Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካዊው ምርጫ ታዛቢ ሞት ተፈጥሯዊ እንደሆነ አመላካች መረጃ ተገኘ

ፖሊስ በሰጠው ቅድመ የምርመራ ውጤት መረጃ ምርጫ ለመታዘብ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አሜሪካዊው ህይወታቸው አልፎ በተገኙበት ሆቴል ሲፈተሽ በኢሶቻቸው ውስጥ ራሳቸውን ከሚገልጹ ሰነዶች በተጨማሪ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ መድሃኔቶች መገኘታቸውን አመልክቷል። በርግጠኛነት ምክንያቱን ለማወቅ ግን የአስከሬን ምርመራ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑን ገልጿል።

በአሜርካ የትህነግ ደጋፊና የፕሮፓጋንዳ ክንፎች አሜርካዊው የምርጫ ታዛቢ በሰው እንደተገደሉ፣ ተገድለው የተገኙበት አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና አሜሪካ ለዜጋዋ ሞት አስቸኳይ ማብራሪያና ማታራት እንደምታደርግ፣ ይህም በምርቻው ላይ አሉታዊ ሚና እንዳለው እየተቀባበሉ የዜናውን ግልባጭ ሲያሰራጩ ነበር።

በውጭ አገር ታዛቢው የአሟሟት ሁኔታ ላይ ምርምራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት፣ ሙዚቃ፣ ትያትርና የስፖርት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ እንዳሉት ግን “ትናንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍሉ ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል”፤ ሟች ከአልጋቸው ወድቀው ነበር የተገኙት።

የሆቴሉ የጽዳት ሠራተኛ ትናንት ጠዋት አንድ ሠዓት ገደማ አሜሪካዊው ያረፈበትን የመኝታ ክፍል ለማጽዳት ስትገባ ያየችውን ገልሳ ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥታለች። ኮማንደሩ እንዳሉት ፖሊስ መረጃውን እንዳገኘ ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱንና አሜሪካዊው ከአልጋው ላይ ወደ መሬት ወድቆ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ ጥቆማ የሰተችውን የሆቴሉን የጽዳት ሰራተኛ ቃል በቃል ጠቅሰው አመልክተዋል።

በሟች ኪስ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ የምርጫ ታዛቢ ወረቀት (ባጅ)፣ የተለያዩ መታወቂያዎችና መንጃ ፈቃድ መገኘታቸውን ያስታወቁት ኮማንደሩ፣ መንጃ ፈቃዱ “በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ብሔራዊ የድራይቪንግ ላይሰንስ” እንደሚል አስታውቀዋል። በተጨማሪም አሜሪካዊው ከጤና ጋር በተያያዘ ይጠቀሙባቸው የነበሩ “በርካታ” መድሃኒቶችን ፖሊስ ማግኘቱን ጠቁመዋል። በዚሁ መነሻ ” ምናልባት ሁኔታው ሲታይ በተፈጥሮ የሞቱ እንደሚመስል፣ ነገር ግን ትክክለኛው መረጃ ከአስከሬን ምርመራ ውጤት በኋላ የሚታወቅ ነው” ብለዋል።

“በአሜሪካዊው ዜጋ ሰውነት ላይ ምንም አይነት የአካል ጉዳትና ቁስለት አልተገኘም” ብለዋል ኮማንደር ፋሲካ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን በአሜሪካዊው ዜጋ አሟሟት ላይ በጣምራ ምርምራ እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል። ፖሊስ አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግም አክለዋል።

የካርተር ሴንተር ፕሮግራም በኢትዮጵያ በይፋዊ የትዊተር ገጹ ዛሬ ማለዳ ባወጣው መረጃ በራዲሰን ብሉ ሆቴል ሕይወቱ ያለፈው የተቋሙ የአዲስ አበባ የፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ዶክተር ጆን ማርሽ መሆናቸውንና ሕይወታቸውም ትናንት እንዳለፈ ገልጿል።

“በኢትዮጵያ በጆን ማርሽ ድንገተኛ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል፤ ጆን ማርሽ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ነው” ሲል የካርተር ሴንተር አመልክቷል።የካርተር ሴንተር ለዶክተር ጆን ማርሽ ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል።

ትክክለኛው ዜና ከተሰራጨ በሁዋላም ቢሆን ሃሰተና ዜና ያሰራጩ ክፍሎች ማስተባበያ ወይም በዚናቸው ላይ ማስተካከያ አላደረጉም።

Exit mobile version