Site icon ETHIO12.COM

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

የትግራይ ተወላጁ ታዋቂው አክቲቪስት ናትናኤል አስመላሽ፣ ለትግራይ ህዝብ ድጋፍ አሰባስቦ በመሄድ፣ እግረ መንገዱንም በትግራይ ክልል እየተከናወነ ያለውን ሁኔታና በአካል ተገኝቶ ያረጋገጠውን እውነት ለህዝብ ይፋ አድርጓል።

ዋና ዋና ያጋለጣቸው #እውነታዎች….

√ ህወሓት ‘የትግራይ ህዝብ ጠላት ናቸው’ ብሎ በቅደም ተከተል ያስቀመጣቸው፡ ብልፅግና፣ ኤርትራ፣ እና አማራ ናቸው። ነገር ግን የትግራይን ህዝብ እየገደለ፣ እያስገደለ፣ ሴቶችን እየደፈረ ያለው እራሱ ህውኃት ነው። ልጆችን ለውጊያ አንሰጥም ያሉ እናቶች፣ ከልጆቻቸው ፊትም ተደፍረዋል።

√ ህወሓት አሁንም በየገጠሩ የመከላከያ ደጋፊ፣ የሻቢያ ደጋፊ ናቸው የሚላቸው ወጣቶች ይገድላል፣ ዋሻ ወስዶ ያስራል፣ ከዛም አልፎ ቤተሰቦቻቸውን ከ30 ሺ እስከ 200 ሺ ብር ድረስ ይቀጣል።

√ በተለይ በምስራቅ ትግራይ አካባቢዎች የአዲግራት፣ የአፅቢ እና የውቅሮ ህዝብ ‘ከድሮውም የኢህአፓ ደጋፊ በመሆኑ’ ዛሬም ህወሓት እንደ ጠላት የሚያየው ህዝብ ነው። በእነዚህ አካባቢዎች ልጆቻቸውን ‘ለውጊያ አንሰጥም’ ያሉ እናቶች በአደባባይ እየተገደሉ ነው። በተለይ አዲግራትና ውቅሮ እራሱ ህወሓት የመከላከያና የሻቢያ ዩኒፎርም እያለበሰ ሴቶችን ያስደፍራል። አልዘምትም ያሉ ወጣቶችንም ያስገድላል።

√ ህወሓት ከዚህ በኋላ አንዲት ቀበሌም የሚይዝበት አቅም የለውም። በየከተማው ‘ክብሪት’ ብለው የሰየሟቸውን የከተማ ወጣቶች በሰርግ እና ልዩ ልዩ ማህበራዊ ስብስቦች ላይ በመግባት ጥይት ተኩሰው ህዝብ ከማሸበር ውጭ፣ የረባ ትግል አያደርጉም። ከዚህ በኋላ ህወሓት ተደራጅቶ መከላከያን የመግጠም ሞራልም አቅምም የለውም።

√ በፌስቡክ የሚወራው የህወሓት ትግልን ተቀላቀሉ የሚባለው በሙሉ ውሸት ነው። በየ ገጠሩ ነው ተበታትነው ያሉት። ያው ‘አለን’ ለማለት ነው፣ በማህበራዊ ሚድያው የሚያጮሁት።

√ በአሁኑ ወቅት በየገጠሩ እናቶች ልጃቸውን ለውጊያ እንዲሰጡ እየተገደዱ ነው። ልክ እንደ 67ቱ ትግል፣ አራት ልጅ ያላት እና ሁለቱን ለውጊያ መስጠት ግዴታ ሁኗል። ልጄን አልሰጥም ያለች እናት በአደባባይ ትገደላለች። ይሄን መንግስት በአስቸኳይ መቆጣጠር ካልቻለ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ በራሱ በህውኃት የዘር ማጥፋት እየተፈፀመ ነው።

√ የውጭ መንግስታትን ተፅእኖ በተመለከተ፣ የአሜሪካ መንግስት ማእቀብ አደረገ እያሉ የሚጨፍሩ ዲያስፓራ ተጋሩዎች እራሳቸውን አይሸውዱ። ሁሉም ውሸት ነው። መቀሌ ላይ እራሴ በአካል የ #CIA ከፍተኛ ተወካዮች እና የ #INTERPOL ትላልቅ ኤጀንቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አብረው ሲሰሩ በአይኔ አይቻለሁ። በዚህ ወቅት አሜሪካም ሆኑ አለም አቀፉ ፖሊስ (Interpol) ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን ሁነው የትግራይን ህዝብ በሚደግፍበት ሁኔታ ላይ አብረው እየሰሩ ነው።

√ በአሁኑ ሰአት የትግራይን ህዝብ መከላከያ ሰራዊት እየገደለው አይደለም፣ የአማራ ልዩ ሀይልም እየገደለው አይደለም፣ የሻቢያ ወታደርም እየገደለው አይደለም። የትግራይን ህዝብ እየገደለው ያለው እራሱ ትግራዋዩ ህወሓት ነው።

√ የትግራይን እናት መርዳትና ‘ትግራይ ትስዕር’ ማለት
ይለያያል። አዲስ አበባ ላይ በየመጠጥ ቤቱ አስር አስር
ሺህ ብር መበተን ትግል አይደለም።

√ በመጨረሻም፦ በተለይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በትክክል ለህዝባቸው ለትግራይ እናት የሚያስቡ ከሆነ፣ ብልፅግናን ወይም ሻቢያን ወይም የአማራ ልዩ ኃይልን ይተውትና መቀሌ፣ አዲግራት፣ እና የትግራይ ገጠሮች ውስጥ በችግር እየተጎዳ ላለው ህዝባቸው ድጋፍ ያድርጉለት። ከዛ ውጭ ‘አደይ ትግራይ’ እያሉ መዝፈን፣ ለትግራይ እናት የሚጠቅማት ነገር የለም።
~~~
ምንጨ፦ ናትናኤል አስመላሽ በ Yeneta tube የኔታ ቲዩብ የሰጠው ምስክርነት። አዳም አብርሃም ወደ ጽሁፍ የቀየረው:

Exit mobile version