Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ-ህግ የማይሆን፣ አስገዳጅነትን የማያካትት ” ቀ.ው” ነው

አንቶኒ ብሊንከን ይፋ ያደረጉት የማዕቀብ ዜና ውሳኔ እንጂ ህግ አይደለም። ስሙም  ቀላል ውሳኔዎች ወይም ( ቀ.ው) (Simple Resolution ወይም S. Res.) የሚባለው ነው። ከአሜሪካ ሕግ አወጣጥና አተገባበር አኳያ “ቀላል ውሳኔዎች፡ Simple Resolution ( S. Res.) አስገዳጅ አይደሉም። በፕሬዚዳንቱ ፊርማ የሚጸናም አይደለም። ሕግ የማይሆን፣ ለተግባራዊነቱ የማያስገድድ፣ በአንደኛው ምክርቤት ብቻ የሚወሰን፣ ዓይነት ነው።  የጥቂት ሰዎች ውሳኔ እንጂ ሕግ አይደለም። 

Simple resolutions are designated H.Res. and S.Res., followed by a number. A simple resolution addresses matters entirely within the prerogative of one house, such as revising the standing rules of one Chamber. Simple resolutions are also used to express the sentiments of a single house, such as offering condolences to the family of a deceased member of Congress, or it may give “advice” on foreign policy or other executive business. Simple resolutions do not require the approval of the other house nor the signature of the president, and they do not have the force of law.

መረጃውን ከምንጩ senate.gov ላይ ያንብቡ

“ለምሳሌ ለቅሶ ሲኖር ማለትም አንድ የምክርቤት አባል ዘመድ ወይም ቤተሰብ ሲሞት ለቅሶ ለመድረስ ወይም የሀዘን መልዕክት ለማስተላለፍ፤ የሥራ አስፈጻሚውን ሥራ አስመልክቶ ወይም የውጪ ፖሊሲ በተመለከተ “ምክር” ለመስጠት የሚወጣ ውሳኔ ነው። ይህ ቀላል ውሳኔ የሚባለው የሌላኛውን ምክርቤት ድጋፍና ውሳኔ የሚያስፈልገው አይደለም። እንደ ሕግ የማይቆጠር ስለሆነ እንዲሁም ለዚያ የበቃ ሰላልሆነ ለፕሬዚዳንቱም እንዲፈርሙበት የሚቀርብ አይደለም። እንደ ሕግ የሚደነገግ፤ የሚጸና፣ እንዲተገበር የሚያስገድድ አይደለም” ሲል ህጉን ውሳኔው ምን ማለት እንደሆነ የአሜሪካ ሴናት ድረገ ገጽ ያስረዳል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋ ያደረጉት የጉዞ፣ የኢኮኖሚና የደህንነት ማዕቀብ ለሴኔት ያልቀረበና በዚህ መልኩ በተወሰኑ የሃሳቡ ደጋፊዎችና ህግ አስፈጻሚዎች ተዘጋጅቶ እንደ “ለቅሶ ሃዘን መልዕክት ” በድብቅ የተወሰነ ውሳኔ ነው።

“በትህነግና በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ታስቦ የነበረው የሰላም አስከባሪ ጦር እንዲሰማራ ነበር” ሲሉ አንድ ዲፕሎማት ለኢትዮ 12 አስታውቀዋል። እኚሁ ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት፣ የጸጥታው ምክር ቤት ይህን ሃሳብ እንደማይቀበለው ገልጾ ጉዳዩን ላይከፈት ስለዘጋው አሜሪካ አሁን ይፋ ወዳደረቸው የቀላል ውሳኔ ማዕቀብ ሃሳብ መጥታለች።

“ለጊዜው ውሳኔው እንዴት እንደተዘጋጀ በናውቀም እንለፈው” ሲሉ ሴናተን ጂም ኢንሆፍን በምሳሌነት ያነሱት ዲፕሎማቱ፣ ውሳኔው በሴኔት ደረጃ ቢቀርብ ውድቅ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ስለሚረዱ ለውሳኔው ዓይነት በተሰጠው ስምና ክብደት ደረጃ መወሰናቸውን አመልክተዋል።

ታዋቂው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል እና የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማእቀብ እንደሚቃወሙ በቲውተር ገጻቸው ሲያስታውቁ በዝርዝር አይግለጹት እንጂ አንዱ መነሻቸው ይህ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል።

የአሜሪካን ሴኔት የጦር አገልግሎት ኮሚቴ አባል የኾኑት ሴናተር ጂም፦«የባይደንን አስተዳደር ጠንካራ የቪዛ እገዳ እቃወማለሁ» ብለዋል። አያይዘውም «ግጭቶችን ለማስወገድ እየደከመች ላለችው ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የእኛ ርዳታ ነው። እንዲህ ያለ ድርጊት ወደ ሰላማዊ መፍትሄ ለማምራት አይበጀንም» ሲሉ ምክንያታቸውን አመልክተዋል።

ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ኤች አር 2003 የተሰኘውን ህግ እንዳይጸድቅ ያደረጉ ነበሩው። ህጉ የዴምክራሲ ነክ ጉዳዮችን ኢህአዴግ እንዲያሟላ የሚጠይቀው ነበር። ህጉ በአብዛኞች ተደግፎ የነበረ ቢሆንም እሳቸው በመቃወማቸው ለምክክር እንኳን ሳይደርስ ነው የተጨናገፈው። ያለፈውን በመርሳት ዛሬ በገሃድ ኢትዮጵያን ለመታደግ ሴናተሩ ላበረከቱት ተግባር ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋናቸውን እንዲያጎርፉላቸውም እግረመንገዳቸውን ጥሪ አቅረበዋል። በርካታ ጉዳዮች ሊቀያየሩ እንደሚችሉም አመለክተዋል።

አንጋፋው አሜሪካዊ ሴናተር በረዥም ጊዜ ወታደራዊ አመራርነት ይታወቃሉ። በዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስቴር ውስጥም በረዥም ጊዜ አገልግሎታቸው ስማቸው ይነሳል። ከብሔራዊ መከላከያ ኢንዱስትሪ ማኅበር በቅርቡ የአይዘንአወር ሽልማት ስለመቀበላቸው የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ሴናተሩ ቀደም ሲል ምን አደረጉ? – ለትውስታ ከጎልጉል

ሴናተሩ ከኢትዮጵያዊት ልጅ ልጃቸው ጋር (ፎቶ ምንጭ)

ቀደም ሲል HR 2003 በመባል የሚታወቅ ረቂቅ ሕግ በአሜሪካ ምክር ቤት ወጥቶ ነበር። ይህ ረቂቅ ሕግ በርካታ መሰናክሎችን አልፎ ድምጽ ወደመስጠቱ መስመር እየሄደ ባለበት ወቅት ያከሸፉት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ መሆናቸው ይታወሳል።

ልጃቸው ከኢትዮጵያ አንዲት እትብቷ ሳይቆረጥ ተጥላ የነበረች ህጻን ልጅ በጉዲፈቻነት በማሳደግ የጥቁር የልጅ ልጅ እንደሆኑ በኩራት ይናገራሉ። በአማካይ በዓመት ሁለት ጊዜ ወደ አፍሪካ እንደሚጓዙ የሚነገርላቸው ኢንሆፍ ጉዟቸው ከሃይማኖት ጋር የተያያዘና ለአፍሪካ ልዩ ትኩረት ስላላቸው እንደሆነ ይናገራሉ። እኤአ ከ1998 እስከ 2008 ባሉት አስር ዓመታት ቢያንስ 20 ጊዜ ወደ አፍሪካ በመጓዝ ከማንኛውም የአሜሪካ ሴናተር ቀዳሚ ናቸው የሚባልላቸው ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለጉዟቸው ወታደራዊ አውሮጵላን መጠቀማቸውና እጅግ በርካታ የመንግሥት ገንዘብ ለጉዞ

በተመሳሳይ ዜና ኢትዮጵያ ተመሳሳይ እርምጃ ልትወሰድ እንደምትችል አስታውቃለች

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ላይ የጣለውን የቪዛ እገዳ የሚያፀድቀው ከሆነ፣ ኢትዮጵያም በምላሹ የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ የሚያደርግ ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ፣ አንድ ስማቸው ያልተገለፀ፣ የኢትዮጵያ የዲፕሎማት አመራር ለአልጀዚራ ገለፁ::

አልጀዚራ ከኢትዮጵያ እንደዘገበው ከሆነ አሜሪካ በኢትዮጵያውያ የመንግስት ባለስልጣኖች ላይ ያወጣችው የቪዛ ማዕቀብ ተግባራዊ ካደረገች፣ ኢትዮጵያም የምትወሰደው እርምጃ ተመሳሳይ የቪዛ እገደ ነው።

“የቪዛ እገዳው የአሜሪካ ባለስልጣናት ብቻ የሚመለከት አይደለም” ያሉት ዲፕሎማቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትንና ሰራተኞችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሌሎች ድርጅቶች የሚሰሩ አሜሪካኖችን እንደሚጨምር ይፋ አድረገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በመሆን፣ ሽብርተኝነት ለመዋጋት ወደሶማሊያ የላከቻቸውን ወታደሮቿን ለመመለስ በሂደቱ ላይ እያጠናች መሆኗን አምባሳደሩ ለአልጀዚራ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ከሱማሌ በመቀጠል በመላው አፍሪካ ከአሜሪካ ጋር በተረደጉ ስምምነቶች ሰላም ለማስከበር የላከቻቸውን ወታደሯቿን ትመልሳለች ነው ያሉት አምባሳደሩ። የሚመለሱ ወታደሮችን በተመከለተ በተመድ ስምምነት መሰረት የተላኩትን እንደማይመለከት አልጃዚራ ሃላፊውን ጠቅሶ ዘግቧል።


Exit mobile version