነት ስልት ተከትሏል ወይ በሚለው ላይ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በክልሉ በሚደረገው የእህል ስርጭት ላይ ይወያያል። ፬. ስብሰባው እንዳለቀ መግለጫ አይሰጥበትም። ፭. ከፈረንጅ ተኣምር የሚጠብቁ የህወሃት አክቲቪስቶች ከዛሬው ውይይት ብዙ ይጠብቃሉ። ፈረንጅ false hope መጥፎ ነው ይላል ። የተባበሩት መንግስታት ዲፕሎማሲን የችግር መፍቻ ዋና መንገዱ ያደረገ ተቋም ነው። እናም ህወሃትን የሚያድን ውሳኔ ከኒውዮርክ ይመጣል ብላችሁ ተስፋ የምታደርጉ ጀሌዎቹ ምሽቱን ቀዝቃዛ ውሃ ካጠገባችሁ ባይለይ ይመከራል ” በማለት የውይይቱን ጅማሬና ፍጻሜ አስታውቀው ነበር።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት ውይይቱ ያለአንዳች ስምምነት መበተኑን ሳያስታውቁ በርካታ መረጃ እንዳለና በትግራይ ከፍተኛ የሰብአዊ መበት ጥሰት፣ የጦር ወንጀል ሊሆን የሚችል ተግባርና ተመሳሳይ ወንጀሎች በተለያዩ ሃይሎች መፈጸሙን አመልክተዋል። ገለልተኛ ሙያዊ ተቋም እንዲያጣራ መንግስት ፈቃደኛ እንዲሆን ጠይቀዋል። ሃላፊዋ የመከላከያ ሰራዊትና የማይካድራ ንጹሃን ዜጎች ላይ ስለተፈጸመው ወንጀል ለይተው ያሉት ነገር ግን የለም።

ቀደም ሲል “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ትግራይ ክልል ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ተደራሽነትን ለማሳደግ የወሰዱትን እርምጃ አበረታታለሁ” ሴናተር ጂም ኢንሆፍ መናገራቸው በራሳቸው ይቲውተር ገጽ ላይ መታተሙ የፈጠረው ቅሬታ ሳያንስ፣ ትልቅ ውሳኔ ይወስናል ተብሎ የተጠበቀው የጸጥታው ምክር ቤት ያለአንዳች መግባባት መበተኑ በትህነግ ደጋፊዎች ዘነድ የነበረውን ደስታ አቀዛቅዞታል።

ህወሃት ስልጣን ላይ እያለ ከባድ ህጎች እንዳይጸኑበት ሲከላከሉ የነበሩት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ተወያይተዋል። ወይይታቸው አስከትለው በቲውተራቸው ይህንን ብለው ነበር።

ይህ በንዲህ እንዳለ በሌላ ዜና የአማራ ክልል ላለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ ለተፈጸመው ግፍና የዘር ማጽዳት ወምጀል ካሳ እንደሚገባው አስታውቋል። እነ አብርሃ ደስታ አማራ የትግራይን ክልል ወሯል በሚል ያቀረቡትን ክስ ተከትሎ እንደተደመጠው የአማራ ክልል በተደራጀ መልኩ በህዝብ ላይ የደረሰውን ወነጀል ወደ ህግ ለመውሰድ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

የክልሉ ባለስልጣናት በተለያዩ አጋጣሚዎች ” ካሁን በሁዋላ የአማራ ሕዝብ ድጋሚ ለባርነት ተላልፎ አይሰጥም” ሲሉ ተደምጠዋል። ካሳ እንደሚጠይቁም አስታውቀዋል።

” የአማራ ክልል ብቻ ለትግራይ ህዝብ ችግር አልደረሰም” ሲሉ በፌስ ቡክ ገጻቸው ሌሎችን ብሄሮች ስም ጠርተው ያወደሱት አቶ አብረሃ ደስታ ” የትግራይ ህዝብ የሚጠብቀው ባጣ ጊዜ” ሲሉ ህወሃት ባለመኖሩ ይህ እንደሆነ አስታውቀዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የሆኑት አቶ አብርሃ ከትግራይ ተወሰዱ ያሉዋቸውን ቦታዎች አልዘረዘሩም።

እሳቸው ይህን ባሉ በሰዓታት ውስጥ “ነጭ ጋዜጠኞች” አንድ ሚሊዮን የሚሆን የትግራይ ህዝብ የት እንዳለ እንደማይታወቅ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት እንዳስታወቁ በስፋት ጠቅሰዋል። የአረና የህዝብ ግንኙነት የሆኑት አቶ አንዶም ይህንኑ በማብራራት ለአሜሪካ ሬዲዮ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ከዚ በሁዋላ ነው እንግዲህ የአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍ በመዘርዘር የክልሉ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ” በሃይል የተያዘ ቦታ የለም” ሲሉ ህዝቡ በትግል ነጻ መውጣቱ ይፋ ያደረጉት።

በመጨረሻ ባገኘነው መረጃ የማራ ህዝብ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በማሰብሰብ በዓለም አቀፍም ሆነ የህግ አግባቡ በሚፈቅደው መንገድ የህወሃት መሪዎችን በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመጠየቅ ስራ ተጀምሯል። ነዋሪነታቸው እንግሊዝ የሆኑ የንሄሩ አባል ” በመለፍለፍ ሳይሆን ውጭ ያለው የአማራ ብሄር አባላትና ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተባብረው የውጭ አገር ጠበቃ ልንቀጥር ይገባል” ብለዋል። በሚልዲያ በጁልም እጅግ ሙያዊ የሆነ ማስተባበያና ህወሃትን የሚያጋልጥ መረጃዎችን ማዘጃትና ለውጭው ማበበረሰብ ማሰራጨት ጊዜ የሚሰጠው ትገባር እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

Exit mobile version