Site icon ETHIO12.COM

አማራ ክልል የአንድ አካባቢ ባለህብቶች የሚመሩት የተቀናጀ መዋቅር ተለየ፤ አብን ሃላፊነት ወስዶ ” ምረጡኝ”አለ

በአማራ ክልል የአንድ አካባቢ ባለሃብቶች ናቸው የተባሉ ከጀርባ ሆነው የሚመሩት የተቀናጀ አደረጃጀት መዋቅር መያዙ ተሰማ። አብን ” ካርድ ውሰዱ፤ ምርጫ እወዳደራለሁ” ሲል የምረጡኝ ጥሪ አቀረበ። የአምራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከቀናት በፊት” ባለባቶች፣ ነጋዴዎች እጃችሁን አንሱ” ብለው ነበር።

በአማራ ክልል የተካሄዱና እየተካሄዱ ያሉ ሰላማዊ ሰልፎች ፍትሃዊና ተደጋጋሚ ጥቃቶች የፈጠሩት ቢሆንም ቀደም ሲል ባለሃብቶች የሚመሩት መዋቅር አጋጣሚውን እየተጠቀመበት መሆኑንን የክልሉ መንግስት አረጋግጧል። የፌደራሉ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ደግሞ ሙሉ አደረጃጀቱን ለይቶ ከነሙሉ መዋቅሩ እጁ እንዳስገባ የመረጃ ሰዎቻችን አስታውቀዋል።

ቀደም ብለው የተደራጁት እነዚህ ክፍሎች አደረጃጀታቸው በሚዲያና ሚዲያ ውስጥ የሚሰሩ ፣ ቤተ ክርስቲያን፣ የመንግስት ሃላፊዎች፣ በአክቲቪስት ስም የሚንቀሳቀሱ አካላት ሲሆን መዋቅሩ ፊት ለፊት ከሚታወቁት በተጨማሪ ሌሎችንም ያካተተ የውጭ አገር ትሥሥር አላቸው። አገር ውስጥና በውጭ አገር የተቀናጁ ተደራጅተው እንደሚነቀሳቀሱ በስፋት ቢነገርም ደህንነት የለያቸው ክፍሎችና አመራሮች በርካታ አዳዲስና ስማቸው የማይታወቅ መሆኑ ታውቋል።



በአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት እዳ አለባቸው የሚባሉት ቀደም ሲል ” ልማታዊ” የሚባሉት ባለሃብቶች እንዲህ ያለውን አካሄድ ለምን እንደመረጡ የመረጃው ምንጮች ለማብራራት አልፈለጉም። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ክፍሎች መካከል ቀደም ሲል ከተፈጸመው የአማራ ክልል መሪዎች ግድያ ጋር የሚነካኩ እንዳሉ የሚያሳይ መረጃ መገነቱን ፍንጭ ሰጥተዋል። ስም ዝርዝራቸውን እንደማይገልጹ ጠቁመው ” ላባቸውን ጠብ አድርገው ለአገራቸው የሚሰሩትንም የሚያስፈራሩ የማፍያ ይዘት ያላቸው ይገኙበታል” ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስት ከያዘው መዋቅር ውስጥ ይመደብ አይመደብ ባይታወቅም፣ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን በመክዳትና አሉ የሚባሉ ጀነራሎቿን በማስፈጀት የሚወነጀሉት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ በመረጃ ቴሊቪዥን ቀርበው ” መንግስት መገልበጥ አለብን፣ ወለጋና ሊሎች ቦታዎችን እናስመልሳለን” ሲሉ የተደራጀ እንቅስቃሴ መኖሩን ማረጋገጣቸው ይታወሳል። በአዋጅ ክልልና የክልል አስተዳደሮች፣ እንዲሁም የክልል ፓርቲዎች መፍርስ እንዳለባቸው የሚያስገድድ ረቂቅ አዘጋጅተው ውድቅ የተደረጋቸው ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ በገሃድ መንግስት እንዲወገድ ነው ጥሪ ያቀረቡት።

ሻለቃው ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ” ወለጋን እናስመልሳለን” የሚሉ በትክክለኛ ስማቸው የማይታወቁና ሌሎች በማህበራዊ ገጾች ” ወለጋ የኛ ነው” በሚል በቅርቡ እንደሚያስመልሱ እየገለጹ ነው። ይህ ወደ ትርምስ የሚነዳ ጥሪ ለምን ዛሬ ላይ አስፈላጊ ሊሆን እንደቻለ የበርካቶች ጥያቄ ሆኗል። “እንዲህ ያለውን ጥሪ ለማስተላለፍ የሚዲያ ችግር የለባቸውም፣ ጥሪውን ተከትሎ ህዝብ ሲጫረስ ሚዲያዎቹ ተጨማሪ ገቢ አላቸው” ሲሉ አቶ አያልነህ ሃይሌ በሃዘኔታ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከቀናት በፊት ሕዝብ ተቃውሞ የሰማበትን ስለፍ ጨዋነት አድንቀውና ድጋፍ እንደሚሰጡ አረጋግጠው በሰጡት መግለጫ ” የንጽሃንን እልቂት መነገጃ ማድረግ ይሳፍራል” ሲሉ ተናግረው ነበር። በዚሁ መግለጫቸው ” ባለባቶችና ነጋዴዎች እጃችሁን አንሱ” ሲሉ በጥቅሉ አስታውቀው ነበር። የሕግ ማስከበር ስራም እንደሚሰራ ማስታወቃቸውም አይዘነጋም።

ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ለወጣቶች ያቀረቡትን “የመንግስት ይለውጥ፣ አራት ኪሎ ግቡ፣ ጩሁ፣ ተቃወሙ፣ በዋና ዋና ከተሞች ሰልፉ ይቀጣጠል” ጥያቄ ተንተርሶ የምስራቅና የደቡብ አጎራባች ክልሎች አንድ የሚያድረጋቸውና ጸጥታቸውን አስጠብቀው የሚኖሩበትን ስትራቴጂ ነድፈው ለማጽደቅ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። አፋር፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ክልል፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል አንድ ላይ ሆነው በመከሩበት ስብሰባ ” መንግስት ይቀየር” የሚለውን ጥሪ ” ወግድ” የማለት ያህል አስተያየት ሲሰጡ ተድምጧል። የህብረቱ መመስረት በራሱ ትርጉም ሰፊ እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ስብሰባውን የመንግስት መገናኛዎች ናቸው የዘገቡት።

በሌላ ዜና አብን በክልሉ ለተደረጉ ሰልፎች በሙሉ ሃላፊነት ወስዶ ” አመስግናለሁ” ካለ በሁዋላ ” አብን በምርጫ አይሳተፍም” የሚለው ሃሰት በመሆኑ ሕዝቡ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ ጠይቋል። አብን የምርጫ ክርክር ረግጦ መውጣቱ አይዘነጋም። በአንዳንድ ሰልፎች ላይ የሌሎች ፓርቲዎች ባነሮች ሲሰባበሩና ሲቀዳደዱ የሚያሳይ መረጃ በመቅረቡ ለሰለፎቹ ባለቤትነቱን ከውሰደ ምርጫ ቦርድ በስነስርዓ ደንቡ መሰረት ሊጠይቀው እንደሚችል ተሰምቷል። አብን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ” አሸባሪ” ሲል መፈረጁ አይዘነጋም።


Exit mobile version