ETHIO12.COM

ሰበር ዜና – የትግራይ ክለቦች በመጪው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር መሳተፍ እንደሚፈልጉ አስታወቁ

ሶስቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አሳወቁ። እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚችለው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የክለቦቹ ውሳኔ የበረሃውን ፖለቲካ በአገርም ሆነ በውጭ ውሃ እንዲደፋበት ሰልመሚያደርገው ከወዲሁ በክለቡ አመራሮች ላይ ዘመቻ እንዳይጀመር ተሰግቷል።

ዜናውን ኢቢሲ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የነጋገርናቸው እንዳሉን ከሆን ተቃውሞ መነሳቱ አይቀርም። ” ኳስ ሰፊ መሰረቱ ማህበራዊ ግኝኙነት ነውና በትግራይ የእግር ኳስ ውድድር ከተጀመረ የበረሃው ፖለቲካ ላይ ትልቅ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው፣ በዓለም ዓቀፍ ደራጃ ስፖርት የሰላም ማሳያ ስለሆን እይታ ስለሚቀይር የበረሃው ሃይል ደጋፊ ሚዲያዎች ዘመቻ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል” ሲሉ የአንዱ ክለብ አስልጣኝ የነበሩ ነግረውናል።

የፕቲማየር ሊጉ ውድድር በዲኤስ ቲቪ በቀጥታ ለዓለም እይታ ስለሚበቃ እንደርታ፣ መቀሌና አዲግራት ትግራይ ላይ ሲጫውቀቱ ማሳየት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚፈጥረው ስዕል ከፍተኛ በመሆኑ አዲሱ ይክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ እንዲሁም በቂ ካፒታል ያላቸው ክለቦች ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም አስተያየት ሰጪው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ከ3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ጋር ስለ ቀጣይ የውድድር ዘመን ተሳትፏቸው ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ክለቦቹ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ያስረዱ ሲሆን ወደ ውድድር ለመመለስ ፋይናንስ ትልቅ ማነቆ እንደሚሆንባቸው አስረድተዋል።

ከውይይቱ ያገኟቸውን የሀሳብ ግብዓቶች ወስደው ወደ ክለቦቻቸው በመመለስ፣ ከደጋፊዎቻቸው እና ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመነጋገር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔያቸውን እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በኩል የ600 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን፣ ለዚህም የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምስጋናውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ክለቦቹ ወደ ውድድር እንዲመለሱ ለማድረግ በሚችለው ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን መግለፁን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


Exit mobile version