Site icon ETHIO12.COM

የዓባይ በረሃ በደን ሊሸፈን ነው


በኢትዮጵያ አካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የተቀናጀ ሥራ ከጐሐፅዮን እስከ ደጀን የሚዘልቀው የዓባይ በረሃ ሙሉ በሙሉ በቆላ የቀርከሃ ተክል የመሸፈንና አረንጓዴ ዐሻራ የማኖር ሥራ መጀመሩ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ አካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት የባዮ ቴክኖሎጂ ተመራማሪ አቶ አዱኛው አድማስ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ከሰሜን ሸዋ ዞን ጐሐፅዮን ወረጃርሶ ወረዳ እስከ አማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ደጀን ወረዳ የሚዘልቀው የዓባይ በረሃ በደን ለመሸፈን የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ ወደ ሥራ ተገብቷል። ከጐሐፅዮን እስከ ደጀን የሚዘልቀው የዓባይ በረሃ ከፍተኛ የሆነ ማዕድንና አሸዋ መገኛ በመሆኑ ሰፊ ቦታ ማዕድናትን የማውጣት ሥራ እየተከናወነ ቢሆንም መልሶ የማልማት ሥራ ባለመከናወኑ የመሬት መራቆትና አፈር መሸርሸር እየተከሰተ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአካባቢው ቀደም ሲል የነበረውን ደን በመጨፍጨፍ አርሶ አደሮች ለከሰል እና ለሌላ አማራጭ ስለተጠቀሙበት አካባቢው ለመሬት መከላት መጋለጡንና ለኑሮ አስቸጋሪ መልክዓ ምድር እየሆነ መምጣቱን አስገንዝበዋል።በአሁኑ ወቅትም የቀረው የእንጨት ዝርያ ለከሰል ኃይል ምንጭ ሲባል እየተጨፈጨፈ ነው። አፈር እየተሸረሸረ በቀጥታ ወደ ዓባይ ወንዝ እየገባ ነው።በመሆኑም አካባቢውንም ሆነ የዓባይን ወንዝ ከችግር ለመታደግ በረሃማውን አካባቢ በቀርከሃ ደን የመሸፈን ልዩ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመዋል። via (ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version