ETHIO12.COM

ወስዋሹ ድርጅት-በድል ስሜት”ሩጫዬን ጨረስኩ” አለ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ ተቃረኑ

ዶ/ር ካርል ቮን

የማዕቀቡ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የትህነግ ዋና ሎቢስት ደስታቸውን ሲገልጹ፣ አቶ ጌታቸው ” ማዕቀቡ ተጣለ አልተጣለ ኢሳያስንና አብይን እንፈነቅላቸዋለን” ማለታቸው አስገርሟል።

“የተሰጠን ተልእኮ በትግራይ ውስጥ ስለሚፈጸመው ጭካኔ ግንዛቤን ማሳደግ ነበር። በጠነከረ ቋንቋ ግፊት አድርገን አር.ኤስ 97 ማዕቀብ እንዲወሰን አድረገናል።ሁሉም ተሳክቷል። አሁን የቤት ስራችን ተጠናቋል። በዚህ ጉዳይ ውስወሳ ማድረግን ዳግም አንመለስበትም። ትግራይን ሆነን መናገራችንን ግን እንቀጥላለን” ይላል የወስዋሽ ድርጅቱ የቲውተር መልዕክት። በተመሳሳይ ቲዊት ይኸው ወስዋሽ ” እናመስግናለን ” ሲል ጆ ባይደንን እድሜና ጤና ተመኝቷል። ለሌላ ተከታታይ ውሳኔዎች እየሰራ መሆኑንንም አመልክቷል።

von Batton Montague york በምዝገባ ቁጥር 44924 የተሰነደ ህጋዊ ወስዋሽ ድርጅት ነው። ከድረገጹ በተወሰደው ምስሉ እንደሚታየው የዚሁ ወስዋሽ ድርጅት የገበያ ደንበኛ (Tigray center for information and communication) የትግራይ የመረጃና የኮሙኒኼሽን ማዕከል የሚባል ማህበር ነው።

ድርጅቱ አሁን የተደረሰበትን ውሳኔ አስመልክቶ ” ሩጫዬን ጨርሻለሁ፣ መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ” አይነት የልዩ እርካታና የድል መልዕክቱን እስቀድሞ ውሳኔው እንደሚወሰን በይፋ ቢያስታውቅም፣ በጋለ ስሜት አውጇል። ይህ ቀላል የተባለ ውሳኔ የወስዋሽ ድርጅቱን፣ ጉዳዩን የሚከታተሉ ደጋፊዎችና በውጭ ያሉ የህወሃት ሴሎችን ቢያስደስትም በረሃ ውስጥ ያለው ትህነግ ግን ቅሬታውን ነው ያስተጋባው።

” ተበዳይ ሆነን ሳለ እንዴት የጉዞ ማዕቀብ ይደረግብናል” ሲል በረሃ ባለው ትህነግ ስም መግለጫ ቢወጣም፣ አቶ ጌታቸው ባሰራጩት መልዕክታቸው ማዕቀቡ ተጣለ አልተጣለ ኢሳያስና አብይን እንፈነቅላቸዋለን ማለታቸው ሁለት ስሜት ፈጥሯል። በውሳኔው መደሰታቸውን አስታውቀው ምስጋና አለማቅረባቸው ” ምን ጎድሎባቸው ነው” የሚለውን ጥያቄ አስነስቷል።

በትግራይ ውስጥ የተከሰተው ማህበራዊ ቀውስ ከምንም በላይ አሳዛኝ መሆኑን፣ ቀውሱ በዚህ ሊቀጥል እንደማይገባው የሚያምኑ ወገኖች “በህግ የሚጠየቁ ተለይተው ንግግር ቢደረግ” ወደሚል መለሳለስ እየመጡ ባለበት ወቅት፣ አቶ ጌታቸው ከበረሃ ጽህፈት ቤታቸው ሆነው ያሰራጩት መልዕክት ዛሬም ምን እንደሚፈልጉ አለማወቃቸውን የሚያመላክት እንደሆነ አመልክተዋል።

“አቶ ጌታቸው ውሳኔውን አድንቀው እንደ አንድ ተጨማሪ ጥይት እንደሚጠቀሙበት ማስታወቅ ሲገባቸው ወደ ዛቻ መግባታቸው የሰላም አስከባሪ እንዲገባ የተደረገውን ውስወሳ መመከን አመላካች ነው” ሲሉ የተቹም አሉ። እነዚሁ ክፍሎች እንደሚሉት ” የቀድሞ የትህነግ አመራሮችም እገዳው ይመለከታቸዋል መባሉ በውጭ ያሉትን ስላስከፋ አቶ ጌታቸው ከበረሃ ሆነው ይህንን እንዲሉ ተመክረው ሊሆን ይችላል” የሚል ግምት እንዳላቸው ገልጸዋል።

መንግስት “አሸባሪ” ተብሎ ከተሰየመው ትህነግ ጋር መወያየት ከቶውንም እንደማይታሰብ በሚገልጽበት ወቅት፣ በህግ የሚጠየቁ ተለይተው፣ አዲስ የተጀመረው የኢትዮጵያና የኤርትራ ወዳጅነት ሳይበላሽ የኤርትራ ሰራዊት እንዲወጣ በማድረግ፣ ህግ ከማይፈልጋቸው ጋር መነጋገር እንዲቻል የሚያመቻቹ ክፍሎች በሚስጢር እየሰሩ እንደሆነ በሚሰማበት ሁኔታ አቶ ጌታቸው በሃይል የኢትዮጵያንና የኤርትራን መንግስት ለማንበርከከና ለመፈንቀል መዛታቸው ” የማይረጥቡ አሳ” አሰኝቷቸዋል። ቀደም ሲልም ” በኢትዮጵያና ኤርትራ ፍርስራሽ ላይ ታልቋን ትግራይ እንመሰርታለን” የሚለው ቅዠት ዛሬም እንዳልተማሩበት የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቁሟል። አካሄዱ በችግር ላይ ላለው ወገን የትግራይ ህዝብ የሚተቅም እንዳልሆነም ተመልክቷል።

ወስዋሹ ድርጅት በቲውተር ገጹ ለስኬቱ እርዳታ ያደረጉለትን ድጋፍ ሰጪ ያላቸውን ኦላ ኦሮሞ፣ ሴና ጂምጂሞ አመስግኗል። ይህም ቀደም ሲል “የኦሮሞን ህዝብ ጨፍጭፏል፣ አስሯል፣ አኮላሽቷል፣ እንዲሰደዱ አድርጓል፣ ዘርፏል፣ ኦነግ በሚል ስም እያሸማቀቀ እስር ቤት አጉሯል፣ ቶርቸር አድርጓል፣ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጄኖሳይድ ፈጽሟል …” በማለት ሲከሱት ከነበረው ትህነግ ጋር ዳግም ህብረት መስርተዋል በሚል የሚነሳውን ቅሬታ የሚያጎላ ሆኖ ተገኝቷል። S.Res.97 passed & @POTUS has now authorized travel restrictions & sanctions. While the fight is not over, we thank @ollaaOromo & @SeenaaJimjimo for bringing this issue to our attention, & @TigrayCIC for asking us to take up this fight. God bless the people of Tigray & the USA

ኢትዮጵያ ከባድ ፈተና ቢኖርባትም በቀጭን የስምምነት ውሳኔ ሁሉንም ጉዳይ መገልበጥ እንደምትችል የሚያምኑ እንደሚሉት የአቶ ጌታቸው ንግግር የታሰበው የሰላም አስከባሪ መሰማራት ጉዳይ ውሃ ስለበላው የተፈጠረ ስሜት እንደሆነም እየተጠቆሙ ቢሆንም ውሳኔው የቀጣይ ማእቀቦች አመላካች በመሆኑ መንግስት ታክቲካዊ መለሳለስ እንዲያደርግ የሚመክሩም አሉ።

በትግራይ ቁጥራቸው በርካታ እርዳታ ሰጪዎች፣ ሰፊመጠን ያለው እርዳታ እየገባ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የረሃብ አደጋ መኖሩን ዪኤስ አይ ዲ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ የመጪው ክረምት ጣጣ ሳያመጣ መፍትሄ ማፈላለግ በሁሉም አቅጣጫ አግባብ እንደሆነ ምክር የሚለግሱ እየተሰሙ ነው።

ወስዋሹ ዶክተር ካርል ቮን ባተን በሜይ 28 ሲኤን ኤን ላይ ቀርበው መንግስት ከትሀንግ ጋር መነጋገር እንዳለበት ተናግረዋል። ከየአቅጣጫው የድርድር ጉዳይ በስፋት ከማስፈራሪያ የወንጀል ክሶች ጋር እየተሰማ ይገኛል።

ሎቢስቱ ( ወስዋሹ) ድርጅት

በተለይም የጦር ወንጀለኛነት የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለመክሰስ የሚደረገው ሩጫ ምንም ዓይነት ምልክት ባልነበረበትና ጦርነት ስለመጀመሩ ምንም በማይሰማበት ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት እነ ዳኔል ብረሃኔ በተደጋጋሚ ” አብይን የዓለም አቀፉ የጦር ፍርድ ቤት እንወረውርና ” እያለ ቀታይ እቅዳቸውን ሲናገር እንደነበር ይታወሳል። ገና ግጭቱ እንደተሰማ ሱዛን ራይትስ ” ይህማ የጦር ወነጀል ይሆናል” ማለቷ ከጅምሩ ሆን ተብሎ የተሰራ ድራማ ስለመኖሩ አመላካች እንደሆነ አየተጠቆመ ነው።፡

በኦፊሳል ድረ ገጻቸው በየደቂቃው ዘመቻውን የሚመሩት ወስዋሽ ስንት እንደሚከፈላቸው አይታወቅም። ድንበኛቸው ሆኖ በስም የተጠቀስው ማህበር ግን ጎ ፈንድ ሚ ከፍቶ እርዳታ እየጠየቀ ነው።

ይህ በንዲህ እንዳለ የትህነግ የውጭ ክንፍ ተተሪ የተባሉትና ባለቀ ሰዓት ወደ አሜሪካ ያመሩት አምብሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ” ምንም ገንዘብ አልዘረፍንም” ሲሉ በትግራይ ሚዲያ ሃውስ አስታውቀዋል። የዓለም የገንዘብ ድርጅቶችም ሆኑ አገራት በቂ መረጃ እንዳላቸውና ድርጅታቸው በዝርፊያ ሊታማ እንደማይችል ያስታወቁት ብረሃነ ገብረክስርቶስ ለፈቷት ሚስታቸው በፍርድ ቤት ሚሊዮን ዶላር ስለመክፈላቸው ተነስቶ አልተጠየቁም። ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ የወታውን ገንዘብ አሃዝ በቢሊዮን ዶላሮች ተንትኖ ማቅረቡ ተጠቅሶ ይፋ ስለመሆኑ አልተጠየቁም እሳቸውም አላነሱትም። ከረዥም ጊዜ በሁዋላ ወደ ሚዲያ ብቅ ያሉበት ምክንያት አንዳንድ ጉዳዮችን እንዲያብራሩ መሆኑ በተገለጸበት ቃለ ምልልስ ስለ ትህነግ ሲጠየቁ ማብራሪያቸው በሙሉ ” የትግራይ ሕዝብ” በሚል ትህነግን ከህዝብ ጋር በመቀላቀል ነበር።


Exit mobile version