ETHIO12.COM

የቅዳሜ ቅምሻ- ኮሮና አምስት ሚሊዮን አዳዲስ ሚሊየነሮች ፈጠረ

ብዙዎችን ያደኸየው ይህ ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሊየነሮችን ቁጥር ከ5.2 ሚሊዮን ወደ 56.1 ሚሊዮን ማሳደጉን ክሬዲት ስዊስ የተሰኘው የምርምር ተቋም አስታውቋል።

በ2020 በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አዋቂ ሰዎች ውስጥ አንድ በመቶው ለመጀመሪያ ጊዜ ሚሊየነር የሆነበት ዓመት ነበር።

ለሀታሞቹ የበለጠ ሀብት ማግኘትም የአክሲዮን ገበያ በቶሎ ማገገም እና የቤት ዋጋ መናሩ ምክንያት ሆኗል።

በኮቪድ-19 ወቅት የተፈጠረው ሀብት ወረርሽኙ ካስከተለው የኢኮኖሚ ችግር ጋር “ምንም የሚያያይዘው ነገር የለም” ሲሉ ተመራማሪዎቹ ገልፀዋ።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና የ’ግሎባል አሴት ሪፖርት’ የተባለውን ዘገባ ያዘጋጁት አንቶኒ ሽሮክ በበኩላቸው ወረርሽኙ “በዓለም ገበያዎች ላይ አንገብጋቢ ነገር ግን የአጭር ጊዜ ተፅእኖ” እንዳለው ገልፀው፤ ይህ ግን “በሰኔ ወር 2020 መጨረሻ በጣም ተለውጧል” ብለዋል።

“ዓለም አቀፉ ሀብት በእንዲህ አሰጨናቂ ጊዜ ሳይናጋ መቆየቱ ብቻ ሳይሆን በእውነቱ በዓመቱ ሁለተኛ አጋማሽ በፍጥነት ጨምሯል” ሲሉ ተናግረዋል።

ሆኖም በአውሮፓውያኑ 2020 በአዋቂዎች መካከል ያለው የሀብት ልዩነት እየሰፋ ሄዷል ያሉት ሾሮክስ እንደ የቤት ዋጋ ጭማሪ ያሉ የቋሚ ንብረቶች ዋጋ ጭማሪዎችን ከትንተናው አውጥተን ከተመለከትናቸው “በዓለም አቀፍ ደረጃ በየቤቱ ያለው ሀብት ወድቆ ሊሆን ይችላል” ብለዋል። ቢቢሲ እንደዘገበው


የወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በዓለም ላይ ያለው አጠቃላይ ሀብት በ7.4 በመቶ እድገት አሳይቷል።

ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ10 ሺህ አስከ 100ሺህ ዶላር ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከሦስት እጥፍ በላይ የጨመረ ሲሆን፤ ይህም በ2000 (እአአ) 507 ሚሊዮን የነበሩት በ2020 አጋማሽ ላይ 1.7 ቢሊዮን ሰዎች ይህን ያህል ገንዘብ አላቸው ማለት ነው።

ለዚህም ምክንያቱ “በማደግ ላይ ያሉ አገራት ሀብት እያፈሩ መሆናቸውና በታዳጊ አገራት ውስጥ የሚገኙ መካከለኛ ገቢያላቸው ሰዎች ቁጥር እያደገ በመሆኑ ነው” ተብሏል።

የክሬዲት ስዊስ ባልደረባ የሆኑት ናኔት ሄሽለር እናዳሉት “በወረርሽኙ ወቅት በመንግሥታት በኩል ግለሰቦችንና የንግድ ተቋማትን ለመደገፍ የተሰጡ ድጋፎችና የወለድ መጠን እንዲቀንስ መደረጉ ከባድ ዓለም አቀፋዊ ቀውስ እንዳይከሰት አድርጓል” ብለዋል።


የደቡብ አፍሪካ የህግ አስከባሪዎች ባለፉት ጥቂት ወራቶች ብቻ ከ1ነጥብ 2ቢሊየን በላይ ግምት ያለው ኮኬይን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ፡፡

የህግ አስከባሪዎቹ ይህንን ያህል መጠን ያለው ኮኬይን በቁጥጥር ስር ያዋሉት በሀገሪቱ በሶስት ዋና ዋና ከተሞች ነው ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ የህግ አስከባሪዎች ከባህር እና ከወንጀል መከላከል ከፍተኛ መርማሪዎች ጋር በጋራ ባከናወኑት ጥብቅ ክትትል ነው ኮኬይኑ ሊያዝ የቻለውም ተብሏል፡፡

የደርባን ፖሊስ አዛዥ ኮረኔል ፊላኒ ኑኳላሲ እንደተናገሩት ኮኬይኑ የእንስሳት መኖ በጫኑ ኮንቴነሮች ስር ተጭኖ ወደ ከተማ ሊገባ ሲል በህብረተሰቡ እና በፖሊስ ጥምረት ሊያዝ ችሏል ብለዋል፡፡

26 አይነት የንግድ ምልክት የተደረገባቸው የኮኬይን ምርቶች በተለያዩ ሻንጣዎች ተደርገው ነው በወቅቱ ሊያዙ የቻሉት ሲሉም ተናግረዋል፡፡

እያንዳንዳቸው ሻንጣዎች 541 ኪሎግራም የሚመዝኑ ሲሆን በግምት እስከ 243 ሚሊየን የደቡብ አፍሪካ ራንድ እንደሚያወጡ ነው የተነገረው፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው የኮኬይን ምርት በሀገር ውስጥ ለገበያ የሚቀርብ አልነበረም ያሉት የፖሊስ አዛዡ ወደ አውሮፓ ሀገራት ለማስተላለፍ የተዘጋጀ ነበር ብለዋል፡፡ Ethio FM

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በመግቢያ መንገድ ላይ ባለ ዛፍ ምክንያት በጎረቤታሞች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት አንድ ዛፍ በግማሽ እንዲቆረጥ ተደረገ።

በዎተርቶርፕ ሼፊልድ ነዋሪ የሆኑት የ56 ዓመቱ ባሐራት ሚስትሪ እንደሚሉት ጎረቤታቸው ከእርግቦች ጎጆ በሚወጣ ቆሻሻ ምክንያት ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

የዛፎችን ቆራጭ ከመጠራቱ በፊት ሁለቱም ጎረቤታሞች “በሠላማዊ መንገድ” መፍትሔ ላይ ለመድረስ ቢሞክሩም ሌላኛው ነዋሪ ዛፍ ቆራጭ ጠርተዋል ብለዋል።

የሚስትሪ ጎረቤት ባለመገኘቱ አስተያየቱን ማካተት አልተቻለም።

ጎረቤታቸው ባልና ሚስቶች መጋቢት መጀመሪያ ላይ ዛፉ እንዲቆረጥ ጠይቀው እንደነበር ሚስትሪ ተናግረዋል።

በመቀጠልም ዛፉን ለመከርከም ወይንም ወፎቹ ጎጆዋቸውን እንዳይቀልሱ ለመከላከል መረቦችን ለማልበስ “በርካታ ውይይቶች” ተካሂዷል።

ሚስትሪ ለዛፍ ባለሙያዎች እና አትክልተኞች ጥያቄዎችን ያቀረቡ ቢሆንም የ28 ዓመቱ ጎረቤታቸው የራሱን ዛፈፍ ቆራጭ በመጥራት እርምጃ ወስዷል። “መጀመሪያ ሲያደርገው እኛ እንደተቆጣን መገመት ትችላላችሁ” ብለዋል። “በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ከሁለት ቀናት በኋላ ትንሽ ተረጋጋን።”

የዛፉ ፎቶዎች በበይነ መረብ ከተለቀቁና ብዙዎች ከተጋሯቸው በኋላ ዛፉ የቱሪስት መስህብ ሲሆን ብዙዎች ሊጎበኙት ወደ አካባቢው አቅንተዋል። ሌላኛው ጎረቤታቸው ብራያን ፓርክስ ጉዳዩ “በትንሹ እየተጓዘ” እንደነበረ ገልፀው “ለሁለቱም ማዘን አለባችሁ” ብለዋል።

“በጣም አስከፊ ይመስላል። አሁን ተጠናቅቋል። መቀልበስ አይችሉም። ሁለቱ ጎረቤታሞች ክፉኛ ነበር የተቃቃሩት፤ ጦርነት ማለት ይቻላል” ብለዋል ጎረቤታሞቹን አለምግባባት ሲገልጹ። እዚያው ሰፈር የምትኖረው አን ዊልስ በበኩሏ ጎረቤታሞቹ ከዚህ ቀደም የልጆችን ድግስ በአንድነት እንዳዘጋጁ ተናግራለች።

“እስከማውቀው ድረስ በጥሩ ሁኔታ አብረው እንደኖሩነው። እኛ በመቶዎች የሚቆጠሩ ብዙ ርግቦችን አግኝተናል። በአንድ አገር ውስጥ ስለምንኖር እነዚህን ነገሮች መቀበል ነበረባቸው” ብላለች። ዛፉ በሳይደርቅ መቆየት ካልቻለ መቆረጥ ሊኖርበት እንደሚችል ሚስትሪ ተናግረው ሆኖም የበለጠ ሊቆረጥ ወይም ሊስተካከል ይችላል የሚል እምነት አላቸው። ባለቤታቸው ደግሞ ነገሩ “ወደዚህ ደረጃ በመድረሱ በእውነት በጣም አዝናለሁ” ብለዋል።

‹በ12 ዓመት ውስጥ በናይጄሪያ ከ 300 ሺህ በላይ ህፃናት በግጭት ምከንያት ተገድለዋል ››

ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመላከተ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኘው ሀገር ናይጄሪያ በሰሜንናዊው ምስራቅ አካባቢዋ በአክራሪው ቦኩሃራም ጥቃትን ጨምሮ ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ባልሆነ ጥቃት ከ300 ሺህ በላይ ህፃናት ለህልፈት እንደተዳረጉባት ሪፖርቱ ያመላክታል፡፡በአካባቢው ከ 350 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መሞታው የተገለፀ ሲሆን ከነዚህም አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ከ 5ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው ብሏል፡፡ በዩኤን ሪፖርት እንደተመላከተው 350 ሺህ ከሚሆኑት ዜጎቿ ውስጥ 314 ሺህ የሚሆኑት ቀጥተኛ ባልሆነ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል፡፡በአዲሱ ጥናት ላይ በተጨማሪ የተመላከተው የሃገሪቷ ህዝብ የፀጥታ ስጋት፣ የስራ አጥነት እና የኑሮ መናር፣ በአማፅያን መጠቃት ተደማምሮ ህዝቡን ወደ አደባባይ እንዲወጣ እያረገው ነውም ተብሏል፡፡ የአልጄዚራ ዘገባ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2009 ዓ.ም በአክራሪው ቦኩሃራም ከ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መገደላቸውን አስታውሷል፡ እትዮ ኤፍ ኤም

ናይሮቢ፤ በኬንያ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ 17 ወታደሮች ሞቱ

ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወጣ ብሎ በደረሰ የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ 17 ወታደሮች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ ባለሥልጣን አስታወቁ። ሌሎች ከአደጋው የተረፉ ስድስት ሰዎች ደግሞ ከስፍራው መወሰዳቸውንም አመልክተዋል። ማንነታቸው እንደገለጽ ያልፈለጉት የፖሊስ ባለሥልጣኑ አደጋው ባጋጠመው ሄሊኮፕተር ውስጥ የነበሩት ወታደሮች ለስልጠና በመጓዝ ላይ እንደነበረውም ለአሶሲየትድ ፕረስ ገልጸዋል። የኬንያ ጦር ኃይል የሄሊኮፕተሩን መከስከስ በማረጋገጥ አደጋ የደረሰባት የኬንያ አየር ኃይል Mi 171 E ሄሊኮፕተር መሆኗን ቢገልጽም ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥቧል። ሆኖም መረጃውን ለዜና ወኪሉ የገለጹት የፖሊስ ባለሥልጣን ዛሬ ጠዋት በተከሰከሰችው ሄሊኮፕተር ውስጥ 23 ወታደሮች እንደነበረው አመልክተዋል። DW

ቱኒዝ፤ የቱኒዚያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች 267 ስደተኞችን አተረፉ

የቱኒዚያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ጀልባቸው ተሰብሮ ሊሰጥሙ የነበሩ 267 ስደተኞችን ማትረፋቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። አብዛኞቹ የባንግላዴሽ ዜጎች መሆናቸው የተነገረው ተሰዳጆች ቤን ጉዌርዳኔ ከተባለችው የባሕር ወደብ ከተማ ወደ አውሮጳ ለመሄድ አልመው የተነሱ እንደነበሩ በስፍራው የሚገኘው የቀይ ጨረቃ ኃላፊ ለጀርመን የዜና ወኪል ዲፒኤ ገልጸዋል። የሰብዓዊ ርዳታ ድርጅቱ እንደሚለው እንዲህ በርካታ ስደተኞች በአንድ ጊዜ የማዳን ዘመቻ በቱኒዚያ የባሕር ዳርቻ ሲገኙ የመጀመሪያ ነው። ከተሰዳጆቹ አብዛኞቹ ከባንግላዴሽ፤ ሦስቱ ደግሞ ከግብፅ ሲሆኑ ዝዋራ ከተባለው የሊቢያ ከተማ የመጡ መሆናቸውንም የረድኤት ድርጅቱ አስታውቋል። ምናልባት ባሕር ውስጥ የሰመጠ እንዳለ ግን እስካሁን አለመታወቁንም ዜናው አመልክቷል። በየዓመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ቱኒዚያ እና ሊቢያን አቋርጠው ወደ አውሮጳ ለመሻገር ይሞክራሉ። አብዛኛውን ጊዜም ለባሕር ላይ ጉዞ አደገኛ የሆኑ የእንጨት እና የጎማ ጀልባዎችን ይጠቀማሉ።

Exit mobile version