Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ተኩስ አቁሙን ተላልፎ ከተንኮሰ ክፉኛ ይቀጣል፤ መቀለንም በአጭር ቀን ይነጠቃል

መንግስት የወሰነውን የተኩስ አቁም ሰራዊቱ የሚደግፈውና እየፈጸመው ያለ መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ።ህውሀት ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ትንኮሳ የሚያስብ ከሆነ በአጭር ቀን መልሶ መቀሌን መቆጣጠር እንደሚቻልም አረጋግጠዋል ፡፡

ጀነራሉ ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ም/ሚኒስትር ሬደዋን ሁሴን ጋር በሰጡት መግለጫ ፣ በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻ ወቅት መቀሌ ወታደራዊ የስበት ማእከል ነበረች ፡፡ በአሁኑ ሰአት ግን መቀሌ ለሰራዊታችን የግዳጅ ስበት ማዕከል አይደለችም ብለዋል ።

በአሁኑ ሰዓት ሰራዊታችን መቀሌን ለቆ መውጣቱ ትክክለኛ ውሳኔ ሲሆን ፣ ጁንታው ይህን የተኩስ አቁም ተጠቅሞ ትንኮሳ ካሰበ የከፋ ቅጣት ሊሰጠው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ህወሀት የሀገር ስጋት የነበረው የሰሜን ዕዝን ከማጥቃቱ በፊት ነበር ያሉት ሀላፊው ፣ ሰራዊታችን በወሰደበት እርምጃ አቅሙን ማዳከም በመቻሉ ከወታደራዊ ትንታኔ አኳያ ትግራይ ውስጥ ሰራዊት ማስቀመጥ አስፈላጊ አይደለም ብለዋል።

እንደ ሌተና ጄኔራል ባጫ ማብራርያ ፣ የሀገራችን አሁናዊ ስጋት ሌሎች ሀይሎች ሲሆኑ ህወሀት እየፎከረ እንዳለው ወደ ፈለገበት ተንቀሳቅሶ ጥቃት ማድረስ እንዳይችል የሚያግድ የሰራዊት ተደርጓል።

ለሀገር ስጋት የሆኑ ሀይሎችን መከላከል የሚያስችል ዝግጅትም እየተደረገ ይገኛል።ሰራዊት ተገዶ ሳይሆን አቅዶና በተደራጀ መንገድ ከሺህ በላይ ኮምቦዮችን ይዞ ከትግራይ መውጣቱን የጠቆሙት ጀነራል ባጫ ፣ ህወሀት ጉዞአችንን ለማስተጓጎል ምንም አይነት ትንኮሳ አለመሞከሩ ፣ የማድረግ አቅሙ መዳከሙን የሚመሰክር እንደሆነም ገልፀዋል።

ፀጋዬ ገብሬፎቶግራፍ ኢቢሲ መከላከያ ሚ/ር

Exit mobile version