Site icon ETHIO12.COM

የጉሙሩክ ስነ ስርአት ሂደቱን ሳይጠብቁከውጭ ሃገር የገቡ 68 ኮንቴነር እቃዎች ተሸጠው ከ82 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተደረገ


በሞጆ ጉሙሩክ ወደብ የጉሙሩክ ስነ ስርአት ሂደቱን ሳይጠብቁ ከውጭ ሃገር የገቡ 68 ኮንቴነር እቃዎች ተሸጠው 82 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ታክስና ቀረጣቸው ገቢ ተደረገ።

በጨረታ ከተወገዱት እቃዎች መካከል ኤሌክትሮኒክስ፣ የፋብሪካ ጥሬ እቃዎችና የግንባታ ግብአቶች የሚገኙበት ሲሆን፥ እቃዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሃገር ገብተው በቀነ ገደባቸው ያልተነሱ ናቸው ተብሏል።

የሞጆ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ የጉሙሩክ ኦፕሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ በንቲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ለእቃዎቹ ባለቤቶች ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ እቃዎቹን ባለማንሳታቸው ተሸጠው ታክስና ቀረጡ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል ብለዋል።

በዚህ መልኩ በአሁኑ ወቅት የጉሙሩክ ስነ ስርአት ሂደቱን ያልጠበቁ 752 ኮንቴነር እቃዎች ከወደቡ የሚነሱበት ቀነ ገደብ በማለፉ በጨረታ ተወግደው ታክስና ቀረጣቸውን ለመንግስት ገቢ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version