Site icon ETHIO12.COM

የሶማሌ ክልል አሁን ለደረሰበት ሰላም፣ልማትና እድገት መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል- አቶ ሙስጠፌ

የሶማሌ ክልል አሁን ለደረሰበት ሰላም፣ልማትና እድገት መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ተናገሩ።

የሶማሌ ክልል ባለፋት በርካታ አመታት በከፍተኛ የፀጥታ ችግር ውስጥ በነበረበት ወቅት የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል የምስራቅ ዕዝ የሰራዊት አመራርና አባላት ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ብለዋል።

ከለውጡ በኋላ በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግርን በፍጥነት በመቆጣጠር ህዝባዊነቱን ያስመሰከረ ሲሆን በዚህም ክልሉ ላይ ይደርስ የነበረውን ኪሳራ መቀነስ ችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

የህወሃት ጁንታ ኢትየጵያን ለመበተን አስቦ በሰራዊቱ ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ቢሰነዝርበትም የህዝብ ልጅ የሆነው ሰራዊት ከደረሰበት ድንገተኛ ጥቃት በፍጥነት አገግሞ በወሰደው የመልሶ ማጥቃት በሁለት ሳምንት ውስጥ ጁንታውን በመደምሰስ ኢትዮጵያን ከተጋረጠባት አደጋ አድኗል ብለዋል፡፡

አቶ ሙስጠፌ የህወሃት ርዝራዦች ቀደም ሲል የዘረጉትን የሴራ ኔትወርክ በመጠቀም ሰራዊቱ ላይ ያልተገባና ከእውነት የራቀ ውሸት እያስተጋቡ ቢሆንም ሰራዊቱ ግን በህዝባዊነቱ ስነ ምግባር ተመራጭ በመሆን የጎረቤት ሃገራትን ጭምር በአስተማማኝ ሁኔታ እያስጠበቀ የሚገኝ ተወዳጅ ሰራዊት ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via FBC

Exit mobile version