Site icon ETHIO12.COM

ዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር pስምምነት ተፈራረመ


የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩት ሶስት ፕሮጀክትች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና ዓለም ባንክ ግሮፕ ምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚ/ር ዲዮን ነው የተፈራረሙት።

የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን አሰጣጥንና ተደራሽነትን ለማሳደግ እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚውል ነው ተብሏል።

የመጀመሪያው የ200 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ የተጎዱ እንተርፕራይይች አዋጭ በሆነ መንግድ እንዲቀጥሉና በንግድ ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ ያግዛልም ተብሏል።

በሀገሪቱ ውስጥ ለሚከናወኑ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ተደራሽነት ለማሳደግ 500 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት የተደረገ ሲሆን በዘርፉ ዘላቂ ፋናይንስ አመራጮችን ለማምጣት የሚያስችል አከባቢን ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።

ከዚህ ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ የሚውለው በግሉ ዘርፍ በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ እና አቅርቦት ላይ ተሳትፎ እንዲኖረው ለማስቻል ነው ተብሏል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Exit mobile version