Site icon ETHIO12.COM

ዘርና ሃይማኖት ሳይለያየን ለሀገራችን የምንቆምበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን -ፕሮፌሰር አደም ካሚል

ፕሮፌሰር አደም ካሚል እንዳስታወቁት፣ ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ ከመከፋፈል ይልቅ ወደ አንድነት መምጣቷ ያሳሰባቸውና የሀገሪቱ መረጋጋት የቀጠናውን መረጋጋት እንደሚያመጣ የተረዱ ሀገራት እየተፈጠረ ያለውን ህብረትና አንድነት ለመበተን ቀን ከሌት እየሰሩ ነው፡፡

የሀገሪቱ መጠናከር እንደፈለጉ እጃቸውን ለመስደድ ለሚፈልጉ ወገኖች አመቺ እንዳልሆነላቸው ፕሮፌሰር አደም ጠቁመዋል፡፡

ላለፉት 30 ዓመታት ስንከተለው የነበረው የልዩነት ፖለቲካ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን፤ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን፤ አብሮ ከማደግ ይልቅ አብሮ መውደቅን የመረጠ እንደነበር ያመለከቱት ፕሮፌሰር አደም፣ ይህ የፖለቲካ አካሄድ ሀገሪቱን ከውስጥ አልፎ ለውጭ ጠላቶች አሳልፎ እንደሰጣት አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያን መጠንከር የማይሹና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድክመቷን ለሚመኙ አካላት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸው የቆየ መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሰር አደም፣ እነዚህ ሃይሎች እንደገና ይህንን ከፋፋይ ሥርዓት ለመመለስ የሞት ሽረት ትግል እያካሄዱ ነው ብለዋል።

‹‹ቀደም ሲል ሊደፍሩን ወኔ የሌላቸው ሀገራት ጭምር ድንበራችንን በኃይል ለመውረር ችለዋል፤ አንዳንዶቹም ጭራሽ ሀገሪቱን ለማፈራረስ ቆርጠው ተነስተዋል።

በርካታ የውጭ ተቋማትና ሚዲያዎቻቸውም ኢትዮጵያን ለማዳከምና የተጀመረውን የአንድነት መንፈስ ለመበረዝ ሌት ተቀን እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው።

Exit mobile version