ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ተበድሮ ብድሩን በአግባቡ መክፈል ያልቻለው በቱርካውያን ባለቤትነት የተመሰረተውን ኢቱር ቴክስታይል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን ተረክቦ ማስተዳደር ጀመረ።
ዋዜማ ራዲዮ እንዳረጋገጠችው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካው የተበደረውን ገንዘብ በአግባቡ መመለስ ባለመቻሉ ለብድር አመላለስ በዋስትናነት የተመዘገበውን በአዳማ ከተማ ያለውን የጨርቃጨርቅ ፋብሪካን ተረክቦ ማስተዳደር ጀምሯል። የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካውን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ግለሰቦችን በማንሳትም ልማት ባንክ ለኩባንያው ስራ አስኪያጅ ፣የፋይናንስ ሀላፊ ፣የማርኬቲንግ እና ሌሎች ሀላፊዎችን ራሱ መድቧል።
በ1950ዎቹ በቱርክ የተቋቋመውና በጨርቃጨርቅ ምርቶች አለም አቀፍ አቅራቢነት የሚታወቀው የዩክሴል ቴክስታይል እህት ኩባንያ የሆነው ኢቱር ቴክስታይል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ስራ የጀመረው በ2002 አ.ም ነበር። በወቅቱም ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቢሊዮን የሚቆጠር ብድር ከወሰዱ መሰረታቸውን ቱርክ ካደረጉ ፋብሪካዎች ውስጥ የሚመደብ ነው።
አዳማ ላይ ባቋቋመው ፋብሪካ በዋነኝነት ክርን የሚያመርት ሲሆን ክርን በመጠቀም የተለያዩ ምርቶችን ለሚያመርቱ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ግብአት ሲያቀርብም የቆየ ነው።
ነገር ግን እንደሌሎች የቱርክ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የወሰደውን ብድር በጊዜው መክፈል አልቻለም። ከስድስት አመት ወዲህም ፋብሪካው የልማት ባንክን ብድር መመለስ ስላልቻለ የተበላሸ ብድር መዝገብ ውስጥ ገብቶ የቆነ ነው።
በተደጋጋሚ ብድሩን እንዲመልስ ከልማት ባንኩ ደብዳቤ የተጻፈለት ቢሆንም በተገቢው መንገድ ብድሩን እንዳልከፈለ ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች።
የፋብሪካው ብድር ከነወለዱ ከ1.2 ቢሊየን ብር እንደሚያልፍያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ልማት ባንኩ በተደጋጋሚ ፋብሪካውን ሽጦ ገንዘቡን ለማስመለስ አስቦ የነበረ ቢሆንም ኩባንያው የሰራው ፋብሪካ እና ያስመጣቸው ማሽኖች ዋጋ ከወሰደው ከፍተኛ ብድር አንጻር በጣም አነስተኛ መሆኑና የቀጠራቸው ሰራተኞች የስራ ዋስትና ስጋት ስለፈጠረበት ሀራጅ የማውጣቱን ነገር አልተገበረውም።
አልሲ አዲስና አይካ አዲስ የሚባሉ ሁለት የቱርክ ኩባንያዎች ልክ እንደ ኢቱር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቢሊየን የሚቆጠር ብር ተበድረው መክፈል ስላልቻሉ ባንኩ ገንዘቡን ለማስመለስ ተደጋጋሚ ጨረታ ቢያወጣው የፋብሪካዎቹ ዋጋ ብድሩን የማያስመልስ ብቻም ሳይሆን የወሰዱት ብድርና ያስገቧቸው ማሽኖች ዋጋ ሊመጣጠን ባለመቻሉ ተረክቦ ማስተዳደር ከጀመረ ሰነባብቷል። በተለይ ለቱርክ ኩባንያዎች የተሰጠው ብድር የተጋነነና የሰሩት ፋብሪካና ያስመጡት ማሽን የወሰዱትን ብድር አይመጥንም በሚል በተደጋጋሚ ባንኩ ላይ ትችት ሲቀርብ እንደቆየ የሚታወቅ ነው።
ልማት ባንኩ ኢቱር ቴክስታይል ኩባንያን ካለበት የብድር አከፋፈል ችግር እስኪወጣም ራሱ በሰየመለት አመራሮች እየተመራ የሚቀጥል ይሆናል። [ዋዜማ ራዲዮ
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና። ፍርድ… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው ግን… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው