Site icon ETHIO12.COM

የኦሮሚያ ክልል መግለጫ አወጣ፤ ስጋት የለም

ኦሮሚያ ከምርጫው ቀን ቀድማ እንደምትታመስ ቀደም ሲል ጀመሮ የሚነገር ቢሆንም በያዝነው ሳምንት ግን ተባብሷል። የጀርመን እንግሊዝኛው አምድ ” ከኦነግ የተገነጠለው” ሲል ስም የሰጠው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኦሮሚያን እንደሚያውካት አስገንዝቧል። የኦሮሚያ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ግን ምስጋና ብቻ ነው ያቀረበው።

የሚዲያ ዘመቻ የሚነዛባት ኢትዮጵያ ይህንን ምርጫ እንዳታከናውን ሰፊ ተግዳሮት አጋጥሟት እንደነበር በማስታወስ ” ይባላሉ ሲሉን እዚህ ደርሰናል” ሲሉ ምርጫውን በሰላም በማካሄድ ለዓለም ትምህርት መስጠት እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በትናንት ንግግራቸው አመልክተዋል።

የጀርመን ድምጽን ጨመሮ ሌሎች ምርጫው እንደሚሰናከል ለሟርታቸው የሚስማማቸውን እየመረጡ በማነጋገር ሲዘግቡ ቢሰነብቱም ጸዳለ የምትመራው አዲስ ስታንዳርድ ግን በልዩ ሁኔታ ይህንን ሃሳብ አራማጀ እንደሆነች አቶ ጉልማ ሁንዴ በክፍተኛ ደረጃ ወቀሳ አሰምተው ተናግረዋል።

የምርጫ ቅድመ ትንተና ውጤትን ጠቅሰው ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹ እንዳሉት ሕዝ ከዚህ አዙሪትና ጭንቀት ምርጫውን አከናውኖ መውጣት ይፈልጋል። እናም ምርጫውን ለማስተጓጎል የሚቀርብ ጥሪን እንደማይሰማ ገልጸዋል። አሜሪካም ይህን መረጃ ከወሰደች በሁዋላ ” ምርጫ ቦርድን አከብራለሁ፣ መጀመሪያ ምርጫ” ማለቷን ተከትሎ ” ከምርጫው ባለቀ ሰዓት ለማፈንገጥ ዘግጅት ላይ የነበሩ ” ምርጫውን ለቀን አንወጣም” ሲሉ በህዝብ ጫና አሳባቸውን አምክነዋል።

በኦሮሚያ ምርጫ የማይደርገው ለሰባት የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብቻ ሲሆን በሌሎቹ ስፋራዎች ሁሉ ያለአንዳች ችግር ምርጫ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል። ይህን መረጃ ዋቢ የማያደርጉት ሚዲያዎች ረብሻ ሊኖር እንደሚችል በስፋት ቢዘግቡም፣ የክልሉ መንግስት ዛሬ ባወታው መግለጫ ምስጋና እንጂ ስጋትን አላጎላም። እንደተለመደው የህዝብን ድጋፍና ትብብር ግን ጠይቋል። መግለጫው እንዲህ ይነበባል።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ

በሀገራችንና በክልላችን ታሪካዊ ምርጫ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ይህን ስድስተኛ ዙር ምርጫ ሰላማዊ፤ዲሞክራሲያዊ፤ፍትሃዊ እና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረዉ ከህብረተሰቡ፤ከፖለቲካ ፓርቲዎች፤ከግል እጩዎች፤ከምርጫ አስፈጻሚዎችና ከመንግስት ከፍተኛ ሀላፊነት እንደሚጠበቅ መግለጫዉ አትቷል፡፡ከምንም በላይ ሰላማ ለሁሉ ነገር መሰረት በመሆኑ መንግስት ሁለኩንም የህብረተሰብ ክፍል በማስተሳሰር የምርጫዉን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ሲያደርግ የነበረዉን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ተጨባጭ ስራ ዉስጥ ገብቷል፡፡

ምርጫ በሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች ለምርጫ ስኬታማነት የሚንቀሳቀሱ አካላት በጥምረት እንዲንቀሳቀሱና ዜጎች ካለምንም ስጋትና ፍራቻ ድምጻቸዉን እንዲሰጡ መንግስት ሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጣ መሆኑም ተመልክቷል መግለጫዉ፡፡

በተለይም የፌደራልና የክልል የጸጥታ አካላትን በማቀናጀት አሰማርቷል፡፡የምርጫ ህጎችና ስነ-ምግባሮችን እንዲሁም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚሰጠዉን መመሪያና አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ የተሰጣቸዉን ተልዕኮ በታማኝነት እየተወጡ መሆናቸዉንም ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም የምርጫዉን ዋዜማ፤በምርጫዉ ዕለት እንዲሁም ከምርጫዉ በኋላ የተረጋጋ ሰላም እንዲኖር ለሚመለከታቸዉ አካላት ተልዕኮ ከመስጠት ባለፈ ከሰፊ የህብረተሰብ ጋር ዉይይት በማድረግ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

በዚሁ መሰረት ሰፊዉ ህዝብ ሶስት ሀላፊነቶችን ወስዷል፡፡አንደኛዉ ምርጫዉ በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር መቀናጀትና ምርጨጫዉን ለማወክ የሚጥሩ አካላትን ማጋለጥ፤ሁለተኛዉ የምርጫ ካርድ እንደወሰደዉ ሁሉ ካለምንም ስጋትና ፍራቻ ይበጀኛል የሚለዉ አካላ በነጻነት መምረጥ ይጠበቅበታ፤ሶስተኛ የምርጫዉ ዉጤት ስልጣን በተሰጠዉ አካል ይፋ እስኪሆን ድረስ በትዕግስት በመጠበቅ ሊፈጠር ለሚችለዉ ወዥንብር ጆሮ ሳይሰጥ ድምጹን ማስከበር አለበት፡፡

ከምንም በላይ በቅድመ ምርጫ ወቅት በነበረዉ እንቅስቃሴ የክልላችንም ሆኑ የመላዉ ሀገሪቱ ወጣቶች ላሳዩት መልካም ስነ ምግባር መንግስት ትልቅ አክብሮትና ምስጋና አለዉ፡፡ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ትልቅ እምንት መንግስት አለዉ፡፡በመጨረሻም ስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ አባቶቻችን ያስረከቡንን ጠንካራና ሉዓላዊት ሀገርን መጽኑ መሰረት ላይ ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ያለዉ መግለጫዉ መንግስት የምርጫዉን ደህንነት ለማረጋገጥ ያለዉ ዝግጁነት የላቀ መሆኑንመግለጽ ይወዳል፡፡

ጠንክረን በመስራት የሰፊዉን ህዝብ አሸናፊነት እናረጋግጣለን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትሰኔ 2013ፊንፊኔ

Exit mobile version