Site icon ETHIO12.COM

ኮረምን ለመያዝ ጥቃት የከፈተው የትህነግ ሃይል መመታቱ ተሰማ

የትህነግ ሰራዊት ኮረምን ለመቆጣጠር ያደረገው ማጥቃት ሳይሳካለት መቅረቱ ተሰማ። ትህነግ ከተመታ በሁዋላ ለመጀምሪያ ጊዜ ራሱን አጠናክሮና ጉልበት ሰብስቦ ኮረምን ለመያዝ ያደረገው ሙከራ የከሸፈው በአማራ ልዩ ሃይል እንደሆነ ነው የተጠቆመው።

በኢትዮጵያዊው ጀግና አሉላ አባ ነጋ ስም ተሰይሟል የተባለው ዘመቻ ካላ የሆነው የዳግም ጥቃት በራያ፣ ባላና ወፍላ አቅጣጫ ነበር የተከፈተው። አስቀድሞ በጥብቅ ቁጥጥር ላይ የነበረው የአማራ ልዩ ሃይል ሙከራውን ማምከን ብቻ ሳይሆን በዘመቻው ትህነግ ባሰለፈው ሃይል ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል። በአሃዝ ግን አልተገለጸም። የተማረኩ መኖራቸውም ተመክቷል።

ትህነግ ሰሞኑንን በሰሞኑ የተለያዩ አውዶች ውጊያ መክፈቱን ጠቅሶ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ መደምሰሱን አስታውቋል። ስለ ኮረም ግንባር ግን ያለ ነገር የለም። የጦርነት ቀጠናዎችን ማስፋትና ማርዘም በሚለው ስልት በተመሳሳይ ጊዜ በተለያዩ ግንባሮች ጥቃት ለመሰንዘር የታቀደው አርሶ አደሩ እንዲያርስና አካባቢው ከስጋት ነጻ እንዲሆን በመንግስት በኩል ፍላጎት በመኖሩ ሰራዊቱ እንዲለቅ መውሰኑንን ተከትሎ ነው።

ከዛ በፊት የትህነግ አመራሮችን አሦ የመያዙ ዘመቻ በስፋት ሲካሄድ ስለነበር ውጊያውን ማስፋትና በየቦታው ራሱን ደብቆ የነበረው ሃይል በያለበት ትንክሳ እንዲኢያካሂድ መደረጉን ነው ከመከላከያ ወገን የተጠቀሰው።

የአማራ ክልል በይፋ ባይናገርም ኮረምን ለመያዝ ሰፊ ሃይል ይዞ የመጣው የትህነግ ሃይል መደምሰሱን ለክልሉ ሃላፊዎች ቅርብ የሆኑ የማህበራዊ ገጽ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል። የትህነግ ሰዎችም ኮረምን ለመያዝ ማቀዳቸውን ከመግለጻቸው ውጪ እቅዳቸው ስለመሳካቱ የግንባሮቹን ስም ጠቅሰው ይህ እስከታተመ ድረስ ያሉት ነገር የለም።

ከራያ አስመላሽ ኮሚቴ አንዱ ደጀኔ አሰፋ ስለ ኮረሞ ዘመቻ አስመልክቶ ሰሞኑን ከሃውዜን እስከ ቆላ ተንቤን: ከአገረ ሰላም እስከ አግበ የጭላ: ከብዘት እስከ እንጥጮ እስከ ራማ ድረስ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ባካሄደው የአሰሳ ዘመቻ የተቀጠቀጠው የጁንታው ርዝራዥ ማምለጫ ሲያጣ እንደለመደው ጥሻ ለጥሻ በመሸሽ ሸጡን ተከትሎ ወደ አበርገሌ እና ወደ ኮረም ዙሪያ በመምጣት ተደብቆ እንደከረመ የአካባቢውን ምስክሮች ተቅሶ አስታውቋል።

ዘወትር ሃሙስ የሚቆመውን የኮረም የገበያ አስታኮ ጁንታው ሰርጎ ገቦችን ገበያተኛ በማስመሰል በማለዳ ወደ ኮረም ከተማ አስገባ። ቀጥሎም የጁንታው ርዝራዥ ሃይል አድነባ ተብሎ በሚጠራው የኮረም ገጠር አካባቢ ጥይት መተኮስ ጀመረ። ይህ ማለት በከተማ ውስጥ እና ከከተማ ውጭ ጥቃት በመክፈት ከእጁ የወጣውን የራያን ህዝብ ለመበቀል ያለመ እንደነበር ደጀኔ ያስረዳል።

ዲያ ይህን የጁንታውን ሃሳብ እና እንቅስቃሴ የተገነዘበው የራያ ኦፍላ ኮረምን እና አካባቢውን እያስተዳደረ ያለው ኮማንድ ፖስት ሦስት ነገሮችን በአስቸኳይ ማከናወኑ ደጀኔ ገልጿል። እነሱም

1ኛ) የዛሬው የኮረም ገበያ ዛሬ ጧት ሶስት ሰዓት ገደማ በፍጥነት እንዲፈርስ አደረገ

2ኛ) ህዝቡ ወደ ቤት እንዲገባ አዘዘ:: ከገጠር ለገበያ የሚገባውንም ባለበት እንዲቆይ አደረገ

3ኛ) ገበያው እንዲፈርስ እና ህዝቡ ወደ ቤት እንዲገባ ካደረገ በኃላ አድነባ አካባቢ የሽፍታነት ተግባር ሲፈፅም የነበረውን ርዝራዥ የጁንታ ሃይል ዛሬ ከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ጀግናው ሰራዊታችን አይቀጡት ቅጣት በመቅጣት የሞተው ሞቶ የተማረከው ተማርኮ የተረፈው ፈርጥጦ ወደ ዛታ እና ወደ ሰቆጣ መስመር ሸሽቷል። የሙት ቁጥሩን በውል ማረጋገጥ ባልቻልም ተማርከው ወደ ወልዲያ የተወሰዱት ግን 29 መሆናቸውን የአይን እማኞች አረጋግጠውልኛል። ሲል ደጀኔ ጽፏል።

በሌላ ዜና ለተሳፋሪዎች ጥንቃቄ ሲባል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላልተውሰነ ጊዜ ወደ ትግርያ እንደይበር አስታውቋል። አየር መንገዱ ወደ አመራ በረራ መጀመሩ ይታወሳል። በትናትናው እለት የትህነግ ሃይል መትቼ ጣልኩት ያለው ሄሪኩለስ የመጓጓዛ የጦር አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር እንጂ ተመቶ እንዳልወደቀ አስታውቋል።

Exit mobile version