Site icon ETHIO12.COM

የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋምና እየተሰሩ ያሉትን አበረታች ስራዎች መካድ ተቀባይነት እንደሌለዉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ

የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋምና ወደነበረችበት ሠላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ በመንግስትና በተለያዩ አካላት እየተሰሩ ያሉትን አበረታች ስራዎች መካድ ተቀባይነት እንደሌለዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋም በመንግስትና በተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሰሩ ባሉት መሠረተ ሰፊ ስራዎች የጤና ተቋማት ስራ በመጀመር ላይ መሆናቸዉን: የመማር ማስተማር ሂደቱ በአንዳንድ ቦታዎች መጀመሩን: የተለያዩ ፋብሪካዎችን ወደ ስራ ለማስገባት በመሠራት ላይ መሆኑን: 70% የሚሆነዉ የክልሉ የእርሻ መሬት ለተለያዩ የግብርና ስራዎች ዝግጁ መሆኑን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በፖለቲካ ዲፕሎማሲ: በዜጋ ተኮርና በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ ባለፈዉ ሳምንት በተሰሩት ስራዎች ዙሪያ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋም እየተሠሩ ካሉት መጠነ ሰፊ ስራዎች መካከል ባንኮችና ኤርፖርቶችን ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የክልሉ አርሶ አደሮች በመህርና በክረምት እርሻ ላይ እንዲሳተፉ በመንግስት በኩል አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነዉ ብለዋል።

ፍትህን ከማረጋገጥ ጋር ተያይዞም ሰብአዊ ጥሰትን ፈጽመዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ወደ 60 የሚጠጉ ወታደሮች መከሰሳቸዉን ገልጸዋል።

ባለፈዉ ሳምንት 1136 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ መመለሳቸዉንም ቃል አቀባዩ በመግለጫቸዉ ጠቅሰዋል።

የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸዉን: በቴሌኮም ዘርፍና በተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር መወያየታቸዉን: በተለያዩ የአለም ሃገሮች የሚገኙ ኤምባሲዎች በርካታ የዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራታቸዉንም አምባሳደሩ በመግለጫቸዉ ጠቅሰዋል።

በካናዳ የሚኖሩ ዜጎች 140ሺ የካናዳ ዶላር ለሕዳሴዉ ግድብ ማበርከታቸዉንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

የሱዳንን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ በያች ሃገር እየታየ ያለዉን የጸጥታ መደፍረስ አንደግፍም ብለዋል። በወዳጆቻችንንና በጎረቤት ሃገራት መቃጠል አንደሰትም ብለዋል።

አምባሳደሩ ከጋዜጠኞች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ወንድማገኝ አሰፋ OBN

Exit mobile version