Site icon ETHIO12.COM

ጌታቸው ረዳ ለድል ወሬ ሲጠበቁ፤ ሮሮ አሰሙ፤ መንግስት 24 ሚሊዮን ችግኝ ይተክላል

ኢትዮ12 ዜና – ነገ ዘመቻ ዋለልኝ በትግራይ ” አንጸባራቂ” የተባለ ድል እንደሚያስመዘግብ በሚጠበቅበት የድል ብስራት ዋዜማ ላይ “The international community is our first line defense” ሲሉ ተገዳላይ ጌትቸው ረዳ ካሉበት ግንባር በቲውተር አመለከቱ። “የዓለም ዓቀፉ ማህበተርሰብ የመጀመሪያ ደረጃ መከላከያችን ነው” ያሉት ጌታቸው ረዳ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ “እርምጃ መውሰድ አለበት” ብለዋል። ለምን ይህን እንዳሉ ግን አላብራሩም። ውጤቱን በቀናት ውስጥ ይፋ እናደርጋለን ስላሉት አዲስ ዘመቻ ይህ እስከታተም ድረስ አልተነፈሱም። መንግስት 24 ሚሊዮን ችግኝ እንደሚተክል አስታወቀ።

ይህን ከማለታቸው አስራ አምስት ሰዓት በፊት የምዕራብ ሚዲያ ጋዜጠኛች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን መልዕክት ማስተላለፍ እንደምፈልጉ ጠይቀዋቸው፣ ተገዳላይ ጌታቸው “እኛ የትግራይ መሪዎች በትግራይ የሚፈጸመውን ፍትሃዊነት የጎደለው ተግባር ስለምታጋልጡ አድናቆት አለን፤ እውቅናም እንደሚሰጠዋለን” ብለው መመለሳቸውን ቲዊት አድርገዋል። ለሶስት ተከታታይ ቀናት የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት መግቢያ መውጫ እንዳሳጣው ሲያስታውቁና በምርጫው ቀን ዋዜማ ላይ ይሰማል ስለተባለው ድል ለሚዲያ ምን መረጃ እንደሰጡ አልተነፈሱም። የአገር መከላከያ አቶ ጌታቸው ከምሽግ የመሰረቱትን የመገናኛ የዋሻ ቢሮ ተቆጣትሮ ንብረታቸውን መውሰዱንና እሳቸውም ለጥቂት ማምለጣቸውን አስመልክቶም ምላሽ አልሰጡም።

ለጋዜጠኞች መልስ የሰጡትን ከገለጹ በሁዋላ ባሰፈሩት የቲውተር ሌላ ሃሳብ “እስከምንረዳው ድረስ  ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የእኛ የመጀመሪያ የመከላከያ መስመር እንጂ የመጨረሻችን አይደለም። ህዝባችን፣ የትግራይ ሰራዊትና ምክንያታችን የመጨረሻው የመከላከያ መስመሮቻችን ናቸው። ለትግራይ ማሸነፍ ዋናው እውነት ይህ ነው ብለዋል። ይህን ያሉት ጣልቃ ይገባል የተባለው የሰሜን ቃል ኪዳን አገሮች ህብረት NATO ዝም በማለቱ የተነሳ ይሁን በሌላ የተለየ ምክንያት የታወቀ ነገር የለም። የሰላም አስከባሪ እንዲገባ በጸጥታው ምክር ቤት የተሞከረው ሙከራ ከመክሸፉ ጋር ተዳምሮ ሊሆን እንደሚችል ግን አብዛኞች ይገምታሉ።

ለምዕራብ አገራት ጋዜጠኞች የመለሱትን መልስ ከጠቆሙ በሁዋላ ወዲያው ባሰራጩት ቲዊት “የውግዘት መግለጫዎች ብቻቸውን በቂ ናቸው ብለን አናምንም” አሉ ጌታቸው ረዳ፣ “እርምጃ የግድ ይላል” ሲሉ አስከተሉ። በማውገዝ ረገድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያከናወነውን ተግባር እንደሚያደንቁ አስታውቀው፣የዛኑ ያህል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይና ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ እያምታቱ መሆኑን እንደሚገነዘቡ አመልክተዋል።

ጌታቸው ረዳ የድል ብስራት እንደሚያሰሙ ” እርግጠኛ ነኝ” ብለው ኦስሎ ላሉት አጋራቸው ፕሮፌሰር ሼትል በስልክ ቃል ገብተው ነበር። ይህን መረጃና በትህነግ ሚዲያዎች በቀረቡ አዋጊዎች በይፋ እንደተብራራው በደጋፊዎችም ዘንዳ ምርጫው በትህነግ የድል ዜና ወደ መርዶ ይቀየራል የሚል ተስፋ አሳድሮ ነበር።

ለሶስተኛ ተከታታይ ቀን አራተኛ፣ ሶስተኛ አንደኛ የሚባለው የትህነግ  ሰራዊት ጥቃቱን አጠናክሮ የኢትዮጵያን ሰራዊት እየደመሰሰ መሆኑንን አቶ ጌታቸው ካሉበት ሲያመልክቱ ያሉት “ዱላውን ያልቻለው ወንጀለኛ ” ያሉት የአገር የመከልከያ ጦር ህጻናትና ያልታጠቁ እናቶችን እንደሚገድል ነው። መከላከያ በበኩሉ ” ውጊያ ሳይሆን እያሳደዱ መቃረም ነው” ሲል ትህነግ ግንባር ገጥሞ የመዋጋት ሃይሉ እንዳከተመ ሲያስታውቅ በሰሞኑ የመቃረም አሰሳ ሕጻናት እጃቸውን መስጠታቸውን ይፋ አድርጓል። ከዚያም በላይ ምርጫ ብቻ ሳይሆን ከምርጫው ጎን ለጎን 24 ሚሊዮን በላይ መራጭ ህዝብ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ዐሻራውን እንደሚያኖር እየተጠቆመ ነው።

ይህን ዜና የተከታተሉ አስተያየት ሰጪ ” የነገው ምርጫ ከዚህ ቀደም የተደረጉትን አምስት ምርጫዎች መቀመቅ የሚከት፣ መድበል ፓርቲና የጥምር መንግስት ሃሳብ የሚሰርጽበት፣ ዴሞክራሲ የሚወለድበት፣ የትህነግ ትርክትና መርዝ የሚነቀልበት፣ኢትዮጵያ አዲስ ሙሽራ የምትሆንበት ነው” ይሉና ትህነግ ይህ እንዳይሆን ማትቃት ሞክሮ ሳይሳካለት ጩኸት ማሰማቱ መቃብሩ እየራቀ ሲሄድ ከማየቱ የተነሳ እንደሆነ ይገልጻሉ። ” አክቲቪስ ነኝ የምትለ ጂጂ ኪያ እንኳን የማትለውን የወረደ ክስ ያሰራጩት የፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳደረጉት አይነት አዲስ ትንግርት ፈጥረው ብቅ ለማለታቸው ጩኸቱ አመካች ነው” ሲሉ አስተአየታቸውን ይጨርሳሉ።

ትህነግ ቀድሞ አጀንዳ በማስቀመጥና በምሳሳት ፕሮፓጋንዳ የተካነ መሆኑንን የሚገልጹ መንግስት ከምርጫው በሁዋላ ከተባበሩት መንግስታት ጀምሮ በተለያዩ አገራት ያሉትን በውል ከትህነግ ጋር ሲሰሩ የነበሩትን ዲፕሎማቶች ማስወገድ እንዳለበት ከወዲሁ እየተገለጸ ነው። ኢትዮ12 ዜና

Exit mobile version