Site icon ETHIO12.COM

“በስራ እንጂ በአሉባልታ ስም-ማጥፋት ያደገ ሀገር የለም!” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ጠዋት”በስራ እንጂ በአሉባልታ ስም-ማጥፋት ያደገ ሀገር የለም!” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ‼

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው … ‼

👉 የደቡብ አፍሪካው ኩባንያ ለቤት ግንባታ የሚያስፈልገውን 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ካፖኒው ከውጪ ይዞት ለመምጣት እንጂ ከእኛ ባንኮች ምንም አይነት የሚፈልግ ብድር አልፈረምንም፤

👉 አልሚው በመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ ለሚገነባው 100,000 ቤቶች ግንባታ የሚውል 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ ያዘጋጀ ስለመሆኑ ህጋዊ ሠነዶችን አቅርቧል፤

👉 በእኛ በኩል ደግሞ ለግንባታው የሚያስፈልገውን መሬት በአስተዳደሩ ስር ሆኖ ለግንባታ እናቀርባለን፤

👉 በተጨማሪም ለግንባታ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ የምንፈቅድ ይህናል፤

👉 በስምምነቱን መሠረት ለግንባታ የሚያስልገው መሬት በአስተዳደሩ ባለቤትነት ስር የሚቆይ እንጂ ለአልሚው ድርጅት የሚተላፍ አይደለም፤

👉 ለግንባታው የሚያስፈልጉ የተወሰኑ ግብአቶችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ይፈቀድለታል፤

👉 እቃዎቹ አገር ውሰጥ ከገቡ በኃላ የሚሰጥ መብት ስለሚሆን ከውጪ ወደ እኛ ጋር ይገባል እንጂ ከአገር ውስጥ ይዞት የሚወጣው ምንም ነገር አይኖርም፤

👉 ይህ ማለት በቀላል አነጋገር ለግንባታ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ ይዞ ይመጣል ማለት ነው፤

ሙሉ መልዕክታቸው እንደሚከተለው ቀርቧል።

በስራ እንጂ በአሉባልታ ስም-ማጥፋት ያደገ ሀገር የለም!

እንኳንስ በአሉባልታ ውድ ጊዜያችን ልናጠፋ ይቅርና ለዘመናት የተነባበረውን የአገራችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማቅለል በሂደትም ለመፍታት ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ከድህነትና ኋላቀርነት ጋር የጀመርነው እልህ አስጨራሽ ግብግብ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ነገር ግን “ዉሸት ሲደጋገም” ነዉና ነገሩ..ለግልፅነት ያክል የሚከተለውን ማለት አስፈላጊ ነዉ።

በለውጡ ዋዜማ በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጲያ ጭንቅ ላይ ወድቃ በነበረችበት በዛ ፈተኝ ወቅት ፈተናውን ከህዝባችን ጋር ተጋፈጠን፣ ነፋሳችንን አስይዘን በኢትዮጲያችን የፈነጠቀው የለውጥ ጮራ እውን እንዲሆን አደረግን እንጂ ::ይህ እንዲሁ ሲነገር ቀላል ይሁን እንጂ ወንድምና እህቶቻችንን ቀብረን የእነሱ ኢትዮጵያን ከድህነት የማለቀቅን አደራ ተቀብለን ነው ሌትና ቀን በጽኑ የአገልጋይነት መንፈስ እየሠራን ያለነው፡፡

በዚህም በብዙ ድርብርብ ችግሮች ዉስጥ ሆነን ድንቅ ሊባል የሚችል ለውጥ እያስመዘገብን እንገኛለን፡፡

ታሪካችንን ከተጣለበት አንስተን ተገቢውን ክብርና ቦታ እየሠጠን አዲሲቷን የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመገንባት ከዉስጥም ከዉጪም ትግላችንን ቀጥለናል ፡፡

ይህ ሂደት ታዲያ አልጋ በአልጋ አይደለም፡፡ ሀገር ወዳድ ህዝባችን አይዞአችሁ፤ እለንላችሁ፤ ከጎናችሁ ነንሲለን ጥቆቶች ደግሞ ካፌ ተቀምጠው አቃቂር እያወጡ፤ በአሉባልታ ስም-ማጥፋት : በእኩይ እያነሱ ሊያዘናጉን፤ ወደ እነሱ ደረጃ ሊጎትቱን፣ ይዘን የተነሳውን የህዝብ አደራ በአጭር ሊያስቀሩ ይሞክራሉ ፡፡

እኛ ግን ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አንልም፡፡ አዲስ አበባችን የድህነት ምጣኔው አንገት የሚያስደፋ፤ ልጆቿ ባዶ ምሳ እቃ ይዘው ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱበት ፤ ወጣቶቿ በከፍተኛ የስራ አጥነት ችግር ውስጥ የሆኑበት ፤ በቤት ኪራይ የሚንገላታ ለአመታት በቆጠበው ብር በተስፋ የሚኖር ነዋሪ ያለባት ስሟ እንጂ ምግባሯ አንገት ቀና የማያደረግ ከተማ ነዉ የተረከብነው፡፡

ለዘመናት የተከማቸውን የመኖሪያ ቤት ችግር እንኳ ብንመለከት ለ 16 ዓመታት የከተማቸውን በሚሊዮን የሚቆጠር ተመዝጋቢና ቤት ፈላጊ ፤ በከተማችን ነዋሪዎችን ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የቤት ፍላጎት በማስታረቅና ፈጣን ምላሽ መስጠት በራሱ ከፍተኛ ስራና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ተግባር ነበር ፡፡

በአጭር ጊዜ በዘርፍ ላለፍት አስር አመታት ያልነበረውን የአሠራር ግልጽነት በጥናት በመመለስ፤ ተገንብተው የነበሩ ነገር ግን ከፍተኛ የግንባታ ጥራትና የመሠረተ ልማት ችግር የነበረባቸውን ግንባታዎች በማሻሻልና በማጠናቀቅ የተነባበረውን የቤት ፈላጊ ቁጥር በአጭር ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ አማራጮችን በመተግበር ጭምር ብዙ ርቀት መጓዝ ተችሏል፡፡

ከእነዚህም መካከል የማህበር ቤቶች ግንባታ ከሊዝ ነፃ መሬት በማቅረብ፤ የአገር ውስጥ የግል አልሚዎችን ወደ ዘርፍ እንዲገቡ በማድረግ፤ እንዲሁም በዘርፍ ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ ያላቸውን አለም አቀፍ የቤት አልሚ ካምፖኒዎችን ጭምር ለማሳተፍ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ይቆተዋል፤ ከብዙ ድርድርድና ውይይት በኋላ በብዙ መመዘኛዎች ሁሉት አለም አቀፍ አልሚዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን አነስተኛ ገቢ ላላቸው ለመንግስተ ሠራተኞች፤ ተመዝግበው የቤት ባለቤትነትን እየጠበቀ ላሉ ነዋሪዎች.. ወዘተ ለመገንባት ከስምምነት ተደርሷል፡፡

አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችም በመጠናቀቀ ላይ ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህ መካከል ከወራቶች በፊት አስቀድመን የጀመርነው እና በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ ከከተማና ኮንስትራክሽ ሚኒስትር ጋር በትብበር በቅንጅት ስንሠራው የነበረው በደቡብ አፍሪካና በሌሎች አገራት በአነስተኛ ዋጋ የሚገነቡ ቤቶችን በመገንባት ከሚታወቀው property 2000 አልሚ ጋር ያደረግነው የመግባቢያ ስምምነት ነው፡፡

በስምምነቱ መሠረት አልሚው በመጪዎቹ አምስት አመታት 500,000 ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት (MOU) አድርገናል ፡፡ ለግንባታው የሚያስፈልገውን 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ካፖኒው ከውጪ ይዞት ለመምጣት እንጂ ከእኛ ባንኮች ምንም አይነት የሚፈልግ ብድር አልፈረምንም፡፡

አልሚው በመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ ለሚገነባው 100,000 ቤቶች ግንባታ የሚውል 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ ያዘጋጀ ስለመሆኑ ህጋዊ ሠነዶችን አቅርቧል፡፡ በእኛ በኩል ደግሞ ለግንባታው የሚያስፈልገውን መሬት በአስተዳደሩ ስር ሆኖ ለግንባታ እንዲቀርብ በተጨማሪም ለግንባታ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ የምንፈቅድ ሲሆን በተጨማሪም ቤቶቹን ገንብቶ ካስረከበን በኋላ በ30 ዓመት ውስጥ የግንባታውን ዋጋ ትርፍና ወለድ ለመክፈል ግዴታ መግባት ሲሆን በስምምነቱን መሠረት ለግንባታ የሚያስልገው መሬት በአስተዳደሩ ባለቤትነት ስር የሚቆይ እንጂ ለአልሚው ድርጅት የሚተላፍ አይደለም፡፡

በተጨማሪም ለግንባታው የሚያስፈልጉ የተወሰኑ ግብአቶችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ይፈቀድለታል ማለት እቃዎቹ አገር ውሰጥ ከገቡ በኃላ የሚሰጥ መብት ሲሆን ከውጪ ወደ እኛ ጋር ይገባል ማለት እንጂ ከአገር ውስጥ ይዞት የሚወጣው ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ይህ ማለት በቀላል አነጋገር ለግንባታ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ ይዞ ይመጣል ማለት ነው፡፡

ኩባንያው በደቡብ አፍሪካ ሪልስቴት የማልማት ስራና የመሠረት ልማት ግንባታም ሆነ ዝርጋታ ላይ የረጅም አመት ልምድ ያለው እና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በተለይም በደቡብ አፍሪካ፤ በዙምባቡዌ፣ በጋና ፣ በናይጀሪያ እና በሌሎች በርካታ አገራት ስራዎችን የሰራ እና በመስራት ላይ የሚገኘ መሆኑን መረጃዎች ያገኘን ሲሆን እንዲሁም በኢትዮጵያ ጭምር property 2000 ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቅ ድርጅት ከፍቶ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅትን አጠናቋል፡፡

ተቋሙ በተጨማሪም በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ካላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ የፋይናንስ የልማት ተቋማት በተለያየ ጊዜ በስራው የተመሠገነ ግዙፍ ኩባንያ መሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኩባንያው ባለቤት የሆኑት ቼርማን ናፖ ኤድዋርድ ሞዲሴ በሌሴቶ እየገነባ ስላለው ፕሮጀክት ከጋዜጠኛ የቀረበ ጥያቄን አስመልክቶ የሰጠውን መልስ ወደ ጎን በማለት እና ተጨማሪ የግልፀኝነት ጥያቆ ሳያነሱ፤ ሌላ መረጃና ማስረጃ ሳያቀርቡ እንዲሁ አልሚው አጭበርባሪ ነው ብሉ መደምደም ተገቢ አይደለም፡፡ ደግሞም እኛም ካለን በርካታ አማራጮች መካከል አንዱ እንጂ ብቸኛው አማራጭ አይደለም፡፡

የዘርፉ ብቸኛ አልሚም አይደለም፤ እሱን ብቻ ተማምነን እንቆያለን አላልንም፡፡ ገና ስለ ቤቱ ዋጋ ና ስለፕሮጀከቱ አዋጭነት ጥናት ይደረጋል ነው ያልነው፡ እባካችሁን እንደገና እንደማመጥ:: በዚህ ሂደት ውስጥ የምናተርፈው፤ የምናዳብረው፤ እንጂ የምናጣው እንዳች ነገር የለም፡፡
ሆኖም በቅንነት እንዳትጭበረበሩ በደንብ ተመልከቱ ያላችሁንን እናመሰግናለን ።

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ እስኪ የቱ ጋር ነው በዚህ ሂደት የምንከስረው? በየትኛው መብትና መስፈርትስ ነው መሬት የሚቸበቸው? እዳ እየተባለ የሚወራው በሬ ወለደስ ከየት የመጣ ነው? ተቋሙ በገባው ቃል መሠረት በተባለለት ጊዜና ጥራት ግንባታው ካልተገነባ በኢትዮጵያ ህግ ጭምር እንደሚጠየቅ በስስምነት ውሉ ላይ ተስማምቶ ፈርሟል፡፡

ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ ወትሮም የህዝባችንን ለዘመናት ሰሚ ያጣ ጥያቄ ለመመለስ ሌት ተቀን ስንሰራ አይናቸው የሚቀላ፤ ተሳዳቢዎች ፤ ስም-ማጥፋት እንጂ፤ ሰርተው ማሳየት ያልቻሉ፤ በስራ ሳይሆን በወሬ ስብእናቸውን ለመገንባት የሚጥሩ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንዲት ነገር ሰርተው ማሳየት ያልቻሉ አዋቂ ነን ባዮች የሆኑ ጥቂቶች ይህንን ጥረታችንን፤ ስራችንን ለማጠልሸት እና ህዝቡን ለማደናገር ሲሞክሩ ተመልክተናል፡፡

ወርደው ፤ ወርደው 500,000 ቤት በአምስት አመት ለመጨረስ በቀን ምን ያህል ቢሰራ ነው የሚያልቀው እያሉ ህዝቡን ያደናግራሉ ::

ዋናው ትጋትና ጥንካሬ እንጂ ከዚህም በላይ ይሰራል፡ ግዙፉን የላፍቶ የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማዕከል በ3 ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ገብተናል፣ ኮሮናን ለመከላከል እንኳን 2000 የመማሪያ ክፍሎችን 233 የመመገቢያ አዳራሾችን በየትምህርትቤቶቹ በቀናት ዉስጥ ገንብተናል ።ታሪክ አወደሙ ወዘተ..ብዙ የተባልንበትን ፤በአደባባይ የተዘለፍንበትን የመስቀል አደባባይ በ 10 ወራት ጊዜ ዉስጥ ተአምር ሊባል በሚችል ደረጃ ሀብት የሚያፈራ ለከተማችን ዓይን የሆነ ታሪካዊ ስፍራ አድርገነዋል፤ በርካታ መሰረተልማቶችን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፤እየተገባደደ ባለዉ የ2013 ዓ.ም ብቻ በከተማችን ታሪክ በሚባል ደረጃ 2060 ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት አብቅተናል፡፡

ይህንንም በኢትዮጲያዊ ጨዋነት ጊዜው ሲደርስ ማየት ይሻላል፣ ይበጃልም ፡፡

በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ዕሴቶች ስብራት ለመጠገን ደፋ ቀና ስንል ያጠፋነው እንኳ ካለ በፍጽም የወንድማማችነት እሳቤ እየተደጋገፍን ፤እየተራረምን እንደ ተቀናቃኝ ሳይሆን እንደ ተፎካካሪ ያየናቸው ፖርቲዎች ጭምር በዚህ በሬ ወለደ ተግባር ውስጥ ተዘፍቀው በማየቴ እጅጉን አዝኛለሁ::

እናም ዋናውን አማራጭ መነጋገር ትችታችሁ ስድብን ምን አመጣው ? አንደበታችሁ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጎደለው ለምን ሆነ? ዋነኛ ትኩረታችሁ ትልቋ ኢትዮጵያ ሳትሆን አዲስ አበባና ከንቲባነት ብቻ ይሆን ? እስኪ በቴሌቪዥን መስኮት እና በማህበራዊ ድህረገጾች ወጥቶ ከመሳደብ የተናገራችሁትን ለተመልካቹ እንዲሁም ለህዝብ ክብር ስትሉ በመረጃ አቅርቡት።

ለማንኛዉም እኛ ለአሉባልታና በሬ ወለደ ጊዜ የለንም ህዝባችን የሰጠንን አደራ ከግብ ለማድረስ የጀመርነውን መንገድ አጠናክረን መቀጠል እንጂ ለአፍታ ቢሆን ቆም አንልም፤ እዉነቱ ይኸው ነዉ።

ለደሃ ቤት መስጠት ፤ከቆሻሻ ገንዳ ላይ ምግባቸውን የሚመገቡ ወገኖቻችን መታደግ፤ የነገ ተስፋ የሆኑ ተማሪዎችን መመገብ፤ ምኑ ላይ ነዉ ህዝብን ማታለል የሚሆነው? ኧረ ለመሆኑ የህዝባችንን ችግር ይመጥን ይሆን?

በኮረና ቫይረስ ምክንያያት ዜጎቻችን ወገኖቻችን ለከፋ ችግርና ማህበራዊ ቀውስ ሲጋለጡ ይህንን ለመቋቋም የመተሳሰብና የመደጋገፍ ባህል ለማጎልበት የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ይፋ አድርገን ህዝቡ እርስ በርስ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲደጋገፍ ማድረጋችን የጉዳዩን መልካምነትና የተሻለ ስራን ከመመልከት ይልቅ ፣ በነሱ የሃሳብ ድርቅት ስራችንን ዝቅ በማድረግና ዘንደሮ መመገቢያ ማዕከላት ለምን ተገነቡ ብሎ y እነዚህ ስራዎች ለብልፅግና ፖለቲካዊ ጥቅም ያስገኝ ይሆናል ከሚል ስጋት ስራውን ማጣጣል እውነት ለዚህ ህዝብ የሚመጥነው አይደለም።

ዛሬ ከከተማ አስተዳደራችን ጋር አብረው እየሰሩ ያሉ በርካታ በጎ አድራጊዎችም በመንግስት ስልጣን ላይ የሚገኙም ብቻ አይደሉም እኮ::
ከህዝብ መስራት ከተፈለገ መስራት ሚቻልበት ብዙ መንገድ አለ እና እናንተም ለደሃው ማዕድ እንድታጋሩ እመክራችኋለሁ።

በኢትዮጵያ ጭንቅ ቀን ምዕራብዊያን ጋር ሲከርሙ በማስረጃ መናገርን ከእነሱ ተምረው ይሆናል ብዬ እገምታለሁ እና ስለዚህ ከላይ የተሱትን በማስረጃ እንዲያጋልጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

እኛ ግን ህዝባችንን የሰጠንን አደራ የህዝባችነ አደራ ለመመለስ የጀመርነው መንገድ አጠናክረን መቀጠል እንጂ ለአፍታ ቢሆን ቆም አንልም፤ እዉነቱ ይኸው ነዉ።

Property 2000 በስምምነቱ መሠረት ይገነባል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ባይገነባም ደግሞ አስቀድመን አማራጮችን ይዘናል፡፡ ለማንኛውም በሚቀጥሉት 5 አመታት 1 ሚሊዮን ቤቶች እንገነባለን፡፡

ፈጣሪ የከርሞ ሰው ይበለን ያኔ እንማማራለን፡፡
የትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ጉዳዮን አስመልክቶ ከላይ የዘረዘርኳቸውን መረጃዎች በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር! EPD

Exit mobile version