Site icon ETHIO12.COM

አብይ አሕመድ ዛሬ በብድር፣ በኑሮ ውድነትና በባለስልጣናት አባካኝነት የተናገሩት

የብድር አሰጣጥ ሂደቱ ካለፈው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተገለፀ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ እና ማብራሪያ እየሰጡ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት በያዝነው ዓመት እንደ ሀገር 20 በመቶ ማደጉን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ከተሰጠው የብድር መጠን ውስጥ ባለተለመደ መልኩ ከ74 በመቶ በላይ ለግል ሴክተሮች የዋለ መሆን ገልፀዋል፡፡ 25 በመቶው የሚሆነው ብድር ደግሞ ለመንግስት ተቋማት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህም ማለት አሁን ለግል ሴክተሮች እየተሰጠ ያለው ትኩረትም ከፍ ማለቱን ያሳያል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒቴር ዶ/ር አብይ ተናግረዋል፡፡ የተሰጡት ብድሮች ቆመው የነበሩ ብዙ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እድንችል አድርጓል ብለዋል፡፡

ኑሮ ውድነት ላለፉት 16 ዓመታት በእጥፍ ጨምሯል ተባለ፡፡

የኑሮ ውድነቱ መናር ሸማቾች ሸምተው ለማደር በእጅጉ ፈተና እንደሆነባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ በሃገሪቱ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ የዋጋ ግሽበቱን የሚያመጡ መንስኤዎችን መለየት እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ሲሆን በተደጋጋሚ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የኑሮ ውድነት መባባስ አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ ተጠይቀዋል፡፡

ለዚህ ምላሽ የሰጡት ዶ/ር አብይ፣ የአቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም ፤በአቅርቦት ሰንሰለቱ ያለው ሳንካ ፤የአምራቾች ምርትን ያለአግባብ መያዝና ሌሎችም ችግሮች ተዳምረው ለዜጎች የኑሮ ውድነት መባባስ ምክንያት እንደሆኑ አንስተዋል፡፡

እስካሁን መንግስት ይህንን የኑሮ ውድነት ለማሻሻል ምግብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች ከውጪ እንዲገቡ ማድረግ፤ለሸማቹ በቂ የግብይት ሰንሰለትን መፍጠር፤የግሉ ሴክተር ተጨማሪ ታክስ ሳይከፍል እንደ ስንዴ፤ዘይት፤የህፃናት ምግብ ከውጪ እንዲገቡ መደረጉን በማንሳት እነዚህ ሙከራዎችም የዋጋ ግሽበቱን ባይቀንሰውም መሻሻል አሳይቷል ብለዋል፡፡

ለዚህ የኑሮ ውድነት መናር ዘለቂታዊ መፍትሄ ነው የሚያስፈልገው ያሉት ዶ/ር አብይ ኢትዮጲያዊያን መሬትን አርሰን ምርትን ማሳደግ ፤የበጋ ስንዴ ውጤትን ማሳደግ፤ ኩታ ገጠም ልማትን ማሳደግ፤ አረንጓዴ ገፅታን ወይንም ዛፍ የመትከል ልማድን ማሳደግ፤ 9 በመቶ ድርሻ ወጪ ብቻ የሚደረግበትን የግብርና ምርትን ማሳደግ፤ ዘርፉን በቴክኖሎጂ፤በፋይናንስ፤መደገፍ፤የሃገር ውስጥ የምግብ ፍጆታን በሃገር ውስጥ እንዲመረት ማድረግ ፤ እንደሚገባና ሌሎችንም አማራጮች በማስፋት የኑሮ ውድነቱ መባባስ ለመቀነስ እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡

ባለስልጣናት ያለ አግባብ የሚያባክኑት ሃብት መቆም አለበት፡፡

በአንዳንድ ክልሎች ላይ በሚሊሻ የሚታጀብ አመራር አለ ይሄም ተገቢ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አህመድ አስታውቀዋል፡፡ ሹመኛ ማለት ሰው ማንጋጋት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይልቁኑም ህዝብን ለማገልገል እድሉን ያገኙ የመንግስት ሃላፊዎች የሚጠበቅባቸው ሃላፊነት በሚገባ መወጣት ይሮርባቸዋል እንጂ የህዝብን ሃብት ያለአግባብ ማባከንና ያልተገባ ወከባ መፍጠር እንደሌለባቸው አሳስበዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ መሰረተ ልማት ላይ በክልሎች ያለው ተደራሽነት ፍታሃዊነት አለው ወይ የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡

በክልሎች በተለየ መልኩ የሚበጀት ፍትሃዊ ያልሆነ በጀት የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይልቁኑም በጀት ብቸኛ የልማት መደገፊያ ያለመሆኑንና በየአካባቢው ተዝቆ የማያልቅ ሃብት መኖሩን እና ያንን ሃብት የመጠቀም ሁኔታ መኖሩ ሊታወቅ እንደሚገባ አሰታውቀዋል፡፡

በየክልሉ የሚበጀተው በጀት ብቻ ሳይሆን ክልሎች ያላቸውን ሃብት በመጠቀም የሚያመጡት የልማት ውጤት በክልሎች ያለውን የመልማት አቅም ይወስነዋል ያሉት ዶ/ር አብይ ለዚህ ደግሞ አመራሮች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በማንሳት፣ ነገር ግን ይሄ መሆን ሲገባው አንዳንድ ባለስልጣናት ባልተገባ መልኩ የሚያባክኑት ጊዜና ሃብት በህዝብ ላይ ተፅእኖ እንደሚያሳድርና ብልፅግናንም የሚያመጣ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

Ethio FM 108

Exit mobile version