👉 ሱዳንን በሚመለከት በዲፕሎማስው ሰፊ ስራ እየሰራን ነው፡፡ ከሱዳን ጋር ጦርነት መጀመር አያስፈልግም ኪሳራ ነው ፤
👉 ሱዳንም አሁን ባለው ሁኔታ ከጎረቤት አገር ጋር ለመዋጋት በሚያስችል ቁመና ላይ አይደለም ያለችው ፡፡ብዙ የውስጥ ችግር አለባት፤
👉 ኢትዮጵያም አሁን ባለው ሁኔታ ከሱዳን ጋር ለመዋጋት ብዙ ችግር አለባት፤ ስለዚህ ጦርነቱ ለሁለታችንም አያስፈልገንም፤
👉 ችግሩን በንግግር፣ በውይይት፣ በድርድር መፍታት ነው የሚያስፈልገው፤ ያ ተጀምሯል፤
👉 ከአጼ ሚኒሊክ ዘመን ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በንግግር ያለጉዳይ ነው፤ በእኛ በኩል በምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚመራ ኮሚቴ በእነሱ በኩልም በሚንስትር የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራበት ነው፤
👉 ላለፈው አንድ አመት ያህል ስራ ስንሰራ ቆይተናል፤ አሁን ይሄ የሕግ ማስከበሩ ስራ ሲጀመር ነው የተቋረጠው፡፡ በዚህ ወቅት እነሱ ወደማይገባ መንገድ ሄዱ፤
👉 እኛ ለዚህ የሰጠነው ምላሽ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ውጊያ አያስፈልግም፤ በውይይትና በድርድር እንፍታው ነው ያልነው፤
👉 ይሄን ስንልም የእኛ አርሶ አደሮች ተፈናቅለዋል፤ ማሳቸው ተቃጥሏል፤ ቤታቸው ተቃጥሏል፤ በደል ደርሶብናል፤ ያም ሆኖ አንዋጋ እያልን ነው፤ ውጊያ ስለማይጠቅመን፤
👉 ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ ሱዳን ከሌሎች ጋ ወዳጅነት ፈጠረች የተባለው ሱዳን ከማንኛውም አገር ጋ ወዳጅ መሆን ትችላለች፤ የኢትዮጵያ ጠላት መሆን ግን አትችልም፤
👉 ሱዳን የሚለው ቃል በአርብኛ እና ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በግሪክኛ አንድ ነው ትርጉሙ፤ አንድ ሕዝብ ነው፤ የትም አገር ሄዳችሁ ሱዳናዊ ብታዩ በአማርኛ ነው የምታወሩት፤
👉 ኢትዮጵያን ከሱዳን መለየት አይቻልም፤ ከማንኛውም አገር ጋ ወዳጅ መሆን ይቻላል፤ ችግር የለውም፡፤ እኛም ከሌሎች አገራት ጋር ወዳጅ መሆን እንችላለን፤ የሱዳን ጠላት መሆን ግን አንችልም፤
👉 በብዙ ነገር አንድ ሕዝቦች ነን፤ ተከባብረንና ተዋድደን የኖርን ወደፊትም አብረን የምንኖር ሕዝቦች ነን፤