Site icon ETHIO12.COM

በትግራይ ህግ ማስከበር ዘመቻ “ከሰላማዊ ዜጎች ግድያና ጾታዊ ጥቃት”ጋር በተያያዘ 53 የመከለካያ ሰራዊት አባላትን ተጠያቂ ተደረጉ

ከሰላማዊ ዜጎች ግድያና ጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ በ53 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ክስ መመስረቱንና በትግራይ የርዳታና የሰብአዊ ድጋፉ በስፋት እየተሰራጨ መሆኑንን የውጭ ሚዲያዎችና ትግራይ ተቀምጠው ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች የሚያቀርቡትን የተሳሳተ ሪፖርት የሚያመክን መግለጫ ተሰጠ።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ የውጭ ሚዲያዎች ተገኝተው ነበር።

በከረረ ቃላቸው ኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን የሚዲያ ዘመቻና ወገንተኛነት በአሃዝ በተደገፈ መረጃ ያስረዱት ቢለኔ ስዩም፣ በውጭ አገር የሚኖሩ የሽብረተኛው ትህነግ ደጋፊዎች በበቂ ደረጃ ብር ለሚሰጡዋቸው ሎቢስቶች የተሳሳተ መረጃ በመቀበል የሃሳት ዘመቻ በመክፈት የኢትዮያን ስም ማተልሸታቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም ከቢቢሲ ጋዜጠኛነቱ ወደ በረሃ ያመራውና አሸባሪውን ቡድን የተቀላቀለውን የሽብረተኛው አባል እንደማስረጃ ጠቁመዋል።

ለጦርነቱ መነሳት ምክንያት የሆኑትንና ዓለም በውሉ የሚገነዘበውን ነጥብ በማስረዳት የተደራጀ መግለጫ የሰጡት ሃላፊዋ በኢትዮጵያ በኩል የተሰራዉን አስረድተዋል። ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንዳሉት ለማንም ስልባል ሳይሆን ለህግ የበላይነት ሲባል ሰፊ ስራ መሰራቱን አመልክተዋል።

በትግራይ ክልል ከሰላማዊ ዜጎች ግድያና ጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ በ53 የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ክስ መመስረቱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገልጸዋል።በማይካድራ ከንጹሃን ግድያ ጋር በተያያዘ 200 ሰዎች መለየታቸው እና ከእነዚህም ውስጥ 23ቱ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸውም ይፋ አድርገዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ጋር በመሆን በአገር ውስጥ ለሚገኙ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

መግለጫውም በዋናነት በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ተፈጸሙ የተባሉ ወንጀሎች ላይ ያተኮረ ነው።

ጠቅላይ አቃቤ ህጉ በዚህ ወቅት በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉ ወንጀሎችን በማጣራት ረገድ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

በምርመራው የአሸባሪው ህወሃት ስራ አስፈጻሚ አባላት የታጠቁ ወታደሮችን በማደራጀት የሰሜን እዝን ከማጥቃት ጀምሮ የህገ መንግስት ጥሰትን በተለያዩ አካባቢዎች የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲፈጸም ጥረት ማድረጋቸው ተረጋግጧል ብለዋል።

በተጨማሪም ይህ ኃይል በፌዴራል ተቋማት የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ፈጽሟል፤ ተቋማቱንም አውድሟል ነው ያሉት።

በወንጀሉ የተጠረጠሩ የተወሰኑ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ ሌሎችን የማደኑ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተለያዩ ጥፋቶች ላይ ተሰማርተው የተገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተጠያቂ እንደሚሆኑ ቀደም ሲል መግለጻቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ክልሉ ከሰላማዊ ዜጎች ግድያ ጋር በተያያዘ 28 እንዲሁም ከጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ 25 የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ክስ መመስረቱንም ጠቁመዋል።

እስካሁን ባለው ሂደትም በክልሉ ከ100 በላይ ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸው ማለፉን ነው ጠቅላይ አቃቤ ህጉ የተናገሩት።

በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ጭፍጨፋ ደግሞ በርካቶች መሞታቸውንና ለከፋ አካላዊ ጉዳት መዳረጋቸውን አንስተዋል።

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ ‘እጃቸው አለበት’ ተብለው 200 ሰዎች መለየታቸውንና ከእነዚህ ውስጥ 23ቱ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ ተመስርቶባቸዋል ነው ያሉት። የፍርድ ሂደታቸውም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

በማይካድራ የሰላማዊ ዜጎች እልቂት እጃቸው አለበት ተብለው ከተለዩ ሰዎች መካከል በርካቶች ወደ ሱዳን መሸሻቸውንም ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ገልጸዋል።

በዚሁ መግለጫ እንድተባለው አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የተጀመረው የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ የአለም አቀፍ ግንኙትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ቢለኔ ስዩም መግለጫውን በሰጡበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ከአለም የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በክልሉ የተለያዩ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ማዕከላት ተቋቁመው እርዳታ እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በዚህም የምግብ፣ የመጠለያ፣የአልባሳት እና የመድሃኒት አቅርቦቶች እየቀረቡ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

የመንግስት ዋና አላማ ወንጀለኞችን ወደ ህግ ማቅረብ መሆኑን የገለጹት ቢለኔ ፤”የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊ ድጋፍ እንቅፋት ሆኗል እየተባሉ የሚነዙ አሉባልታዎች መሰረተ ቢስ ናቸው” ብለዋል፡፡ ከህግ ማስከበር ጎን ለጎን ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዜናው ለኢዜአ ጋር ተቀላቅሎ የተሰራ ነው


Exit mobile version