Site icon ETHIO12.COM

ይናገር ደሴ “እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ያለው ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ጉዳይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም”

“እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ያለው ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ጉዳይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም” ሲሉ ዶክተር ይናገር ደሴ አስታወቁ። ሴራውን የማይታወቅና የተሸፈነ እንዳልሆነም አመልክተዋል። ጥሪም አስተላለፈዋል።

በከረረ የፖለቲካ ንግግር የማይታወቁት የብሄራዊ ባንክ ገዢ የሆኑት ዶክተር ይናገር በአዲስ አበባ ብልጽግና የፌስ ቡክ አምድ ” አላልንም ወይ ያሰኛል” ሲሉ አስቅድሞ ሩጫው እንደሚታወቅ አመላክተዋል። አያዘውም ” ኢትዮጵያን አትንኩ” በማለት አሜሪካ በምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመቻቸውን ፊልትማንን አካሄድ ” ለስለስ ብሎ እጁን ለማስገባትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልዕኮውን ለማሳካት የነደፈውን አቀራረብ ያልተረዳን አላዋቂዎች አድርጎን ከሆነ የዋሁ እሱ ራሱና አጋፋሪዎቹ ናቸው” ብለዋል።

ሲጀመር ጀምሮ የአሜሪካ አቋም እንደሚታወቅ ለመጠቆም “አላልንም ወይ ያሠኛል! ” ሲሉ በአገራቸው ላይ የተቃጣውን ደባ ለማውገዝ ዶክተር ይናገር ቀዳሚ ባለስልጣን ሆነዋል።

በምረጡኝ ዘመቻቸው “ኢትዮጵያን አትንኩ!ብልፅግና የአባቶቹ ትውልድ ነው! ፌልትማን ለስለስ ብሎ እጁን ለማስገባትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልዕኮውን ለማሳካት የነደፈውን አቀራረብ ያልተረዳን አላዋቂዎች አድርጎን ከሆነ የዋሁ እሱ ራሱና አጋፋሪዎቹ ናቸው” በሚል የባክን ገዢው አምርረው ተቃውሞ አሰምተዋል። … የዋህ በራሱ ቀልድ ሊፈነድቅ እንደሚችልም አመላክተዋል።

“በፌልት ማንና በአሜሪካ እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ነው” ሲሉ በአዲስ አበባ አስተዳደር ብልጽግና ፌስቡክ ገጽ ላይ ይፋ ተቃውሞ ያሰሙት ዶክተር ይናገር፣ “ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም የአባቶቻችን ልጆች የእናቶቻችን ፍሬዎች ነንና” ሲሉ የኢትዮጵያን ጀግንነት አውስተዋል። ይህ ጉዳይ የአንድ ፓርቲ ወይም የመንግስት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የመላው ብሔር ብሔረሰቦችና ኢትዮጵያዊውያን የህልውና ጉዳይ መሆኑንንም አመልክተዋል።

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

“ብልፅግና ደግሞ የትውልድ ቅብብሎሽን የሚያስቀጥል መልካሙን የአባቶቹን አደራ የሚያስቀጥል ባለአደራ ፓርቲ ነው” ካሉ በሁዋላ “ኢትዮጵያን ሊበታትኗት እያሴሩ ያሉትን አካላት፤ ኢትዮጵያዊያን በጊዜያዊ የውስጥ ችግሮቻችን ሳንያዝ ጣሊያንን ባንበረከክንበት ያ ታላቅ የሀገር ፍቅር ክንዳችን ዛሬም ሳንለያይ ባንድነት የውጭ ኃይላትን ሴራ በህብረትና በአንድነት መመከት እችላለን” ብለዋል።

”እኔ እያለሁና እያየሁ ጠላቶቻችን ሀገሬን በላዬ አያፈርሱም እኔም የአባቶቼ ልጅ ነኝ ” የሚል ትውልድ ዛሬም እንዳለ ዶክተር ይናገር ገልጸዋል። “ሀገር ሲኖረን የውስጥ ችግሮቻችንን ተነቃቅፈንም ተመካክረንም ማረም እንችላለን” ሲሉ ጊዜው ልዩነት የሚጎላበት እንዳልሆነ አመልክተዋል። ” ኢትዮጵያ ማለት ከ80 በላይ ብሔረሰቦች ድምር ውጤት ነች። አትሞክሩት ! አላልንም ወይ ያሰኛል! ታሪክ መምህር ነው!ፀሐዬ ዮሐንስ ‘ማን እንደእናት ማን እንደሀገር’ እንዳለው ቅስቀሳው ሀገርን መከላከል ለሆነው ብቻ ጆሮዬን እሠጣለሁ በሉ” ሲሉ ሕዝብ የአገሩን ጉዳይ ነቅቶ ሊከታተል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

“አገራችን ከምንም ነገር በላይ ነች። ምሁራን ወገኖች አገራችንን በድፍረት እንከላከል።እንገናኝና የሀገራችንን ምሶሶ በምናጠናክርበት ጉዳይ አብረን እንምከር ! ብልፅግናን እንምረጥ ሃገራችንን እንደሁልጊዜውም በጋራ እከላከል” ሲሉም እግረ መንገዳቸውን ድርጅታቸው እንዲመረጥ ጥሪ አቅርበዋል።

Exit mobile version