ETHIO12.COM

እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ “ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው”

ኢትዮጵያን ለመብላት ዘንዶዎቹ ከያለበት ተነስተዋል። በየአቅጣጫው ወረውናል። ከመሃል ተቀምጠው አብረውን እየበሉና እየጠጡ ያሳርዱናል። ይቦረቡሩናል። ምን እንዳደረግናቸው ሳይገባን ከልጅነት እስከ እውቀት ሊያጠፉን እንደባዘኑ ዛሬ ላይ ደረስን። ሲዘርፉ፣ ሲገርፉ፣ ቶርቸር ሲያደርጉ፣ ጥፍር ሲነቅሉ፣ በግልና በጅምላ ነጹሃንን ሲጨፈጭፉ ማንም ጠያቂ አልነበረም።

” እኛ ወንዶች ነን ግድየለም። ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የተፈጸመው ግፍና ወንጀል ተድበሰበሰ። ጡታቸውን የተቆረጡ አሉ። የተደፈሩና የተዘረፉ፣ በረሃብ የተቀጡ አሉ። መቀሌ የንሣት ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ አጉረዋቸው የፈጸሙትን አምላክ ይየው” ያለው በተዓምር የተረፈው የመከላከያ አባል ነው። ዛሬም ግዳጅ ላይ ነው። ይህን ጉዳይ የሚሰማው፣ የሚመለከተውና የሚከታተለው አካል የለም። ለምን? “ኢትዮጵያ” የሚሉ ዜጎች በመሆናቸው ብቻ!!


“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቦታ ተወስነው መኖር የማይችሉ አርብቶ አደሮች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች (ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን) ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ይህ የትህነግ ወንጀል ነው ግን ዝም ተባለ ሙሉውን ያንብቡ እነዚህ ዜጎች ዜጋ አይደሉም


የእንግሊዝ ፓርላማ ኢትዮጵያን በጄኖሳይድ ለመክሰስ ዳር ዳር እያለ ነው። ከዙሪያዋ አገሮች ጋር ተባብሮ ይህንኑ ዓላማውን ለማሳካት እየሰራ መሆኑንን ይፋ አድርጓል። በትግራይ ሕዝብ የሰብአዊ ድጋፍና ማህበራዊ ምስቅልቅል ውስጥ ተመሽጎ ኢትዮጵያ ላይ የዘመተው የትህነግ ፈጣሪና አሳዳጊ የንግሊዝ መንግስት ይህንኑ እቅዱን በሚቀልባቸው ሚዲያዎቹ አማካይነት ነግሮናል።

ለመሆኑ እንግሊዝ የምትባል አገር ስለ ጂኖሳይድ የማውራት የሞራል ልዕልና አላትን?

Related stories   ሕወሃት 7 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያነት ማዋል እንዳይችልና እንዳያሸሽ ተደረገ

ቢቢሲ የUK ፓርላማ በትግራይ ክልል ጉዳይ መክሮ ሪፖርት ማውጣቱን አውጇል። ለዚሁ ተግባር የተቋቋመው ቢቢሲ እንዳለው መንግሥት በክልሉ ያለውን ግጭት ለማሰቆም በተቻለው ሁሉ የዲፕሎማሲ አማራጮችን ይጠቀማል።

በትግራይ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ቁልፍ ምክንያቱ በክልሉ ያለው ግጭት ነው ብሏል። በክልሉ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የሰብዓዊ ርዳታ ለማቅረብ የሚደረውን ጥረት ማደናቀፉን አክሎ ገልጿል።

የዩኬ መንግሥት ግጭቱ አንዲቆም በተቻለው መጠን ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን መጠቀም አለበት ሲል ድምዳሜ ሰጥቷል። ግጭት ለማስቆም የዩኬ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት፣ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ በግጭቱ ተሳታፊ ከሆኑ አካላት እና ከጎረቤት አገራት ጋር አብሮ መስራት አለበት ብሏል ፓርላማው።

ፓርላማው በሪፖርቱ ላይ በተለይ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የተቃጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እጅጉን እንዳሳዘነው ገልጾ፤ ወንጀሉ ተመርምሮ ጥፋተኞች ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብሏል።

በትግራይ የተፈጸሙ ወንጀሎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ጥፋተኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ የዩኬ መንግሥት ትብብር ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል።

ዜጎችን ከጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች መጠበቅ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነት መሆኑን የብሪታኒያ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥትን ማሳሰብ አለባት ሲል ፓርላማው ምክረ ሃሳቡን ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ እርምጃ መውሰድ ቢሳነው፤ የዩኬ መንግሥት የተመድ የ ‘ጄኖሳይድ ኮንቬንሽን’ ን መሠረት ባደረገ መልኩ ኃላፊነት የመውሰድ ግዴታ እንዳለበት ማወቅ አለበት ብሏል ፓርላማው።

ለትግራይ ምስኪን ህዝብ የሚታሰቡ መልካም ነገሮች ካሉ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ይሁን እንጂ  ከዚህ በላይ የሰፈረው የቢቢሲ ዘገባ መረዳት እንደሚቻለው እንግሊዝን የምትባለዋ አገር ኢትዮጵያ ላይ ያላትን ሴራ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ጋር ምንድን ነው የምትመክረው? ጎረቤት አገሮች ስትል እየወረረችንና “ቢኒሻንጉል የግል ሃብቴ ነው” የምትለዋ፣ የትህነግና የቤኒሻንጉልን አማጺ በሚል የምታሰለጥነዋ ሱዳን? ወይስ ኢትዮጵያ ላይ በጸጥታው ምክር ቤት ጣቷን የቀሰረችው የቀድሞ ግዛቷ ኬንያ?

Related stories   አማራ ክልል የአንድ አካባቢ ባለህብቶች የሚመሩት የተቀናጀ መዋቅር ተለየ፤ አብን ሃላፊነት ወስዶ ” ምረጡኝ”አለ

ለመሆኑ ማይካድራ ላይ ስለተጨፈጨፉትና ግልጽ መረጃ ስለቀረበበት ጉዳይ ለምን አይነገርም? ይህ የትህነግን ጭራቅነት የሚያሳይ ጭፍጨፋ ስለምን ይፈራል? ከእንግሊዝ የመጡት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የማይካድራውን ጭፍጨፋ በይፋ የተተናቀቀውን ሪፖርት የማያቀርቡት ለምንድን ነው?


ዶ/ር ዳንኤል- በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ የለም

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጋዜጠኞች መታሰር እንዳሳሰበው ገለፀ - BBC News አማርኛ

በማይካድራ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ በግልጽ አካባቢውን ሲያስተዳድር፣ በነበረው ወይም በወቅቱ ስራ ላይ በነበረው ሃይል ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎችና ሳምሪ በሚባል የወጣቶች ቡድን ወይም ኢመደበና አደረጃጀት እንደተፈጸመ በመጀመሪያ ደረጃ ኮሚሽናቸው ሪፖርት ማድረጉን በግልጽ ያምናሉ። ሲይብራሩ ግን ሪፖርቱ በሰዎች ዘንዳ ማለታቸው ነው ” ከዛ አልፎ ሲተረጉሙት ከህወሃት መመሪያ በቀጥታ ተሰጥቷቸው ነው …” በሚል ነው።  በትርጉም እዛ ደረጃ እንደወሰዱት ገልጸው … ” እኛ ግን እንደሱ አንሰራም”  እንግዲህ ይህ መሸፋፈን ነው ኢትዮጵያን ዋጋ እያስከፈለ ያለው። አካሄዱ የገባቸው በርካቶች ድርጊቱን” ክህደት” እያሉት ነው። ምክንያቱም ሪፖርቱ ይፋ ቢሆንና ነገሮች ይቀያየሩ ነበርና 

ኮሚሽነሩ አፍነው የያዙት የማይካድራ ጭፍጨፋ ጄኖሳይድ አይደለም? ፎቶው ከብዙ በጥቂቱ

አሁን ላይ እንደሚሰማው ዶክተሩ ዝምታን የመረጡት ሆን ብለው ነው። የእነሱ በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን የተጨፈጨፉበትና የታረዱበትን ገሃድ  የጄኖሳይድ ወንጀል ብሎ ላለመጥራት አዳፍነው ለመያዛቸው ምክንያት የማይሰጡት ዶክተሩ፣ አቋማቸው ከኖሩበት እንግሊዝ ጋር መመሳሰሉ አነጋጋሪ እየሆነ ነው።

ቀድሞ የታወቀውና በሙሉ መረጃ የተጠናቀቀውን ምርመራ ይፋ ቢያደርጉ ዓለም ሚዛኑን እንዲጠብቅና ቢያንስ ሁሉም ወንጀሎች በእኩል ደረጃ እንዲጣሩ ይደረግ እንደነበር ቅሬታቸውን የሚያሰሙ ይናገራሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የዶክተር ዳንኤል በጉዳዩ ላይ ሆን ብለው ዳተኛ መሆናቸው የኢትዮጵያን መከራ አብዝቶታል። አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ፣ ፖለቲከኛ የሚባሉት አካላት እዚህ ጉዳይ ላይ ከመረበባረብና ቻና ከመፍጠር ይልቅ በተራ ጉዳይ ሳንቲም ላይ ያተኮረ ስራ መስራታቸው ሃዘኑን እጥፍ አድርጎታል።


የሰብአዊ መብት ኮሚሽን “የግፍ ደረጃ መዳቢ” – የማይካድራ ምርመራ ላይ ደባ እየተሰራ መሆኑ ተሰማ፤ ኮሚሽኑ ምላሽ ከለከለ


ዛሬ ኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ አድብተው እየሰሩ ያሉት አገራት እንግሊዝን ጨምሮ ሃሳባቸው ” ያልተመረጠ መንግስት” በሚል ክስ ለመመስረት እንዲያመቻቸው ነው። ትህነግ ከምርጫ ቦርድ ማዕቀፍ በመውጣት የጨረቃ ምርጫ እንዲያደርግ ሲገፉ የነበሩ አገሮች ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ እንዳያደርግ እየተጫኑት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዛሬ የንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ኢትዮጵያን እየሰቀሏት መሆኑን ለሚገባቸው አስታውቀዋል። እንዲህ ያላሉ

.. እውነቱን የያዙ ሰዎች ጥቂት ሆኑ። ጥቂት ብቻ ሳይሆን በሐሰተኞችና በሽብር ዜና ነዥዎች ድምጽ ተዋጡ። እውነት መንምና የምትበጠስ መሰለች። አንዳንዶችም ለሦስት ዓመታት ከክርስቶስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ያዩትንና የሰሙትን ሁሉ ካዱት። ተታልለን ነበር ብለው አመኑ። ብዙዎች የሐሰት ምስክሮች ሆነው መጡ። በደስታ የሰከሩበትንና በነጻነት እልል ያሉበትን ወቅት ዘነጉት። በዕለተ ዓርብ አይሁድና ሮማውያን ያሳዩት ጭካኔ የብዙዎችን ልብ ሰለበው። ‹ከክርስቶስ ጋር ሲተባበር የተገኘ ቤቱ ይበረበራል፤ ሀብቱ ይመዘበራል፤ አንገቱ ይቆረጣል› ተብሎ የታወጀው ዐዋጅ የብዙዎችን ሐሞት አፈሰሰው። ብዙዎች መካዳቸው ብቻ ሳይሆን፤ እውነቱን የተቀበሉት ጥቂቶች እንኳን በአደባባይ ለመመስከር ፈሩ። ቅዝምዝሙንና ክፉውን ቀን ከመጋፈጥ ይልቅ ጎንበስ ብለው ማሳለፍን መረጡ። ጎርፉ እስኪያልፍ እንደ ወንዝ ዳር ቄጤማ ድምጽ አጥፍተው መነጠፍን ወደዱ።

ተግራይ ንጹህ ዜጋ ከደረሰበት ቀውስ እንዲወጣ፣ ፍትህ ሊያገኝ እንደሚገባ፣ በተበደለው መጠን አጥፊዎች ሊጠየቁ እንደሚገባ ክርከር የለውም። ሌሎች ላይ የተፈጸመው ግፍም እንደዛው።

ኢትዮጵያዊያን እየሆነ ያለውን አስቡ። አሁን ተመካከሩ። አግራችሁን አድኑ። ዘንዶዎቹ ዙሪያውን ሊበሉን እየሰሩ ነው። ልብ ያለ ልብ ይበል

በመጨረሻም 

ነብሷን ይማረውና ዳያና ባሏን ልዑል ቻልርልስን ትታ ከዶዲ አልፋያድ ጋር የፍቅር ግንኙነት መሰረተች። ቻርልስም በፊናው ከካሚላ ጋር ፍቅር ላይ ነበር። ይህን የተረዳቸው ዳያና “ደህና ሁን” ብላው ተፋታችው። በዚሁ ውሳኔዋ ቀጣይዋ የUK ንግሥት የመሆን ዕድልዋን አሽቀንጥራ ጣለችው።። ቢቢሲም ሐዘን ተቀመጠ፤ የ24 ሰዓት ፕሮግራም አድርጎ ሃዘኑንን ሲያሰራጭ ውሎ አደረ። ቢቢሲ  “በዚህ ውሳኔሽ ቀጣይዋ ንግሥት የመሆን ዕድልሽን ነው መቀመቅ የከተትሽው” የሚል ይዘት ያለው  ጥያቄ አቀረበላት። እሷም ስትመል “በሰዎች ልብ ውስጥ ንግሥት ሆኜ መኖር ነው የምፈልገው” I want to be a queen in people’s hearts” ነበር ያለችው። ከእስከ አሁንም ነች። ወደፊትም ሆና ትኖራች።

Exit mobile version