Site icon ETHIO12.COM

“… ከማንም ጋር ግጭት አንፈልግም ” አብይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ኢትዮጵያ ላይ ግልጽ አደጋ፣ በግልጽ የሚታይ አደጋ እስካልመጣ ድረስ ከማንም ኃይል ጋር ውግያ፣ ግጭት፣ አንፈልግም” ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በሰላምና በትብብር መልማት፣ ማደግ ትፈልጋለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ማደግ ስለምንፈልግ ሰላም እንፈልጋለን፣ ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ነገር እንከፍላለን፣ ሰላም መፈለጋችን ክብራችንን፣ ሕልውናችንን የሚነካ ከሆነ ግን ተገደን ሰላምን ለመምጣት የሚንገባባችው ግጭቶች ይኖራሉ” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፣ “በህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ ፍላጎት፣ የኢትዮጵያን የመብራት ጥያቄ የሚመልስ፣ የሱዳንን ስጋት የሚቀንስ፣ የግብጽን ስጋት የሚቀንስ፣ በቀጠናው ሰላምና ብልጽግናን የሚያመጣ፣ ኃይል ሲመረት በጋራ የምንጠቀምበት፣ የውሃም ችግር ካለ እየተወያየን የምንፈታበት፣ ሰላማዊ የልማት ጉዞ እንዲሆን እንፈልጋለን፤ ለዚህም እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል፡፡

የተለያዩ የዓለም አገራት ኢትዮጵያ ሌሎችን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት፣ በትብብር የማደግ ፍላጎት እንዳላት፣ ተገንዝበው ጉዳዩ ቶሎ ተቋጭቶ ወደ አዳዲስ ልማቶች ለመሄድ በዚህ ሲንነታረክ ጊዜ እንዳናባክን ማገዝ ይኖርባቸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “እኛ ዘፍ የምንተክለው፣ ዝናብ የሚናበራክተው፣ ሱዳን አሁን ከምታገኘው ውሃ በላይ እንዲታገኝ ማድረግ ይቻላል፤ በተከልን ቁጥር ዝናብ ስለምበዛ፣ ግብጽ አሁን ከምታገኘው ውሃ በላይ እንዲታገኝ ማድረግ ይቻላል፣ ለዚያ ምንም ድጋፍ ባናገኝም ዜጎቻችን በቅንነት እያገዙን ስለሆነ በርካታ ዘፍ እየተከልን ዝናብ እናበዛለን፣ ውሃ እናበዛለን፣ የውሃ ብክነት እንቀንሳለን፣ እኛም እንጠቀማለን፣ ሌሎችም እንዲጠቀሙ እንሰራለን”፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ “የምንፈልገው ሰላም ነው፣ የምንፈልገው እድገት ነው፣ ያንን ለመምጣት በትብብር እንሰራለን፣ እኛ እንጀምራለን፣ እንዲያልቅ እንተጋለን፣ ፈጣሪ ያግዘናል፣ በልነው ጊዜ ጨርሰን በድል እንገናኛለን” ብለዋል፡፡ via – EBC

Exit mobile version